Thunder · ar-Ra'd · سورة الرعد · 43 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

المر ۚ تِلْكَ آيَاتُ الْكِتَابِ ۗ وَالَّذِي أُنْزِلَ إِلَيْكَ مِنْ رَبِّكَ الْحَقُّ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يُؤْمِنُونَ

አሊፍ ፤ላም ፤ሚይም፤ ራ፤ (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚህ አናቅጽ ከመጽሐፉ አናቅጽ ናቸው። ያም ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው እውነት ነው። ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያምኑም።

اللَّهُ الَّذِي رَفَعَ السَّمَاوَاتِ بِغَيْرِ عَمَدٍ تَرَوْنَهَا ۖ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ ۖ وَسَخَّرَ الشَّمْسَ وَالْقَمَرَ ۖ كُلٌّ يَجْرِي لِأَجَلٍ مُسَمًّى ۚ يُدَبِّرُ الْأَمْرَ يُفَصِّلُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ بِلِقَاءِ رَبِّكُمْ تُوقِنُونَ

አላህ ያ ሰማያትን የምታይዋት ቋሚዎች ሳይኖራት በችሎታው ከፍ ያረጋት፤ ከዚያ በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ፤ ጸሐይንና ጨረቃንም የገራ ነው። ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ። ነገሩን ሁሉ ያስተናብራል። ከጌታችሁ ጋር መገናኘትን ታረጋግጡ ዘንድ ተዓምራትን ይዘረዝራል።

وَهُوَ الَّذِي مَدَّ الْأَرْضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْهَارًا ۖ وَمِنْ كُلِّ الثَّمَرَاتِ جَعَلَ فِيهَا زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ ۖ يُغْشِي اللَّيْلَ النَّهَارَ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

እርሱ (አላህ)ያ ምድርን የዘረጋ፤ በእርሷም ውስጥ ተራራዎችንና ወንዞችን ያደረገ። በውስጧም ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ዓይነቶችን ያደረገ ነው። ቀኑን በሌሊት ይሸፍናል። በዚህም ውስጥ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች ሁሉ ብዙ ምልክቶች አሉ።

وَفِي الْأَرْضِ قِطَعٌ مُتَجَاوِرَاتٌ وَجَنَّاتٌ مِنْ أَعْنَابٍ وَزَرْعٌ وَنَخِيلٌ صِنْوَانٌ وَغَيْرُ صِنْوَانٍ يُسْقَىٰ بِمَاءٍ وَاحِدٍ وَنُفَضِّلُ بَعْضَهَا عَلَىٰ بَعْضٍ فِي الْأُكُلِ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِقَوْمٍ يَعْقِلُونَ

በምድርም ውስጥ የተጎራበቱ ቁርጥራጮች አሉ። የወይኖች አትክልቶችም፤ አዝርዕቶችም መንታዎችና መንታዎች ያልሆኑ ዘንባባዎችም አሉ። በአንድ ውሃ ይጠጣሉ። በጣዕም ግን ይለያያሉ ከፊልዋንም በከፊሉ ላይ በሚበላው ሰብል እናበልጣለን። በዚህም ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች ሁሉ ብዙ ተአምራት አሉበት።

وَإِنْ تَعْجَبْ فَعَجَبٌ قَوْلُهُمْ أَإِذَا كُنَّا تُرَابًا أَإِنَّا لَفِي خَلْقٍ جَدِيدٍ ۗ أُولَٰئِكَ الَّذِينَ كَفَرُوا بِرَبِّهِمْ ۖ وَأُولَٰئِكَ الْأَغْلَالُ فِي أَعْنَاقِهِمْ ۖ وَأُولَٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ብትደነቅም አፈር በሆንን ጊዜ እኛ አዲስ ፍጥረት እንሆናለን? ማለታቸው በጣም የሚደንቅ ነው። እነዚህ እነዚያ ሰዎች ማለት እነዚያ በጌታቸው የካዱት ሰዎች ናቸው። እነዚህም እንዛዝላዎች በአንገቶቻቸው ላይ ያሉባቸው ናቸው። እነዚህም የእሳት ጓዶች ናቸው። እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው።

وَيَسْتَعْجِلُونَكَ بِالسَّيِّئَةِ قَبْلَ الْحَسَنَةِ وَقَدْ خَلَتْ مِنْ قَبْلِهِمُ الْمَثُلَاتُ ۗ وَإِنَّ رَبَّكَ لَذُو مَغْفِرَةٍ لِلنَّاسِ عَلَىٰ ظُلْمِهِمْ ۖ وَإِنَّ رَبَّكَ لَشَدِيدُ الْعِقَابِ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ በፊት የመሰሎቻቸው ቅጣቶች በእርግጥ ያለፉ ሲሆኑ ከመልካሙ በፊት በመጥፎ ያስቸኩሉሃል! ጌታህም ለሰዎች ሁሉ ከመበደላቸው ጋር በእርግጥ የምህረት ባለቤት ነው። ጌታህ በእርግጥ ቅጣተ ብርቱም ነው።

وَيَقُولُ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْلَا أُنْزِلَ عَلَيْهِ آيَةٌ مِنْ رَبِّهِ ۗ إِنَّمَا أَنْتَ مُنْذِرٌ ۖ وَلِكُلِّ قَوْمٍ هَادٍ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች «በእርሱ ላይ ከጌታው ተአምር ለምን አልተወረደለትም?» ይላሉ። አንተ አስፈራሪ ብቻ ነህ፤ ለሕዝብም ሁሉ መሪ አለላቸው።

اللَّهُ يَعْلَمُ مَا تَحْمِلُ كُلُّ أُنْثَىٰ وَمَا تَغِيضُ الْأَرْحَامُ وَمَا تَزْدَادُ ۖ وَكُلُّ شَيْءٍ عِنْدَهُ بِمِقْدَارٍ

አላህ ሴት ሁሉ የምታረግዘውን ጽንስ ሁሉ ጠንቅቆ ያውቃል። ማሕጸኖች የሚያጎድሉትንም ሆነ የሚጨምሩትን ያውቃል። ነገሩ ሁሉ እርሱ ዘንድ በልክ የተወሰነ ነውና።

عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ الْكَبِيرُ الْمُتَعَالِ

ሩቁንና ቅርቡን አዋቂ የሆነ ታላቅና የላቀ ጌታ ነው።

سَوَاءٌ مِنْكُمْ مَنْ أَسَرَّ الْقَوْلَ وَمَنْ جَهَرَ بِهِ وَمَنْ هُوَ مُسْتَخْفٍ بِاللَّيْلِ وَسَارِبٌ بِالنَّهَارِ

ከናንተ ውስጥ ቃሉን ዝቅ ያደረገ፤ በእርሱ የጮኸም፤ እርሱ በሌሊት ተደባቂም በቀን ተገልፆ ሂያጅም የሆነ ሁሉ (እርሱ አላህ ዘንድ) እኩል ነው (አላህ ያውቀዋል)።

لَهُ مُعَقِّبَاتٌ مِنْ بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ يَحْفَظُونَهُ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوْمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُوا مَا بِأَنْفُسِهِمْ ۗ وَإِذَا أَرَادَ اللَّهُ بِقَوْمٍ سُوءًا فَلَا مَرَدَّ لَهُ ۚ وَمَا لَهُمْ مِنْ دُونِهِ مِنْ وَالٍ

ለእርሱ ለሰው በስተፊቱም ከኋላዉም በአላህ ትዕዛዝ ከክፉ የሚጠብቁት ተተካኪዎች መላዕክት አሉት። አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን (ጸጋ) በነፍሶቻቸው ያለውን (ሁኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም። አላህም በሰዎች ላይ ክፉን በሻ ጊዜ ለእርሱ መመለስ የለዉም። ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም ተከላካይ የላቸዉም።

هُوَ الَّذِي يُرِيكُمُ الْبَرْقَ خَوْفًا وَطَمَعًا وَيُنْشِئُ السَّحَابَ الثِّقَالَ

እርሱ ያ የምትፈሩና የምትከጅሉም ስትሆኑ ብልጭታን የሚያሳያችሁ ከባዶች ደመናዎችንም የሚያስገኝ ነው።

وَيُسَبِّحُ الرَّعْدُ بِحَمْدِهِ وَالْمَلَائِكَةُ مِنْ خِيفَتِهِ وَيُرْسِلُ الصَّوَاعِقَ فَيُصِيبُ بِهَا مَنْ يَشَاءُ وَهُمْ يُجَادِلُونَ فِي اللَّهِ وَهُوَ شَدِيدُ الْمِحَالِ

ነጎድጓድም አላህን በማመስገን ያጠራል። መላዕክትም እርሱን ከመፍራት ያጠሩታል፤ መብረቆችንም ይልካል። እነርሱም (ከሓዲያን) በአላህ የሚከራከሩ ሲሆኑ በእርሷ የሚሻውን ሰው ይመታል። እርሱም ሀይለ ብርቱ ነው።

لَهُ دَعْوَةُ الْحَقِّ ۖ وَالَّذِينَ يَدْعُونَ مِنْ دُونِهِ لَا يَسْتَجِيبُونَ لَهُمْ بِشَيْءٍ إِلَّا كَبَاسِطِ كَفَّيْهِ إِلَى الْمَاءِ لِيَبْلُغَ فَاهُ وَمَا هُوَ بِبَالِغِهِ ۚ وَمَا دُعَاءُ الْكَافِرِينَ إِلَّا فِي ضَلَالٍ

ለእርሱ(አላህ) የእውነት ጥሪ አለው። እነዚያ ከእርሱ ሌላ የሚገዟቸው ጣዖታት ምሳሌው ወደ አፉ ይደርስ ዘንድ ወደ ውሃ መዳፎቹን በሩቅ ሆኖ እንደሚዘረጋና እንደማይደርስባት ሰው እንጂ ለእነርሱ በምንም አይመልሱላቸዉም። እርሱም ወደ አፉ ደራሽ አይደለም። የከሓዲያን ጥሪ በከንቱ ልፋት እንጂ ሌላ አይደለም።

وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَنْ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَظِلَالُهُمْ بِالْغُدُوِّ وَالْآصَالِ ۩

በሰማያትና በምድር ያሉት ሁሉ በዉድም ሆነ በግድ ለአላህ ይሰግዳሉ። ጥላዎቻቸዉም በጧቶችና በማታዎች ይሰግዳሉ።

قُلْ مَنْ رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ قُلِ اللَّهُ ۚ قُلْ أَفَاتَّخَذْتُمْ مِنْ دُونِهِ أَوْلِيَاءَ لَا يَمْلِكُونَ لِأَنْفُسِهِمْ نَفْعًا وَلَا ضَرًّا ۚ قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الْأَعْمَىٰ وَالْبَصِيرُ أَمْ هَلْ تَسْتَوِي الظُّلُمَاتُ وَالنُّورُ ۗ أَمْ جَعَلُوا لِلَّهِ شُرَكَاءَ خَلَقُوا كَخَلْقِهِ فَتَشَابَهَ الْخَلْقُ عَلَيْهِمْ ۚ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው?» በላቸው። «አላህ ነው።» በልም። «ለነፍሶቻቸው ጥቅምንም ጉዳትን የማይችሉን ረዳቶች ከእርሱ ሌላ ያዛችሁን?» በላቸው። «እውርና የሚያይ ይስተካከላሉን? ወይስ ጨለማዎችና ብርሃን ይስተካከላሉን? ወይስ ለአላህ እንደ እርሱ አፈጣጠር የፈጠሩን ተጋሪዎች አረጉለትና ፍጥረቱ በእነርሱ ላይ ተመሳሰለባቸውን?» በልም። «አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው። እርሱም ብቸኛውና ሁሉን አሸናፊው ነው።» በል።

أَنْزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَسَالَتْ أَوْدِيَةٌ بِقَدَرِهَا فَاحْتَمَلَ السَّيْلُ زَبَدًا رَابِيًا ۚ وَمِمَّا يُوقِدُونَ عَلَيْهِ فِي النَّارِ ابْتِغَاءَ حِلْيَةٍ أَوْ مَتَاعٍ زَبَدٌ مِثْلُهُ ۚ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ الْحَقَّ وَالْبَاطِلَ ۚ فَأَمَّا الزَّبَدُ فَيَذْهَبُ جُفَاءً ۖ وَأَمَّا مَا يَنْفَعُ النَّاسَ فَيَمْكُثُ فِي الْأَرْضِ ۚ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ الْأَمْثَالَ

ከሰማይ ውሃን አወረደ። ሸለቆዎቹም በየመጠናቸው ፈሰሱ። ጎርፉም አስፋሪውን የውሃ አረፋ ተሸከመ። ለጌጥ ወይም ለዕቃ ፍላጎት በእርሱ ላይ እሳት የሚያነዱበትም ማዕድን ብጤው የሆነ ኮረፋት አለው። ልክ እንደዚሁ አላህ ለእውነትና ለውሸት ምሳሌን ያደርጋል። የውሃ አረፋዉም ግብስብስ ሆኖ ይጠፋል። ለሰዎች የሚጠቅመውማ በምድር ላይ ይቆያል። ልክ እንደዚሁ አላህ ምሳሌዎችን ይገልጻል።

لِلَّذِينَ اسْتَجَابُوا لِرَبِّهِمُ الْحُسْنَىٰ ۚ وَالَّذِينَ لَمْ يَسْتَجِيبُوا لَهُ لَوْ أَنَّ لَهُمْ مَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا وَمِثْلَهُ مَعَهُ لَافْتَدَوْا بِهِ ۚ أُولَٰئِكَ لَهُمْ سُوءُ الْحِسَابِ وَمَأْوَاهُمْ جَهَنَّمُ ۖ وَبِئْسَ الْمِهَادُ

ለእነዚያ ለጌታቸው ለታዘዙት ሰዎች መልካም ነገር ገነት አለላቸው። እነዚያም ለእርሱ ያልታዘዙት ለእነርሱ በምድር ያለው ሁሉ ከእርሱም ጋር ብጤው ቢኖራቸው ኖሮ በእርሱ በተበዡበት ነበር። እነዚያ ለእነርሱ ክፉ ምርመራ አለባቸው። መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት። ፍራሻቸዉም ገሀነም ከፋች!

أَفَمَنْ يَعْلَمُ أَنَّمَا أُنْزِلَ إِلَيْكَ مِنْ رَبِّكَ الْحَقُّ كَمَنْ هُوَ أَعْمَىٰ ۚ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُولُو الْأَلْبَابِ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው ሁሉ እውነት መሆኑን የሚያውቅ ሰው ልክ እንደዚያ እርሱ እውር እንደ ሆነው ሰው ነውን? የሚገሠጹት የአእምሮ ባለቤቶች ብቻ ናቸው።

الَّذِينَ يُوفُونَ بِعَهْدِ اللَّهِ وَلَا يَنْقُضُونَ الْمِيثَاقَ

እነዚያ የአላህን ቃል ኪዳን የሚሞሉ የጠበቀውንም ኪዳን የማያፈርሱ ናቸው።

وَالَّذِينَ يَصِلُونَ مَا أَمَرَ اللَّهُ بِهِ أَنْ يُوصَلَ وَيَخْشَوْنَ رَبَّهُمْ وَيَخَافُونَ سُوءَ الْحِسَابِ

እነዚያም አላህ እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቀጥሉ፤ ጌታቸውንም የሚፈሩ፤ ክፉንም ምርመራ የሚፈሩ ናቸው።

وَالَّذِينَ صَبَرُوا ابْتِغَاءَ وَجْهِ رَبِّهِمْ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَأَنْفَقُوا مِمَّا رَزَقْنَاهُمْ سِرًّا وَعَلَانِيَةً وَيَدْرَءُونَ بِالْحَسَنَةِ السَّيِّئَةَ أُولَٰئِكَ لَهُمْ عُقْبَى الدَّارِ

እነዚያም የጌታቸውን ፊት (ውዴታ) ለመፈለግ የታገሱ ሶላትንም አዘውትረው የሰገዱ ሰዎች እኛ ከሰጠናቸው ሲሳይም በምስጢርም ሆነ በግልጽ የመጸወቱ ክፉውንም በበጎ የሚገፈትሩ ናቸው። እነዚያ ለእነርሱ መጨረሻይቱ ምስጉን አገር አለችላቸው።

جَنَّاتُ عَدْنٍ يَدْخُلُونَهَا وَمَنْ صَلَحَ مِنْ آبَائِهِمْ وَأَزْوَاجِهِمْ وَذُرِّيَّاتِهِمْ ۖ وَالْمَلَائِكَةُ يَدْخُلُونَ عَلَيْهِمْ مِنْ كُلِّ بَابٍ

እርሷም የመኖሪያ ገነቶች ናት። ይገቡባታል። ከአባቶቻቸዉም ከሚስቶቻቸዉም ከዝርያቸዉም መልካም የሠራ ሰው ሁሉ ይገባባታል። መላዕክትም በእነርሱ ላይ ከየደጃፉ ሁሉ ይገባሉ።

سَلَامٌ عَلَيْكُمْ بِمَا صَبَرْتُمْ ۚ فَنِعْمَ عُقْبَى الدَّارِ

«ሰላም ለእናንተ ይሁን። ይህ ምንዳ በመታገሳችሁ የተሰጣችሁ ነው። የመጨረሻይቱም ሀገር ምን ታምር!» ይሏቸዋል።

وَالَّذِينَ يَنْقُضُونَ عَهْدَ اللَّهِ مِنْ بَعْدِ مِيثَاقِهِ وَيَقْطَعُونَ مَا أَمَرَ اللَّهُ بِهِ أَنْ يُوصَلَ وَيُفْسِدُونَ فِي الْأَرْضِ ۙ أُولَٰئِكَ لَهُمُ اللَّعْنَةُ وَلَهُمْ سُوءُ الدَّارِ

እነዚያ የአላህን ቃል ኪዳን ከጠበቀ በኋላ የሚያፈርሱ፤ አላህም እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ፤ በምድርም ላይ የሚያበላሹ እነዚያ ለእነርሱ እርግማን አለባቸው። ለእነርሱም መጥፎ ሀገር ገሀነም አለላቸው።

اللَّهُ يَبْسُطُ الرِّزْقَ لِمَنْ يَشَاءُ وَيَقْدِرُ ۚ وَفَرِحُوا بِالْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا فِي الْآخِرَةِ إِلَّا مَتَاعٌ

አላህ ለሚሻው ሁሉ ሲሳይን ያሰፋል። ለሚሻውም ያጠባል። ከሓዲያን በቅርቢቱም ሕይወት ተደሰቱ። የቅርቢቱም ሕይወት ከመጨረሻይቱ አንጻር ትንሽ መጠቀሚያ እንጂ ምንም አይደለችም።

وَيَقُولُ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْلَا أُنْزِلَ عَلَيْهِ آيَةٌ مِنْ رَبِّهِ ۗ قُلْ إِنَّ اللَّهَ يُضِلُّ مَنْ يَشَاءُ وَيَهْدِي إِلَيْهِ مَنْ أَنَابَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ የካዱት ሰዎች «በእርሱ ላይ ከጌታው ተዓምር ለምን አልተወረደለትም?» ይላሉ። «አላህ የሚሻውን ሰው ያጠምማል። የተመለሰንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል።» በላቸው።

الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُمْ بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ

እነርሱም እነዚያ በአላህ ያመኑ ልቦቻቸዉም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው። አስተውሉ። አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ።

الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ طُوبَىٰ لَهُمْ وَحُسْنُ مَآبٍ

እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካም ስራዎችን የሠሩት ለእነርሱ ደግ ኑሮና መልካም መመለሻ አለላቸው።

كَذَٰلِكَ أَرْسَلْنَاكَ فِي أُمَّةٍ قَدْ خَلَتْ مِنْ قَبْلِهَا أُمَمٌ لِتَتْلُوَ عَلَيْهِمُ الَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَهُمْ يَكْفُرُونَ بِالرَّحْمَٰنِ ۚ قُلْ هُوَ رَبِّي لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَإِلَيْهِ مَتَابِ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ ከበፊትዋ ብዙ ሕዝቦች በእርግጥ ያለፉ ወደ ሆነችው ሕዝብ እነርሱ በአር-ረህማን የሚክዱ ሲሆኑ ያንን ወደ አንተ ያወረድነውን ቁርኣን በእነርሱ ላይ ታነብላቸው ዘንድ ላክንህ። «እርሱ አር-ረህማን ጌታዬ ነው። ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም። በእርሱ ላይ ተመካሁ። መመለሻዬም ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው።

وَلَوْ أَنَّ قُرْآنًا سُيِّرَتْ بِهِ الْجِبَالُ أَوْ قُطِّعَتْ بِهِ الْأَرْضُ أَوْ كُلِّمَ بِهِ الْمَوْتَىٰ ۗ بَلْ لِلَّهِ الْأَمْرُ جَمِيعًا ۗ أَفَلَمْ يَيْأَسِ الَّذِينَ آمَنُوا أَنْ لَوْ يَشَاءُ اللَّهُ لَهَدَى النَّاسَ جَمِيعًا ۗ وَلَا يَزَالُ الَّذِينَ كَفَرُوا تُصِيبُهُمْ بِمَا صَنَعُوا قَارِعَةٌ أَوْ تَحُلُّ قَرِيبًا مِنْ دَارِهِمْ حَتَّىٰ يَأْتِيَ وَعْدُ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُخْلِفُ الْمِيعَادَ

ቁርኣንም በእርሱ ተራራዎች የሚነዱበት፤ ወይም በእርሱ ምድር የሚቆራረጥበት፤ ወይም በእርሱ ሙታን እንዲናገሩ የሚደረጉበት ቢሆን ኖሮ (ይሀው ቁርአን በሆነ ነበር።) በእውነቱ ነገሩ ሁሉ የአላህ ነው። እነዚያ በአላህ ያመኑት ሰዎች እነሆ አላህ በሻ ኖሮ ሰዎችን በመላ በእርግጥ ወደ ቀናው መንገድ ይመራቸው እንደ ነበረ አያውቁምን? እነዚያን የካዱት በሥራቸው ምክንያት አጥፊ አደጋ የምታገኛቸው ከመሆን ወይም የአላህ ቀጠሮ እስኪመጣ በሀገራቸው አቅራቢያ አንተ የምትሰፍርባቸው ከመሆን አይወገዱም። አላህ ቀጠሮውን አያፈርስምና።

وَلَقَدِ اسْتُهْزِئَ بِرُسُلٍ مِنْ قَبْلِكَ فَأَمْلَيْتُ لِلَّذِينَ كَفَرُوا ثُمَّ أَخَذْتُهُمْ ۖ فَكَيْفَ كَانَ عِقَابِ

ካንተ በፊት የነበሩትም መልዕክተኞች በእርግጥ ተላግጦባቸው ነበር። እናም ለእነዚያም ለካዱት ጊዜን ሰጠኋቸው። ከዚያም በቅጣት ያዝኳቸው። ቅጣቴ እንዴት ነበር (ምን ያህል የከፋ ነበር።)

أَفَمَنْ هُوَ قَائِمٌ عَلَىٰ كُلِّ نَفْسٍ بِمَا كَسَبَتْ ۗ وَجَعَلُوا لِلَّهِ شُرَكَاءَ قُلْ سَمُّوهُمْ ۚ أَمْ تُنَبِّئُونَهُ بِمَا لَا يَعْلَمُ فِي الْأَرْضِ أَمْ بِظَاهِرٍ مِنَ الْقَوْلِ ۗ بَلْ زُيِّنَ لِلَّذِينَ كَفَرُوا مَكْرُهُمْ وَصُدُّوا عَنِ السَّبِيلِ ۗ وَمَنْ يُضْلِلِ اللَّهُ فَمَا لَهُ مِنْ هَادٍ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነፍስ ሁሉ በሰራችው ሥራ ላይ ተጠባባቂ የሆነው አላህም እንደዚህ እንዳልሆነው ጣዖት ብጤ ነውን? ለአላህ ተጋሪዎችን አደረጉ። «ጥሯቸው። አላህን በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን? ወይስ ከቃል በቀጥታ ፍቺ በሌለው ከንቱ ቃል ተጋሪዎቹ በማለት ትጠሯቸዋላችሁን?» በላቸው። በእውነቱ ለእነዚያ ለካዱት ተንኮላቸው ተሸለመላቸው። ከእውነቱ መንገድም ታገዱ። አላህ ያጠመመውንም ምንም አቅኚ የለዉም።

لَهُمْ عَذَابٌ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۖ وَلَعَذَابُ الْآخِرَةِ أَشَقُّ ۖ وَمَا لَهُمْ مِنَ اللَّهِ مِنْ وَاقٍ

ለእነርሱ በቅርቢቱ ሕይወት ቅጣት አለባቸው። የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት በጣም የበረታ ነው። ለእነርሱ ከአላህ ቅጣት ምንም ጠባቂ የላቸዉም።

مَثَلُ الْجَنَّةِ الَّتِي وُعِدَ الْمُتَّقُونَ ۖ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ۖ أُكُلُهَا دَائِمٌ وَظِلُّهَا ۚ تِلْكَ عُقْبَى الَّذِينَ اتَّقَوْا ۖ وَعُقْبَى الْكَافِرِينَ النَّارُ

ያች ጥንቁቆች ተስፋ የተሰጧት ገነት ምጣኔዋ (ምሳሌዋ) እንደሚነገራችሁ ነው። ከሥርዋ ወንዞች ይፈሳሉ። ምግቧ ሁል ጊዜም የማያቋርጥ ነው። ጥላዋም እንደዚሁ። ይህች ገነት የእነዚያ የተጠነቀቁት መጨረሻ ናት። የከሓዲያን መጨረሻ ግን እሳት ናት።

وَالَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ يَفْرَحُونَ بِمَا أُنْزِلَ إِلَيْكَ ۖ وَمِنَ الْأَحْزَابِ مَنْ يُنْكِرُ بَعْضَهُ ۚ قُلْ إِنَّمَا أُمِرْتُ أَنْ أَعْبُدَ اللَّهَ وَلَا أُشْرِكَ بِهِ ۚ إِلَيْهِ أَدْعُو وَإِلَيْهِ مَآبِ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም መጽሐፉን የሰጠናቸው ወደ አንተ በተወረደው ይደሰታሉ። ከአህዛብም ከፊሉን የሚክዱ ሰዎች አሉ። «እኔ የታዘዝኩት አላህን ብቻ እንድገዛና በእርሱም እንዳላጋራ ነው። ወደ እርሱ እጠራለሁ። መመለሻዬም ወደ እርሱ ብቻ ነው።» በላቸው።

وَكَذَٰلِكَ أَنْزَلْنَاهُ حُكْمًا عَرَبِيًّا ۚ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُمْ بَعْدَمَا جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ مَا لَكَ مِنَ اللَّهِ مِنْ وَلِيٍّ وَلَا وَاقٍ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትህ ሲሆን አወረድነው። እውቀቱ ከመጣልህም በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን ብትከተል ከአላህ ቅጣት ወዳጅም ሆነ ጠባቂ ምንም የለህም።

وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِنْ قَبْلِكَ وَجَعَلْنَا لَهُمْ أَزْوَاجًا وَذُرِّيَّةً ۚ وَمَا كَانَ لِرَسُولٍ أَنْ يَأْتِيَ بِآيَةٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۗ لِكُلِّ أَجَلٍ كِتَابٌ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ብዙ መልዕክተኞችን በእርግጥ ልከናል። ለእነርሱም ሚስቶችንና ልጆችን አድርገናል። ማንኛዉም መልዕክተኛ በአላህ ፈቃድ እንጂ ተዓምር ሊያመጣ አይገባዉም። ለየጊዜው ሁሉ ጽሑፍ አለው።

يَمْحُو اللَّهُ مَا يَشَاءُ وَيُثْبِتُ ۖ وَعِنْدَهُ أُمُّ الْكِتَابِ

አላህ የሚፈልገውን ያብሳል። የሚሻውን ያጸድቃል። የመጽሐፉ ዋና መሠረትም እርሱ ዘንድ ብቻ ነው።

وَإِنْ مَا نُرِيَنَّكَ بَعْضَ الَّذِي نَعِدُهُمْ أَوْ نَتَوَفَّيَنَّكَ فَإِنَّمَا عَلَيْكَ الْبَلَاغُ وَعَلَيْنَا الْحِسَابُ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዚያን ያስፈራራናቸውን ቅጣት ከፊሉን በሕይወት እያለህ ብናሳይህ መልካም ነው። ወይም ሳናሳይህ ብንወስድህ (ወቀሳ የለብህም)። ባንተ ላይ ያለብህ መልዕክትህን ማድረስ ብቻ ነው። ምርመራው ግን በእኛ ላይ ነው።

أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّا نَأْتِي الْأَرْضَ نَنْقُصُهَا مِنْ أَطْرَافِهَا ۚ وَاللَّهُ يَحْكُمُ لَا مُعَقِّبَ لِحُكْمِهِ ۚ وَهُوَ سَرِيعُ الْحِسَابِ

እኛ ምድርን ከጫፎችዋ የምናጎድላት ሆነን የምናመጣባት መሆናችንን አላወቁምን? አላህም ይፈርዳል። ለፍርዱም በይግባኝ ገልባጭ የለዉም። እርሱም ምርመራው ፈጣን ነው።

وَقَدْ مَكَرَ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ فَلِلَّهِ الْمَكْرُ جَمِيعًا ۖ يَعْلَمُ مَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ ۗ وَسَيَعْلَمُ الْكُفَّارُ لِمَنْ عُقْبَى الدَّارِ

እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት ሰዎች መከሩ (አሴሩ)። አዘንግቶም የመያዙ ዘዴ በሙሉ የአላህ ብቻ ነው። አላህ ነፍስ ሁሉ የምትሰራውን ያውቃል። ከሓዲያን የመጨረሻይቱ አገር ለማን እንደምትሆን ወደፊት ያውቃሉ።

وَيَقُولُ الَّذِينَ كَفَرُوا لَسْتَ مُرْسَلًا ۚ قُلْ كَفَىٰ بِاللَّهِ شَهِيدًا بَيْنِي وَبَيْنَكُمْ وَمَنْ عِنْدَهُ عِلْمُ الْكِتَابِ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ የካዱ ሰዎች «መልእክተኛ አይደለህም።» ይላሉ። «በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በአላህና እርሱ ዘንድ የመጽሐፉ እውቀት ባለው ሰው በቃ።» በላቸው።