أَتَىٰ أَمْرُ اللَّهِ فَلَا تَسْتَعْجِلُوهُ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ
(ከሓዲያን ሆይ!)፤ የአላህ ትዕዛዝ መጣ ስለዚህ አታጣድፉት። አላህ ከማይገባው ሁሉ ጠራ። ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ።
القرآن الكريمAfrica Academy
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።
أَتَىٰ أَمْرُ اللَّهِ فَلَا تَسْتَعْجِلُوهُ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ
(ከሓዲያን ሆይ!)፤ የአላህ ትዕዛዝ መጣ ስለዚህ አታጣድፉት። አላህ ከማይገባው ሁሉ ጠራ። ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ።
يُنَزِّلُ الْمَلَائِكَةَ بِالرُّوحِ مِنْ أَمْرِهِ عَلَىٰ مَنْ يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ أَنْ أَنْذِرُوا أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاتَّقُونِ
ከባሮቹ መካከል በሚሻው ሰው ላይ መላዕክትን ከራዕይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል። «እነሆ ከእኔ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም። ፍሩኝም።» በማለት (ሰዎችን) አስጠንቅቁ በማለት ያወርዳል።
خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ ۚ تَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ
ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ። ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ ። ከፍም አለ።
خَلَقَ الْإِنْسَانَ مِنْ نُطْفَةٍ فَإِذَا هُوَ خَصِيمٌ مُبِينٌ
ሰውን ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው። ከዚያም እርሱ ወዲያውኑ (ትንሣኤን በመካድ) ግልጽ ተከራካሪ ይሆናል።
وَالْأَنْعَامَ خَلَقَهَا ۗ لَكُمْ فِيهَا دِفْءٌ وَمَنَافِعُ وَمِنْهَا تَأْكُلُونَ
(ሰዎች ሆይ!) ግመልን፤ ከብትን፤ ፍየልንም፤ በእርሷ ብርድ መከላከያ ሙቀትና ሌሎች ጥቅሞችም ያሉባት ስትሆን ለእናንተ ፈጠረላችሁ። ከእርሷም ትበላላችሁ (ትመገባላችሁ)።
وَلَكُمْ فِيهَا جَمَالٌ حِينَ تُرِيحُونَ وَحِينَ تَسْرَحُونَ
በእርሷም ወደ ማረፊያዋ በምትመልሷት ጊዜና ጧት ወደ ግጦሽ ቦታዋ በምታሰማሯት ወቅት ለእናንተ ውበት አለላችሁ።
وَتَحْمِلُ أَثْقَالَكُمْ إِلَىٰ بَلَدٍ لَمْ تَكُونُوا بَالِغِيهِ إِلَّا بِشِقِّ الْأَنْفُسِ ۚ إِنَّ رَبَّكُمْ لَرَءُوفٌ رَحِيمٌ
ጓዞቻችሁንም ነፍሶቻችሁን በማስቸገር እንጂ ወደ ማትደርሱበት አገር ትሸከማለች። ጌታችሁ በእርግጥ ሩህሩህ እና አዛኝ ነውና።
وَالْخَيْلَ وَالْبِغَالَ وَالْحَمِيرَ لِتَرْكَبُوهَا وَزِينَةً ۚ وَيَخْلُقُ مَا لَا تَعْلَمُونَ
ፈረሶችን፤ በቅሎዎችንና አህዮችን ልትጋልቧቸውና ልታጌጡባቸው ፈጠረላችሁ። የማታውቁትን ድንቅ ነገርም ወደ ፊት ይፈጥራል።
وَعَلَى اللَّهِ قَصْدُ السَّبِيلِ وَمِنْهَا جَائِرٌ ۚ وَلَوْ شَاءَ لَهَدَاكُمْ أَجْمَعِينَ
በአላህም ላይ በችሮታው ቀጥተኛውን መንገድ መግለጽ አለበት። ከእርሷም ጠማማ አለ። በሻም ኖሮ ሁላችሁንም ባቀናችሁ ነበር።
هُوَ الَّذِي أَنْزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً ۖ لَكُمْ مِنْهُ شَرَابٌ وَمِنْهُ شَجَرٌ فِيهِ تُسِيمُونَ
እርሱ ያ ከሰማይ ውሃን ያወረደ ነው። ከእርሱም ለእናንተ መጠጥ አለላችሁ። ከእርሱም እንስሳዎችን በእርሱ ውስጥ የምታሰማሩበት ዛፍ ይበቅልበታል።
يُنْبِتُ لَكُمْ بِهِ الزَّرْعَ وَالزَّيْتُونَ وَالنَّخِيلَ وَالْأَعْنَابَ وَمِنْ كُلِّ الثَّمَرَاتِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
በእርሱ አዝመራን፣ የዘይት ወይራን፣ ዘምባባዎችን፣ ወይኖችንና ከፍሬዎችም ሁሉ ያበቅልላችኋል። በዚህ ክስተት ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ሁሉ በእርግጥ ትልቅ ተዓምር አለ።
وَسَخَّرَ لَكُمُ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ ۖ وَالنُّجُومُ مُسَخَّرَاتٌ بِأَمْرِهِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِقَوْمٍ يَعْقِلُونَ
ለእናንተ ሌሊትንና ቀንን ጸሐይንና ጨረቃንም ገራላችሁ። ከዋክብትም በሙሉ በፈቃዱ ብቻ የተገሩ ናቸው። በዚህ ክስተት ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች ሁሉ በእርግጥ አያሌ ተዓምራት አሉ።
وَمَا ذَرَأَ لَكُمْ فِي الْأَرْضِ مُخْتَلِفًا أَلْوَانُهُ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِقَوْمٍ يَذَّكَّرُونَ
በምድርም ላይ መልኮቹ የተለያዩ ሆኖ የፈጠረላችሁን ሁሉ ገራላችሁ። በዚህ ውስጥ ለሚገሠጹ ሕዝቦች ሁሉ ግልጽ ተዐምር አለ።
وَهُوَ الَّذِي سَخَّرَ الْبَحْرَ لِتَأْكُلُوا مِنْهُ لَحْمًا طَرِيًّا وَتَسْتَخْرِجُوا مِنْهُ حِلْيَةً تَلْبَسُونَهَا وَتَرَى الْفُلْكَ مَوَاخِرَ فِيهِ وَلِتَبْتَغُوا مِنْ فَضْلِهِ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
እርሱ ያ ባሕርን ከእርሱ እርጥብ ስጋን ልትበሉና ከእርሱም የምትለብሱትን ጌጣጌጥ ታወጡ ዘንድ የገራ ነው። መርከቦችንም በውስጡ ውሃውን ቀዳጆች ሆነው ሲንሻለሉ ታያለህ። ከችሮታው ልትፈልጉና ልታመሰግኑም ገራላችሁ።
وَأَلْقَىٰ فِي الْأَرْضِ رَوَاسِيَ أَنْ تَمِيدَ بِكُمْ وَأَنْهَارًا وَسُبُلًا لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ
በምድር ውስጥ በናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለባት። ትመሩም ዘንድ ጅረቶችንና መንገዶችን አደረገ።
وَعَلَامَاتٍ ۚ وَبِالنَّجْمِ هُمْ يَهْتَدُونَ
ምልክቶችንም አደረገ። በከዋክብትም እነርሱ ይመራሉ።
أَفَمَنْ يَخْلُقُ كَمَنْ لَا يَخْلُقُ ۗ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
(ሰዎች ሆይ!) የሚፈጥር ልክ እንደማይፈጥር ነውን? አትገሠጹምን?
وَإِنْ تَعُدُّوا نِعْمَةَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا ۗ إِنَّ اللَّهَ لَغَفُورٌ رَحِيمٌ
የአላህን ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም። አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና።
وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا تُسِرُّونَ وَمَا تُعْلِنُونَ
አላህ የምትደብቁትንና የምትገልጹትንም ሁሉ ያውቃል።
وَالَّذِينَ يَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ لَا يَخْلُقُونَ شَيْئًا وَهُمْ يُخْلَقُونَ
እነዚያም ከአላህ ሌላ የሚገዟቸው አማልክት ሁሉ ምንንም አይፈጥሩም። እንዲያዉም እነርሱ ራሳቸው ይፈጠራሉ።
أَمْوَاتٌ غَيْرُ أَحْيَاءٍ ۖ وَمَا يَشْعُرُونَ أَيَّانَ يُبْعَثُونَ
እነርሱ ሕያው ያልሆኑ ሙታን ናቸው። እራሳቸው እንኳን መቼ እንደሚቀሰቀሱ አያውቁም።
إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ ۚ فَالَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ قُلُوبُهُمْ مُنْكِرَةٌ وَهُمْ مُسْتَكْبِرُونَ
አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው። እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ልቦቻቸው ከሓዲያን ናቸው። እነርሱም የኮሩ ናቸው።
لَا جَرَمَ أَنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعْلِنُونَ ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الْمُسْتَكْبِرِينَ
አላህ የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ሁሉ የሚያውቅ ለመሆኑ ቅንጣት ያህል ጥርጣሬ የለበትም። እርሱ ኩሩዎችን አይወድም።
وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ مَاذَا أَنْزَلَ رَبُّكُمْ ۙ قَالُوا أَسَاطِيرُ الْأَوَّلِينَ
ጌታችሁ (በሙሐመድ ላይ) ምን አወረደ በተባሉ ጊዜም: «እርሱ የመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ተረቶች ነው።» ይላሉ።
لِيَحْمِلُوا أَوْزَارَهُمْ كَامِلَةً يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۙ وَمِنْ أَوْزَارِ الَّذِينَ يُضِلُّونَهُمْ بِغَيْرِ عِلْمٍ ۗ أَلَا سَاءَ مَا يَزِرُونَ
ይህንን የሚሉት በትንሣኤ ቀን ኃጢአቶቻቸውን በሙሉና ከነዚያም ያለ ዕውቀት ሆነው ከሚያጣምሟቸው ሰዎች ኃጢአቶች ከፊሉን ሊሸከሙ ነው። ንቁ የሚሸከሙት ኃጢአት ምንኛ ከፋ!
قَدْ مَكَرَ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ فَأَتَى اللَّهُ بُنْيَانَهُمْ مِنَ الْقَوَاعِدِ فَخَرَّ عَلَيْهِمُ السَّقْفُ مِنْ فَوْقِهِمْ وَأَتَاهُمُ الْعَذَابُ مِنْ حَيْثُ لَا يَشْعُرُونَ
እነዚያ ከእነርሱ (ከቁረይሾች) በፊት የነበሩት ከሓዲያን አሴሩ። ከዚያም አላህ ሕንጻዎቻቸውን ከመሠረቶቻቸው አፈረሰ። እናም ጣሪያው በላያቸው ላይ ወደቀባቸው። ቅጣቱም ከማያውቁት ስፍራ መጣባቸው።
ثُمَّ يَوْمَ الْقِيَامَةِ يُخْزِيهِمْ وَيَقُولُ أَيْنَ شُرَكَائِيَ الَّذِينَ كُنْتُمْ تُشَاقُّونَ فِيهِمْ ۚ قَالَ الَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ إِنَّ الْخِزْيَ الْيَوْمَ وَالسُّوءَ عَلَى الْكَافِرِينَ
ከዚያም በትንሣኤ ቀን ያዋርዳቸዋል። «እነዚያም በእነርሱ ጉዳይ ትከራከሩኝ የነበራችሁት ተጋሪዎቼ የት ናቸው?» ይላቸዋል። እነዚያ እውቀትን የተሰጡት ክፍሎች «ዛሬ ሐፍረቱና ቅጣቱ በከሓዲያን ላይ ነው።» ይላሉ።
الَّذِينَ تَتَوَفَّاهُمُ الْمَلَائِكَةُ ظَالِمِي أَنْفُسِهِمْ ۖ فَأَلْقَوُا السَّلَمَ مَا كُنَّا نَعْمَلُ مِنْ سُوءٍ ۚ بَلَىٰ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ بِمَا كُنْتُمْ تَعْمَلُونَ
እነዚያ ነፍሶቻቸውን በዳይ ሆነው መላዕክት ነፍሳቸውን የሚወስዷቸው «ከክፉ ሥራ ምንም ነገር የምንሠራም አልነበርንም» ሲሉ ታዛዥነታቸውን ይገልፃሉ። «አይደለም! (ትሠሩ ነበር)፤ አላህ ትሠሩት የነበራችሁትን ነገር በእርግጥ አዋቂ ነው።» ይባላሉ።
فَادْخُلُوا أَبْوَابَ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا ۖ فَلَبِئْسَ مَثْوَى الْمُتَكَبِّرِينَ
«የገሀነምንም ደጃፎች በውስጧ ዘውታሪዎች ስትሆኑ ግቡ።» ይባላሉ። የኩሩ ሰዎች ሁሉ መኖሪያ የሆነችው ገሀነምም በእርግጥ ከፋች!
وَقِيلَ لِلَّذِينَ اتَّقَوْا مَاذَا أَنْزَلَ رَبُّكُمْ ۚ قَالُوا خَيْرًا ۗ لِلَّذِينَ أَحْسَنُوا فِي هَٰذِهِ الدُّنْيَا حَسَنَةٌ ۚ وَلَدَارُ الْآخِرَةِ خَيْرٌ ۚ وَلَنِعْمَ دَارُ الْمُتَّقِينَ
ለእነዚያም ለተጠነቀቁት ሰዎች «ጌታችሁ ምንን ነገር አወረደ?» ተባሉ። «መልካምን ነገር አወረደ» አሉ። ለእነዚያ ደግ ለሠሩት ህዝቦች ሁሉ በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ኑሮ አለላቸው። የመጨረሻይቱም አገር በእርግጥ በላጭ ናት። የጥንቁቆቹም አገር ገነት ምን ታምር!
جَنَّاتُ عَدْنٍ يَدْخُلُونَهَا تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ۖ لَهُمْ فِيهَا مَا يَشَاءُونَ ۚ كَذَٰلِكَ يَجْزِي اللَّهُ الْمُتَّقِينَ
እርሷም የሚገቧትና በሥርዋ ወንዞች የሚፈሱባት ስትሆን የመኖሪያ አትክልቶች (ጀነት) ናት። ለእነርሱም በውስጧ የሚሹት ነገር ሁሉ አለላቸው። ልክ እንደዚሁም አላህ ጥንቁቆችን ይመነዳል።
الَّذِينَ تَتَوَفَّاهُمُ الْمَلَائِكَةُ طَيِّبِينَ ۙ يَقُولُونَ سَلَامٌ عَلَيْكُمُ ادْخُلُوا الْجَنَّةَ بِمَا كُنْتُمْ تَعْمَلُونَ
እነዚያ ጥሩ ሆነው መላዕክት «ሰላም ለእናንተ ይሁን» እያሉ ነፍሳቸውን የሚወስዷቸው «ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ምክንያትም ወደ ገነት ግቡ።» ይባላሉ።
هَلْ يَنْظُرُونَ إِلَّا أَنْ تَأْتِيَهُمُ الْمَلَائِكَةُ أَوْ يَأْتِيَ أَمْرُ رَبِّكَ ۚ كَذَٰلِكَ فَعَلَ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ ۚ وَمَا ظَلَمَهُمُ اللَّهُ وَلَٰكِنْ كَانُوا أَنْفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ
ከሓዲያን የመላዕክትን ወደ እነርሱ መምጣት ወይም የጌታህ ትዕዛዝ መምጣቱን እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን? ከእነርሱ በፊት የነበሩትም ልክ እንደዚህ ሠርተዋል። አላህም አልበደላቸዉም። ግን እነርሱ ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ።
فَأَصَابَهُمْ سَيِّئَاتُ مَا عَمِلُوا وَحَاقَ بِهِمْ مَا كَانُوا بِهِ يَسْتَهْزِئُونَ
እናም የሠሯቸዉም ኃጢአቶች ቅጣት አገኛቸው። ይሳለቁበት የነበሩት ነገር ሁሉ በእነርሱ ላይ ወረደባቸው።
وَقَالَ الَّذِينَ أَشْرَكُوا لَوْ شَاءَ اللَّهُ مَا عَبَدْنَا مِنْ دُونِهِ مِنْ شَيْءٍ نَحْنُ وَلَا آبَاؤُنَا وَلَا حَرَّمْنَا مِنْ دُونِهِ مِنْ شَيْءٍ ۚ كَذَٰلِكَ فَعَلَ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ ۚ فَهَلْ عَلَى الرُّسُلِ إِلَّا الْبَلَاغُ الْمُبِينُ
እነዚያም ጣዖታትን በአላህ ያጋሩ ህዝቦች «አላህ በሻ ኖሮ ከእርሱ ሌላ እኛም ሆንን አባቶቻችን ምንንም ባልተገዛን ነበር። ያለ እርሱም ትዕዛዝ ምንንም እርም ባላደረግን ነበር።» አሉ። እነዚያም ከእነርሱ በፊት የነበሩት ህዝቦች ልክ እንደዚሁ ሠሩ። በመልዕክተኞቹም ላይ ግልጽ ማድረስ ብቻ እንጂ ሌላ የለባቸዉም።
وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ ۖ فَمِنْهُمْ مَنْ هَدَى اللَّهُ وَمِنْهُمْ مَنْ حَقَّتْ عَلَيْهِ الضَّلَالَةُ ۚ فَسِيرُوا فِي الْأَرْضِ فَانْظُرُوا كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُكَذِّبِينَ
በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣዖትን ራቁ በማለት የሚያስተምር መልዕክተኛን ልከናል። ከእነርሱም ውስጥ አላህ ያቀናው አለ። ከእነርሱም ውስጥ በእርሱ ላይ ጥመት የተረጋገጠበት አለ። እናም በምድር ላይ ሂዱ። የአስተባባዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበር ተመልከቱ።
إِنْ تَحْرِصْ عَلَىٰ هُدَاهُمْ فَإِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي مَنْ يُضِلُّ ۖ وَمَا لَهُمْ مِنْ نَاصِرِينَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመቅናታቸው ላይ ብትጓጓ (ምንም ልታደርግ አትችልም)። ምክንያቱም አላህ የሚያጠመውን አያቀናዉምና። ለእነርሱም ከረዳቶች ምንም የላቸዉም።
وَأَقْسَمُوا بِاللَّهِ جَهْدَ أَيْمَانِهِمْ ۙ لَا يَبْعَثُ اللَّهُ مَنْ يَمُوتُ ۚ بَلَىٰ وَعْدًا عَلَيْهِ حَقًّا وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
ጥብቅ መሐሎቻቸውንም «አላህ የሚሞትን ሰው አያስነሳም።» ሲሉ በአላህ ስም ማሉ። አባባላቸው ሐሰት ነው። ያስነሳቸዋል። በእርሱ ላይ ቃል ኪዳን ገብቷል። አረጋግጧልም። ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም።
لِيُبَيِّنَ لَهُمُ الَّذِي يَخْتَلِفُونَ فِيهِ وَلِيَعْلَمَ الَّذِينَ كَفَرُوا أَنَّهُمْ كَانُوا كَاذِبِينَ
የሚቀሰቅሳቸዉም ለእነርሱ ያንን የሚለያዩበትን ሊገልጽላቸውና እነዚያ የካዱትም እነርሱ ውሸታሞች የነበሩ መሆናቸውን እንዲያውቁ ነው።
إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَيْءٍ إِذَا أَرَدْنَاهُ أَنْ نَقُولَ لَهُ كُنْ فَيَكُونُ
ለማንኛዉም ነገር መሆኑን በፈለግን ጊዜ ቃላችን ለእርሱ "ሁን" ማለት ብቻ ነው። ወዲያዉም ይሆናል።
وَالَّذِينَ هَاجَرُوا فِي اللَّهِ مِنْ بَعْدِ مَا ظُلِمُوا لَنُبَوِّئَنَّهُمْ فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً ۖ وَلَأَجْرُ الْآخِرَةِ أَكْبَرُ ۚ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ
እነዚያም ከተበደሉ በኋላ በአላህ መንገድ ላይ የተሰደዱ በቅርቢቱ ዓለም መልካሚቱን አገር (መዲናን) እናሰፍራቸዋለን። የመጨረሻይቱም ዓለም ምንዳ ታላቅ ነው። (ከሓዲያን) ቢያውቁ ኖሮ (በተከተሏቸው ነበር)።
الَّذِينَ صَبَرُوا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ
እነርሱ እነዚያ የታገሡና በጌታቸዉም ላይ የሚጠጉ ናቸው።
وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ إِلَّا رِجَالًا نُوحِي إِلَيْهِمْ ۚ فَاسْأَلُوا أَهْلَ الذِّكْرِ إِنْ كُنْتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተም በፊት ወደ እነርሱ ወሕይን የምናወርድላቸውን ወንዶችን እንጂ ሌላን አልላክንም። (ሰዎች ሆይ! ) የማታውቁም ከሆናችሁ የዕውቀትን ባለቤቶችን ጠይቁ።
بِالْبَيِّنَاتِ وَالزُّبُرِ ۗ وَأَنْزَلْنَا إِلَيْكَ الذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ
በግልጽ ማስረጃዎችና በመጻሕፍት ላክናቸው። ለሰዎችም ወደ እነርሱ የተወረደላቸውን ፍች ትገልጽላቸውና ያስተነትኑም ዘንድ ወደ አንተ ቁርኣንን አወረድን።
أَفَأَمِنَ الَّذِينَ مَكَرُوا السَّيِّئَاتِ أَنْ يَخْسِفَ اللَّهُ بِهِمُ الْأَرْضَ أَوْ يَأْتِيَهُمُ الْعَذَابُ مِنْ حَيْثُ لَا يَشْعُرُونَ
እነዚያን መጥፎዎችን የዶለቱ ሰዎች አላህ በእነርሱ ምድርን የሚያስዋጣቸው ወይም ከማያውቁት ሥፍራ ቅጣት የሚመጣባቸው መሆኑን ተማመኑን? አይፈሩምን?
أَوْ يَأْخُذَهُمْ فِي تَقَلُّبِهِمْ فَمَا هُمْ بِمُعْجِزِينَ
ወይም ከአገር ወደ አገር በሚዛወሩበት ጊዜ በእንቅስቃሴ ላይ እያሉ የሚይዛቸው መሆኑን አይፈሩምን? እነርሱም አሸናፊዎች አይደሉም።
أَوْ يَأْخُذَهُمْ عَلَىٰ تَخَوُّفٍ فَإِنَّ رَبَّكُمْ لَرَءُوفٌ رَحِيمٌ
ወይም ቀስ በቀስ በማጉደል ላይ የሚይዛቸው መሆኑን ተማመኑን? አይፈሩምን? ጌታችሁ በእርግጥ ሩሕሩህና አዛኝ ነው።
أَوَلَمْ يَرَوْا إِلَىٰ مَا خَلَقَ اللَّهُ مِنْ شَيْءٍ يَتَفَيَّأُ ظِلَالُهُ عَنِ الْيَمِينِ وَالشَّمَائِلِ سُجَّدًا لِلَّهِ وَهُمْ دَاخِرُونَ
ወደዚያ አላህ ከፈጠረው ነገር ሁሉ ጥላዎቹ እነርሱ ተዋራጆች ሲሆኑ ለአላህ ሰጋጆች ሆነው ከቀኝና ከግራዎች የሚዘዋወሩትን አላዩምን?
وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ مِنْ دَابَّةٍ وَالْمَلَائِكَةُ وَهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ
በሰማያትና በምድር ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ መላዕክትም ለአላህ ብቻ ይሰግዳሉ። እነርሱም አይኮሩም።
يَخَافُونَ رَبَّهُمْ مِنْ فَوْقِهِمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ ۩
ጌታቸውን ከበላያቸው ሲሆን ይፈሩታል። የታዘዙትንም ሁሉ ይሰራሉ (ይፈጽማሉ)።
وَقَالَ اللَّهُ لَا تَتَّخِذُوا إِلَٰهَيْنِ اثْنَيْنِ ۖ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَإِيَّايَ فَارْهَبُونِ
አላህም አለ: «ሁለት አማልክት አትያዙ እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው። እኔን ብቻ ፍሩኝ።»
وَلَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلَهُ الدِّينُ وَاصِبًا ۚ أَفَغَيْرَ اللَّهِ تَتَّقُونَ
በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው። አምልኮም ዘወትር ለርሱ ብቻ ነው። ከአላህ ሌላ ያለን ትፈራላችሁን?
وَمَا بِكُمْ مِنْ نِعْمَةٍ فَمِنَ اللَّهِ ۖ ثُمَّ إِذَا مَسَّكُمُ الضُّرُّ فَإِلَيْهِ تَجْأَرُونَ
ማንኛዉም በናንተ ላይ ያለው ጸጋ ከአላህ ብቻ ነው። ከዚያም ችግር በደረሰባችሁ ጊዜ ወደ እርሱ ብቻ ትጮሀላችሁ።
ثُمَّ إِذَا كَشَفَ الضُّرَّ عَنْكُمْ إِذَا فَرِيقٌ مِنْكُمْ بِرَبِّهِمْ يُشْرِكُونَ
ከዚያም ከናንተ ላይ ችግርን ባነሳላችሁ ጊዜ ከናንተ የሆኑ ቡድን ወዲያውኑ በጌታቸው ጣዖትን ያጋራሉ።
لِيَكْفُرُوا بِمَا آتَيْنَاهُمْ ۚ فَتَمَتَّعُوا ۖ فَسَوْفَ تَعْلَمُونَ
የሚያጋሩትም በሰጠናቸው ሊክዱ ነው። ተጠቀሙም ወደፊትም የሚደርስባችሁን ታውቃላችሁ።
وَيَجْعَلُونَ لِمَا لَا يَعْلَمُونَ نَصِيبًا مِمَّا رَزَقْنَاهُمْ ۗ تَاللَّهِ لَتُسْأَلُنَّ عَمَّا كُنْتُمْ تَفْتَرُونَ
ለማያውቁት ጣዖታትም ከሰጠናቸው ሲሳይ ድርሻን ያደርጋሉ። በአላህ እምላለሁ ትቀጣጥፉት ከነበራችሁት ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ።
وَيَجْعَلُونَ لِلَّهِ الْبَنَاتِ سُبْحَانَهُ ۙ وَلَهُمْ مَا يَشْتَهُونَ
ለአላህ ሴቶች ልጆችን ያደርጋሉ። ጥራት ይገባው። ለእነርሱ ግን የሚፈልጉትን ያደርጋሉ።
وَإِذَا بُشِّرَ أَحَدُهُمْ بِالْأُنْثَىٰ ظَلَّ وَجْهُهُ مُسْوَدًّا وَهُوَ كَظِيمٌ
ከመሀከላቸው አንዱ በሴት ልጅ (መወለድ) በተበሰረ ጊዜ እርሱ የተቆጨ ሆኖ ፊቱ ጠቁሮ ቅስሙ ይሰበራል።
يَتَوَارَىٰ مِنَ الْقَوْمِ مِنْ سُوءِ مَا بُشِّرَ بِهِ ۚ أَيُمْسِكُهُ عَلَىٰ هُونٍ أَمْ يَدُسُّهُ فِي التُّرَابِ ۗ أَلَا سَاءَ مَا يَحْكُمُونَ
ከተበሰረበት ነገር መጥፎነት በውርደት ላይ ሆኖም ቢሆን ይያዘውን? ወይስ በአፈር ውስጥ ይደብቀውን? በማለት እያምታታ ከሰዎች ይደበቃል። የሚፈርዱት ፍርድ ምንኛ ከፋ!
لِلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ مَثَلُ السَّوْءِ ۖ وَلِلَّهِ الْمَثَلُ الْأَعْلَىٰ ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
ለእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም ለማያምኑት ሰዎች ሁሉ መጥፎ መገለጫ አላቸው። ለአላህ ግን ከፍተኛው መገለጫ አለው። እርሱም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው።
وَلَوْ يُؤَاخِذُ اللَّهُ النَّاسَ بِظُلْمِهِمْ مَا تَرَكَ عَلَيْهَا مِنْ دَابَّةٍ وَلَٰكِنْ يُؤَخِّرُهُمْ إِلَىٰ أَجَلٍ مُسَمًّى ۖ فَإِذَا جَاءَ أَجَلُهُمْ لَا يَسْتَأْخِرُونَ سَاعَةً ۖ وَلَا يَسْتَقْدِمُونَ
አላህም ሰዎችን በበደላቸው ሁሉ በቀጣቸው ኖሮ በምድር ላይ ከተንቀሳቃሽ ምንንም ባላስቀረ ነበር። ግን እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ያቆያቸዋል። ጊዜያቸዉም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይዘገዩም፤ አይቀድሙም።
وَيَجْعَلُونَ لِلَّهِ مَا يَكْرَهُونَ وَتَصِفُ أَلْسِنَتُهُمُ الْكَذِبَ أَنَّ لَهُمُ الْحُسْنَىٰ ۖ لَا جَرَمَ أَنَّ لَهُمُ النَّارَ وَأَنَّهُمْ مُفْرَطُونَ
ለአላህም የሚጠሉትን ነገር ያደርጋሉ። ለእነርሱም መልካሚቱ (ሀገር) እንዳለቻቸው በምላሶቻቸው ውሸትን ይናገራሉ። ለእነርሱም እሳት ያለቻቸው መሆኑንና እነርሱም ወደ እርሷ በቅድሚያ የሚነዱ መሆናቸው ጥርጥር የለበትም።
تَاللَّهِ لَقَدْ أَرْسَلْنَا إِلَىٰ أُمَمٍ مِنْ قَبْلِكَ فَزَيَّنَ لَهُمُ الشَّيْطَانُ أَعْمَالَهُمْ فَهُوَ وَلِيُّهُمُ الْيَوْمَ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአላህ እንምላለን ካንተ በፊት ወደ ነበሩት ሕዝቦች በእርግጥ ብዙ መልዕክተኞችን ልከናል። ሰይጣንም ለእነርሱ ስራዎቻቸውን ሸለመላቸው። ረዳታቸው ዛሬም እርሱ ነው። ለእነርሱም ኋላ አሳማሚ ቅጣት አላቸው።
وَمَا أَنْزَلْنَا عَلَيْكَ الْكِتَابَ إِلَّا لِتُبَيِّنَ لَهُمُ الَّذِي اخْتَلَفُوا فِيهِ ۙ وَهُدًى وَرَحْمَةً لِقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን በእርሱ የተለያዩበትን ለእነርሱ ልታብራራላቸውና ለሚያምኑትም ህዝቦች መሪና እዝነት ሊሆን እንጂ ባንተ ላይ መፅሀፉን አላወረድንም።
وَاللَّهُ أَنْزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَحْيَا بِهِ الْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَا ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِقَوْمٍ يَسْمَعُونَ
አላህ ከሰማይ ውሃን አወረደ። በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው አደረገ። በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ህዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለ።
وَإِنَّ لَكُمْ فِي الْأَنْعَامِ لَعِبْرَةً ۖ نُسْقِيكُمْ مِمَّا فِي بُطُونِهِ مِنْ بَيْنِ فَرْثٍ وَدَمٍ لَبَنًا خَالِصًا سَائِغًا لِلشَّارِبِينَ
(ሰዎች ሆይ!) ለእናንተ በግመል በከብት በፍየል አፈጣጠር አያሌ ምክር ሰጪ ትምህርት አለላችሁ። በሆዶች ውስጥ ካለው ከፈርስና ከደም መካከል ጥሩ ወተትን ለጠጪዎች ጣፋጭ ሲሆን እናጠጣችኋለን።
وَمِنْ ثَمَرَاتِ النَّخِيلِ وَالْأَعْنَابِ تَتَّخِذُونَ مِنْهُ سَكَرًا وَرِزْقًا حَسَنًا ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِقَوْمٍ يَعْقِلُونَ
ከዘንባባዎች ከወይኖችም ፍሬዎች (እንመግባችኋለን)፤ ከእርሱ ጠጅንና መልካም ምግብንም ትሰራላችሁ (ታዘጋጃላችሁ)። በዚህም ውስጥ ለሚያስቡ ህዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለ።
وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል (አስታወቀ) አስተማረ፡ «ከተራራዎች ከዛፍና ሰዎች ከሚሠሩት ቀፎ ቤቶችን ያዢ።»
ثُمَّ كُلِي مِنْ كُلِّ الثَّمَرَاتِ فَاسْلُكِي سُبُلَ رَبِّكِ ذُلُلًا ۚ يَخْرُجُ مِنْ بُطُونِهَا شَرَابٌ مُخْتَلِفٌ أَلْوَانُهُ فِيهِ شِفَاءٌ لِلنَّاسِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
«ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ ብይ የጌታሽንም መንገዶች ለአንቺ የተገሩ ሲሆኑ ግቢ።» ከሆዶቿ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል። በእርሱ ውስጥ ለሰዎች ፍቱን መድሀኒት አለበት። በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለበት።
وَاللَّهُ خَلَقَكُمْ ثُمَّ يَتَوَفَّاكُمْ ۚ وَمِنْكُمْ مَنْ يُرَدُّ إِلَىٰ أَرْذَلِ الْعُمُرِ لِكَيْ لَا يَعْلَمَ بَعْدَ عِلْمٍ شَيْئًا ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ قَدِيرٌ
አላህም ፈጠራችሁ ከዚያ ይገድላችኋል። ከናንተም መካከል ከእውቀት በኋላ ምንንም ነገር የማያውቅ ወደሚሆንበት የጃጀ እድሜ የሚመለስም ሰው አለ። አላህ ሁሉን አዋቂ፤ በሁሉም ነገር ላይ ቻይም ነው።
وَاللَّهُ فَضَّلَ بَعْضَكُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ فِي الرِّزْقِ ۚ فَمَا الَّذِينَ فُضِّلُوا بِرَادِّي رِزْقِهِمْ عَلَىٰ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَهُمْ فِيهِ سَوَاءٌ ۚ أَفَبِنِعْمَةِ اللَّهِ يَجْحَدُونَ
አላህ ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በሲሳይ አበለጠ። እነዚያም በላጭ የተደረጉት ሲሳያቸውን እጆቻቸው በያዟቸው ባሮች ላይ እነርሱ በእርሱ ይስተካከሉ ዘንድ መላሾች አይደሉም። ታዲያ በአላህ ጸጋ (ለእርሱ ተጋሪ በማድረግ) ይክዳሉን?
وَاللَّهُ جَعَلَ لَكُمْ مِنْ أَنْفُسِكُمْ أَزْوَاجًا وَجَعَلَ لَكُمْ مِنْ أَزْوَاجِكُمْ بَنِينَ وَحَفَدَةً وَرَزَقَكُمْ مِنَ الطَّيِّبَاتِ ۚ أَفَبِالْبَاطِلِ يُؤْمِنُونَ وَبِنِعْمَتِ اللَّهِ هُمْ يَكْفُرُونَ
አላህ ከነፍሶቻችሁ (ከሰው ዘር) ለእናንተ ሚስቶችን አደረገ (የትዳር አጋሮችን ፈጠረ)፤ ለእናንተም ከሚስቶቻችሁ ወንዶች ልጆችን የልጅ ልጆችንም አደረገላችሁ። ከመልካሞችም ጸጋዎች ሰጣችሁ። ታዲያ በውሸት በጣኦት አምነው በአላህ ጸጋ ይክዳሉን?
وَيَعْبُدُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَمْلِكُ لَهُمْ رِزْقًا مِنَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ شَيْئًا وَلَا يَسْتَطِيعُونَ
ከአላህም ሌላ ከሰማያትና ከምድር ምንንም ሲሳይ የማይሰጧቸውንና ምንንም የማይችሉትን እነርሱ ያመልካሉን።
فَلَا تَضْرِبُوا لِلَّهِ الْأَمْثَالَ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ وَأَنْتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
(ሰዎች ሆይ!) ለአላህ አምሳያዎችን አታድርጉ። አላህ ያውቃል፤ እናንተ ግን አታውቁም።
ضَرَبَ اللَّهُ مَثَلًا عَبْدًا مَمْلُوكًا لَا يَقْدِرُ عَلَىٰ شَيْءٍ وَمَنْ رَزَقْنَاهُ مِنَّا رِزْقًا حَسَنًا فَهُوَ يُنْفِقُ مِنْهُ سِرًّا وَجَهْرًا ۖ هَلْ يَسْتَوُونَ ۚ الْحَمْدُ لِلَّهِ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
በምንም ላይ የማይችል ሆኖ በይዞታ (አለቃ ያለበት) የሆነውን ባሪያና መልካም ሲሳይን ሰጥተነው እርሱም ከእርሱ ከሰጠነው በሚስጥርና በግልጽ የሚለግሰውን ነፃ ሰው አላህ (ለጣኦትና ለእርሱ) ምሳሌ አደረገ። ሁለቱ ይስተካከላሉን? ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይሁን። በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም።
وَضَرَبَ اللَّهُ مَثَلًا رَجُلَيْنِ أَحَدُهُمَا أَبْكَمُ لَا يَقْدِرُ عَلَىٰ شَيْءٍ وَهُوَ كَلٌّ عَلَىٰ مَوْلَاهُ أَيْنَمَا يُوَجِّهْهُ لَا يَأْتِ بِخَيْرٍ ۖ هَلْ يَسْتَوِي هُوَ وَمَنْ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ ۙ وَهُوَ عَلَىٰ صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ
አላህ ሁለትን ወንዶች (ለከሓዲያንና ለአማኞች) ምሳሌ አደረገ። አንደኛቸው በምንም ነገር ላይ የማይችል ዲዳ ነው። እርሱም በጌታው ላይ ሸክም ነው። ወደ የትም ቢያዞረው ደግ ነገር አያመጣም። እርሱና ያ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ሆኖ በማስተካከል (ፍትህ) የሚያዘው ሰው ይስተካከላሉን?
وَلِلَّهِ غَيْبُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَمَا أَمْرُ السَّاعَةِ إِلَّا كَلَمْحِ الْبَصَرِ أَوْ هُوَ أَقْرَبُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
በሰማያትና በምድር ያለው ሩቅ ምስጢር የአላህ ብቻ ነው። የሰዓቲቱም ነገር መምጣቷ እንደ ዓይን ቅጽበት እንጂ አይደለም። ወይም ይበልጥ የቀረበ ነው። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።
وَاللَّهُ أَخْرَجَكُمْ مِنْ بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ لَا تَعْلَمُونَ شَيْئًا وَجَعَلَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ ۙ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
አላህ ከእናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ። ታመሰግኑ ዘንድም ለእናንተ መስሚያንና ማያዎችን ልቦችንም አደረገላችሁ (ፈጠረላችሁ)።
أَلَمْ يَرَوْا إِلَى الطَّيْرِ مُسَخَّرَاتٍ فِي جَوِّ السَّمَاءِ مَا يُمْسِكُهُنَّ إِلَّا اللَّهُ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ
ወደ በራሪዎችም በሰማይ አየር ውስጥ ለመብረር የተገሩ ሲሆኑ ከመውደቅ አላህ እንጂ ሌላ የማይዛቸው መሆናቸውን አይመለከቱምን? በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተዓምራት አሉ።
وَاللَّهُ جَعَلَ لَكُمْ مِنْ بُيُوتِكُمْ سَكَنًا وَجَعَلَ لَكُمْ مِنْ جُلُودِ الْأَنْعَامِ بُيُوتًا تَسْتَخِفُّونَهَا يَوْمَ ظَعْنِكُمْ وَيَوْمَ إِقَامَتِكُمْ ۙ وَمِنْ أَصْوَافِهَا وَأَوْبَارِهَا وَأَشْعَارِهَا أَثَاثًا وَمَتَاعًا إِلَىٰ حِينٍ
አላህም ከቤቶቻችሁ ለእናንተ መርጊያን (ማረፊያን) አደረገላችሁ (ፈጠረላችሁ)። ከእንስሳዎችም ቆዳዎች በጉዟችሁ ቀንም ሆነ በመቀመጫችሁ ቀን የምታቀሏቸውን ቤቶች (ዳሶች) ለእናንተ ፈጠረላችሁ። ከበጓ ሱፎች፣ ከግመሏም ጠጉሮች፣ ከፍየሏም ጠጉሮች የቤት እቃዎችን እስከ ጊዜም ድረስ መጠቃቀሚያን አደረገላችሁ።
وَاللَّهُ جَعَلَ لَكُمْ مِمَّا خَلَقَ ظِلَالًا وَجَعَلَ لَكُمْ مِنَ الْجِبَالِ أَكْنَانًا وَجَعَلَ لَكُمْ سَرَابِيلَ تَقِيكُمُ الْحَرَّ وَسَرَابِيلَ تَقِيكُمْ بَأْسَكُمْ ۚ كَذَٰلِكَ يُتِمُّ نِعْمَتَهُ عَلَيْكُمْ لَعَلَّكُمْ تُسْلِمُونَ
አላህ ከፈጠረው ነገር ለእናንተ ጥላዎችን ፈጠረላችሁ። ከጋራዎችም መከለያዎችን ፈጠረላችሁ። ሐሩርንም (ብርድንም) የሚጠብቋችሁን ልብሶች፤ የጦራችሁንም አደጋ የሚጠብቋችሁን ጥሩሮች ፈጠረላችሁ። ልክ እንደዚሁ ትሰልሙ ዘንድ ጸጋውን በእናንተ ላይ ይሞላል።
فَإِنْ تَوَلَّوْا فَإِنَّمَا عَلَيْكَ الْبَلَاغُ الْمُبِينُ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከኢስላም ቢሸሹም ባንተ ላይ ያለብህ ግልጽ ማድረስ ብቻ ነው።
يَعْرِفُونَ نِعْمَتَ اللَّهِ ثُمَّ يُنْكِرُونَهَا وَأَكْثَرُهُمُ الْكَافِرُونَ
የአላህን ጸጋ ያውቃሉ። ሆኖም ከዚያ ይክዷታል። አብዛኞቻቸዉም ከሓዲያን ናቸው።
وَيَوْمَ نَبْعَثُ مِنْ كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا ثُمَّ لَا يُؤْذَنُ لِلَّذِينَ كَفَرُوا وَلَا هُمْ يُسْتَعْتَبُونَ
ከየህዝቡም ሁሉ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን ቀን አስታውስ። ከዚያ ለእነዚያ ለካዱት ንግግር አይፈቀድላቸዉም። እነርሱም በወቀሳ አይታለፉም።
وَإِذَا رَأَى الَّذِينَ ظَلَمُوا الْعَذَابَ فَلَا يُخَفَّفُ عَنْهُمْ وَلَا هُمْ يُنْظَرُونَ
እነዚያ የበደሉ ሰዎች ቅጣትን ባዩ ጊዜ ለእነርሱ አይቃለልላቸዉም። ጊዜም አይሰጣቸዉም።
وَإِذَا رَأَى الَّذِينَ أَشْرَكُوا شُرَكَاءَهُمْ قَالُوا رَبَّنَا هَٰؤُلَاءِ شُرَكَاؤُنَا الَّذِينَ كُنَّا نَدْعُو مِنْ دُونِكَ ۖ فَأَلْقَوْا إِلَيْهِمُ الْقَوْلَ إِنَّكُمْ لَكَاذِبُونَ
እነዚያ በአላህ ያጋሩት ሰዎች ተጋሪዎቻቸውን ባዩ ጊዜ «ጌታችን ሆይ! እነዚህ ካንተ ሌላ እናመልካቸው የነበሩ ተጋሪዎቻችን ናቸው።» ይላሉ። አማልክቶችም «ውሸታሞች ናችሁ።» በማለት ቃሉን ወደ እነርሱው መልሰው ይወረውራሉ።
وَأَلْقَوْا إِلَى اللَّهِ يَوْمَئِذٍ السَّلَمَ ۖ وَضَلَّ عَنْهُمْ مَا كَانُوا يَفْتَرُونَ
አጋሪዎቹ በዚያ ቀንም ታዛዥነታቸውን ወደ አላህ ያቀርባሉ። ይቀጣጥፉት የነበሩትም ሁሉ ከእነርሱ ይጠፋባቸዋል።
الَّذِينَ كَفَرُوا وَصَدُّوا عَنْ سَبِيلِ اللَّهِ زِدْنَاهُمْ عَذَابًا فَوْقَ الْعَذَابِ بِمَا كَانُوا يُفْسِدُونَ
እነዚያ በአላህ የካዱና ከአላህ መንገድ የከለከሉ ያጠፉ በነበሩት ምክንያት ቅጣትን በቅጣት ላይ ጨመርንባቸው።
وَيَوْمَ نَبْعَثُ فِي كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا عَلَيْهِمْ مِنْ أَنْفُسِهِمْ ۖ وَجِئْنَا بِكَ شَهِيدًا عَلَىٰ هَٰؤُلَاءِ ۚ وَنَزَّلْنَا عَلَيْكَ الْكِتَابَ تِبْيَانًا لِكُلِّ شَيْءٍ وَهُدًى وَرَحْمَةً وَبُشْرَىٰ لِلْمُسْلِمِينَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በየህዝቡ ሁሉ ውስጥ ከጎሳቸው በራሳቸው ላይ መስካሪን የምንቀሰቅስበትንና አንተንም በእነዚህ ሕዝቦች ላይ መስካሪ አድርገን የምናመጣህን ቀን አስታውስ። መጽሐፉንም ለሁሉም ነገር አብራሪ፤ መመሪያ፣ እዝነትና ለሙስሊሞች አብሳሪ ሆኖ ባንተ ላይ አወረድነው።
إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالْإِحْسَانِ وَإِيتَاءِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَيَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنْكَرِ وَالْبَغْيِ ۚ يَعِظُكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
አላህ በማስተካከል (በፍትህ) ፤ በማሳመር (በመልካም ሥራ) እና ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል። ከአስከፊ (ጸያፍ ነገር እንደ ማመንዘር)፤ ከሚጠላ ነገር ሁሉ ከመበደልም ይከለክላል። ትገነዘቡ ዘንድ ይገሥጻችኋል።
وَأَوْفُوا بِعَهْدِ اللَّهِ إِذَا عَاهَدْتُمْ وَلَا تَنْقُضُوا الْأَيْمَانَ بَعْدَ تَوْكِيدِهَا وَقَدْ جَعَلْتُمُ اللَّهَ عَلَيْكُمْ كَفِيلًا ۚ إِنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا تَفْعَلُونَ
(ሙስሊሞች ሆይ!) ቃል ኪዳን በገባችሁ ጊዜ በአላህ ቃል ኪዳን ሙሉ። መሓሎቻችሁንም ከአጠነከራችኋት በኋላና አላህን በእናንተ ላይ መስካሪ ያደረጋችሁ ስትሆኑ አታፍርሱ። አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃልና።
وَلَا تَكُونُوا كَالَّتِي نَقَضَتْ غَزْلَهَا مِنْ بَعْدِ قُوَّةٍ أَنْكَاثًا تَتَّخِذُونَ أَيْمَانَكُمْ دَخَلًا بَيْنَكُمْ أَنْ تَكُونَ أُمَّةٌ هِيَ أَرْبَىٰ مِنْ أُمَّةٍ ۚ إِنَّمَا يَبْلُوكُمُ اللَّهُ بِهِ ۚ وَلَيُبَيِّنَنَّ لَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ مَا كُنْتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ
ቃል ኪዳናችሁን በማፍረስ አንዲቱ ሕዝብ ከሌላይቱ ሕዝብ የበዛች ለመሆንዋ በመካከላችሁ መሓሎቻችሁን ለክዳት መግቢያ አድርጋችሁ የምትይዙ ስትሆኑ እንደዚያች ፈትሏን ከጠነከረ በኋላ ትርትሮች አድርጋ እንዳፈረሰችው ሴት አትሁኑ። አላህ በእርሱ ይሞክራችኋል፤ በትንሣኤ ቀንም ትለያዩበት የነበራችሁትን ነገር በእርግጥ ያብራራላችኋል።
وَلَوْ شَاءَ اللَّهُ لَجَعَلَكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً وَلَٰكِنْ يُضِلُّ مَنْ يَشَاءُ وَيَهْدِي مَنْ يَشَاءُ ۚ وَلَتُسْأَلُنَّ عَمَّا كُنْتُمْ تَعْمَلُونَ
አላህ በፈለገ ኖሮ አንዲት ሕዝብ ባደረጋችሁ ነበር። ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያጠማል። የሚሻውን ሰው ያቀናል። ትሠሩት ከነበራችሁት ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ።
وَلَا تَتَّخِذُوا أَيْمَانَكُمْ دَخَلًا بَيْنَكُمْ فَتَزِلَّ قَدَمٌ بَعْدَ ثُبُوتِهَا وَتَذُوقُوا السُّوءَ بِمَا صَدَدْتُمْ عَنْ سَبِيلِ اللَّهِ ۖ وَلَكُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ
ጫማዎች ከተደላደሉ በኋላ እንዳያንዳልጡ ከአላህ መንገድ በመከልከላችሁ ምክንያት ቅጣትንም እንዳትቀምሱ መሓሎቻችሁን በመካከላችሁ ለክዳት መግቢያ አታድርጉት። ለእናንተም ያን ጊዜ ታላቅ ቅጣት አላችሁ።
وَلَا تَشْتَرُوا بِعَهْدِ اللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۚ إِنَّمَا عِنْدَ اللَّهِ هُوَ خَيْرٌ لَكُمْ إِنْ كُنْتُمْ تَعْلَمُونَ
በአላህ ቃል ኪዳን ጥቂትን ዋጋ አትግዙ። የምታውቁ ብትሆኑ አላህ ዘንድ ያለው ምንዳ እርሱ ለእናንተ በላጭ ነውና።
مَا عِنْدَكُمْ يَنْفَدُ ۖ وَمَا عِنْدَ اللَّهِ بَاقٍ ۗ وَلَنَجْزِيَنَّ الَّذِينَ صَبَرُوا أَجْرَهُمْ بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
እናንተ ዘንድ ያለው ሁሉ ያልቃል። አላህ ዘንድ ያለው ግን ለዘለዓለም ቀሪ ነው (አያልቅም)። እነዚያንም የታገሡትን ይሠሩት በነበሩት በመልካሙ ምንዳቸውን በእርግጥ እንመነዳቸዋለን።
مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِنْ ذَكَرٍ أَوْ أُنْثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً ۖ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُمْ بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
ከወንድም ይሁን ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን የሠራ ሁሉ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን። ይሠሩት ከነበሩት ነገር በመልካሙም ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን።
فَإِذَا قَرَأْتَ الْقُرْآنَ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ
ቁርኣንንም ለማንበብ ባሰብክ ጊዜ እርጉም ከሆነው ሰይጣን በአላህ ተጠበቅ።
إِنَّهُ لَيْسَ لَهُ سُلْطَانٌ عَلَى الَّذِينَ آمَنُوا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ
እርሱ በእነዚያ በትክክል ባመኑትና በጌታቸው ላይ በሚጠጉት ላይ ለእርሱ ሥልጣን የለዉምና።
إِنَّمَا سُلْطَانُهُ عَلَى الَّذِينَ يَتَوَلَّوْنَهُ وَالَّذِينَ هُمْ بِهِ مُشْرِكُونَ
ሥልጣኑ በእነዚያ እርሱን (ሰይጣንን) በሚታዘዙት ላይና በእነዚያም እነርሱ በእርሱ ምክንያት አጋሪዎች በሆኑት ላይ ብቻ ነው።
وَإِذَا بَدَّلْنَا آيَةً مَكَانَ آيَةٍ ۙ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يُنَزِّلُ قَالُوا إِنَّمَا أَنْتَ مُفْتَرٍ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአንቀጽም ስፍራ ሌላ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ነገር አዋቂ ነው። «አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም።» ይላሉ። በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም።
قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِنْ رَبِّكَ بِالْحَقِّ لِيُثَبِّتَ الَّذِينَ آمَنُوا وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُسْلِمِينَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ያመኑትን ሰዎች ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር ቁርኣንን ጂብሪል እውነተኛ ሲሆን ከጌታህ አወረደው።» በላቸው።
وَلَقَدْ نَعْلَمُ أَنَّهُمْ يَقُولُونَ إِنَّمَا يُعَلِّمُهُ بَشَرٌ ۗ لِسَانُ الَّذِي يُلْحِدُونَ إِلَيْهِ أَعْجَمِيٌّ وَهَٰذَا لِسَانٌ عَرَبِيٌّ مُبِينٌ
እነርሱም «እርሱን ቁርኣንን የሚያስተምረው ሰው ብቻ ነው።» ማለታቸውን በእርግጥ እናውቃለን። የዚያ ወደ እርሱ የሚያስጠጉበት ሰው ቋንቋ ዐረበኛ ያልሆነ ዐጀምኛ ነው። ይህ ቁርኣን ግን በግልጽ በዐረብኛ ቋንቋ የተነገረ ነው።
إِنَّ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ لَا يَهْدِيهِمُ اللَّهُ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
እነዚያን በአላህ አናቅጽ የማያምኑትን አላህ አይመራቸዉም። ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።
إِنَّمَا يَفْتَرِي الْكَذِبَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ۖ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْكَاذِبُونَ
ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አናቅጽ የማያምኑት ብቻ ናቸው። እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው።
مَنْ كَفَرَ بِاللَّهِ مِنْ بَعْدِ إِيمَانِهِ إِلَّا مَنْ أُكْرِهَ وَقَلْبُهُ مُطْمَئِنٌّ بِالْإِيمَانِ وَلَٰكِنْ مَنْ شَرَحَ بِالْكُفْرِ صَدْرًا فَعَلَيْهِمْ غَضَبٌ مِنَ اللَّهِ وَلَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ
ከእምነቱ በኋላ በአላህ የካደ ሰው (ብርቱ ቅጣት አለው)። ልቡ በእምነት የረካ ሆኖ በክሕደት ቃል ለመናገር የተገደደ ሰው ብቻ ሲቀር። ግን ልባቸውን በክሕደት የከፈቱ ሰዎች ከአላህ ቁጣ አለባቸው። ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው።
ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمُ اسْتَحَبُّوا الْحَيَاةَ الدُّنْيَا عَلَى الْآخِرَةِ وَأَنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْكَافِرِينَ
ይህ ቅጣት እነርሱ ቅርቢቱን ሕይወት ከመጨረሻይቱ በመምረጣቸው ምክንያትና አላህም ከሓዲያንን ሕዝቦች የማያቀና በመሆኑ ነው።
أُولَٰئِكَ الَّذِينَ طَبَعَ اللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ وَسَمْعِهِمْ وَأَبْصَارِهِمْ ۖ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْغَافِلُونَ
እነዚያ እነርሱ በልቦቻቸው፤ በዓይኖቻቸውና በጆሮቻቸዉም ላይ አላህ ያተመባቸው ናቸው። እነዚያም ዝንጉዎቹ እነርሱ ብቻ ናቸው።
لَا جَرَمَ أَنَّهُمْ فِي الْآخِرَةِ هُمُ الْخَاسِرُونَ
እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ከሳሪዎቹ እነርሱ ለመሆናቸው ጥርጥር የለም።
ثُمَّ إِنَّ رَبَّكَ لِلَّذِينَ هَاجَرُوا مِنْ بَعْدِ مَا فُتِنُوا ثُمَّ جَاهَدُوا وَصَبَرُوا إِنَّ رَبَّكَ مِنْ بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَحِيمٌ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያም ጌታህ ለእነዚያ ከተፈተኑ በኋላ ለተሰደዱት ከዚያም ለታገሉትና ለታገሡት ሁሉ ጌታህም ከፈተናዋ በኋላ በእርግጥ መሐሪና አዛኝ ነው።
يَوْمَ تَأْتِي كُلُّ نَفْسٍ تُجَادِلُ عَنْ نَفْسِهَا وَتُوَفَّىٰ كُلُّ نَفْسٍ مَا عَمِلَتْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነፍስ ሁሉ ከራሷ ላይ የምትከራከር ሆና የምትመጣበትን ነፍስም ሁሉ የሠራችውን ዋጋ የምትቀበልበትን ቀን (አስታውስ)። እነርሱም ፈጽሞ አይበደሉም።
وَضَرَبَ اللَّهُ مَثَلًا قَرْيَةً كَانَتْ آمِنَةً مُطْمَئِنَّةً يَأْتِيهَا رِزْقُهَا رَغَدًا مِنْ كُلِّ مَكَانٍ فَكَفَرَتْ بِأَنْعُمِ اللَّهِ فَأَذَاقَهَا اللَّهُ لِبَاسَ الْجُوعِ وَالْخَوْفِ بِمَا كَانُوا يَصْنَعُونَ
አላህ ጸጥተኛ የረካች ሲሳይዋ ሰፊ ሆኖ ከየስፍራው ይመጣላት የነበረችውንና ከዚያም በአላህ ጸጋዎች የካደችውን አላህም ይሠሩት በነበሩት ኃጢአት የረሀብንና የፍርሀትን ቅጣቶች ያቀመሳትን ከተማ ምሳሌ አደረገ።
وَلَقَدْ جَاءَهُمْ رَسُولٌ مِنْهُمْ فَكَذَّبُوهُ فَأَخَذَهُمُ الْعَذَابُ وَهُمْ ظَالِمُونَ
ከእነርሱም ውስጥ የሆነ መልዕክተኛም በእርግጥ መጣላቸው። አስተባበሉትም እነርሱም በዳዮች ሆነው ቅጣቱ ያዛቸው።
فَكُلُوا مِمَّا رَزَقَكُمُ اللَّهُ حَلَالًا طَيِّبًا وَاشْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ إِنْ كُنْتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ
አላህም ከሰጣችሁ ሲሳይ የተፈቀደና ንጹሕ ሲሆን ብሉ። እርሱን ብቻ የምትገዙ ከሆናችሁ የአላህንም ጸጋ አመስግኑት።
إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ الْمَيْتَةَ وَالدَّمَ وَلَحْمَ الْخِنْزِيرِ وَمَا أُهِلَّ لِغَيْرِ اللَّهِ بِهِ ۖ فَمَنِ اضْطُرَّ غَيْرَ بَاغٍ وَلَا عَادٍ فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَحِيمٌ
በእናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትን፣ ደምን፣ የአሳማን ሥጋ፣ ያንንም በሚታረድ ጊዜ በእርሱ ላይ ከአላህ ስም ሌላ የተወሳበትን ብቻ ነው። አመጸኛና ወሰን አላፊም ሳይሆን ከእነዚህ አንዱን ለመብላት የተገደደ ሰው ይፈቀድለታል። አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና።
وَلَا تَقُولُوا لِمَا تَصِفُ أَلْسِنَتُكُمُ الْكَذِبَ هَٰذَا حَلَالٌ وَهَٰذَا حَرَامٌ لِتَفْتَرُوا عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ ۚ إِنَّ الَّذِينَ يَفْتَرُونَ عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ لَا يُفْلِحُونَ
(ሰዎች ሆይ) በአላህ ላይ ውሸትን ልትቀጣጥፉ ምላሶቻችሁ በሚመጥኑት ውሸት «ይህ የተፈቀደ ነው፤ ይህ ደግሞ እርም ነው» አትበሉ። እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ ክፍሎች በፍጹም አይድኑም።
مَتَاعٌ قَلِيلٌ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
ጥቂት መጠቀም ብቻ አለላቸው። ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።
وَعَلَى الَّذِينَ هَادُوا حَرَّمْنَا مَا قَصَصْنَا عَلَيْكَ مِنْ قَبْلُ ۖ وَمَا ظَلَمْنَاهُمْ وَلَٰكِنْ كَانُوا أَنْفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነዚያ አይሁድ በሆኑት ሰዎች ላይ ከአሁን በፊት ባንተ ላይ የተረክነውን ነገር እርም አድርገንባቸዋል። እኛም አልበደልናቸዉም። ግን ራሳቸው ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበሩ።
ثُمَّ إِنَّ رَبَّكَ لِلَّذِينَ عَمِلُوا السُّوءَ بِجَهَالَةٍ ثُمَّ تَابُوا مِنْ بَعْدِ ذَٰلِكَ وَأَصْلَحُوا إِنَّ رَبَّكَ مِنْ بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَحِيمٌ
ከዚያም ጌታህ ለእነዚያ በስህተት መጥፎን ለሠሩትና ከዚያም ከዚህ በኋላ ለተጸጸቱ ሥራቸውንም ላበጁ ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪና አዛኝ ነው።
إِنَّ إِبْرَاهِيمَ كَانَ أُمَّةً قَانِتًا لِلَّهِ حَنِيفًا وَلَمْ يَكُ مِنَ الْمُشْرِكِينَ
ኢብራሂም ለአላህ ታዛዥ፤ ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ተዘንባይ (በበጎ ነገር አርአያ የሆነ) መሪ ነበር። ከአጋሪዎችም አልነበረም።
شَاكِرًا لِأَنْعُمِهِ ۚ اجْتَبَاهُ وَهَدَاهُ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ
ለጸጋዎቹ አመስጋኝ ነበር። መረጠው። ወደ ቀጥተኛዉም መንገድ መራው።
وَآتَيْنَاهُ فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً ۖ وَإِنَّهُ فِي الْآخِرَةِ لَمِنَ الصَّالِحِينَ
በቅርቢቱም ዓለም በጎ ነገርን ሰጠነው። እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም በእርግጥ ከመልካሞቹ ነው።
ثُمَّ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ أَنِ اتَّبِعْ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۖ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዚያም «ቀጥተኛ የሆነውን የኢብራሂምን ሃይማኖት ተከተል» ማለትን ወደ አንተ አወረድን። ከአጋሪዎቹም አልነበረም።
إِنَّمَا جُعِلَ السَّبْتُ عَلَى الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ ۚ وَإِنَّ رَبَّكَ لَيَحْكُمُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فِيمَا كَانُوا فِيهِ يَخْتَلِفُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በቅዳሜ ቀን መስራት ክልክል የተደረገው በእነዚያ በእርሱ በተለያዩበት ሰዎች ላይ ብቻ ነው። ጌታህም በትንሳኤ ቀን ይለያዩበት በነበሩት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ ይፈርዳል።
ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ ۖ وَجَادِلْهُمْ بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَنْ ضَلَّ عَنْ سَبِيلِهِ ۖ وَهُوَ أَعْلَمُ بِالْمُهْتَدِينَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብተኛ ቃልም) ሰዎችን ጥራ። በዚያችም እርሷ መልካም በሆነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው። ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን ሰው በጣም አዋቂ ነው። እንደዚሁም እርሱ ቅን የሆኑትን ሰዎች በጣምች አዋቂ ነው።
وَإِنْ عَاقَبْتُمْ فَعَاقِبُوا بِمِثْلِ مَا عُوقِبْتُمْ بِهِ ۖ وَلَئِنْ صَبَرْتُمْ لَهُوَ خَيْرٌ لِلصَّابِرِينَ
(ሙስሊሞች ሆይ!) ብትበቀሉም በእርሱ በተቀጣችሁበት ብጤ ተበቀሉ። ብትታገሱ ግን እርሱ ለታጋሾች በእርግጥ በላጭ ነው።
وَاصْبِرْ وَمَا صَبْرُكَ إِلَّا بِاللَّهِ ۚ وَلَا تَحْزَنْ عَلَيْهِمْ وَلَا تَكُ فِي ضَيْقٍ مِمَّا يَمْكُرُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ታገስ። መታገስህ በአላህ ማስቻል እንጂ አይደለም። በእነርሱም ላይ ባያምኑ አትተክዝ። ባንተ ላይ በሚመክሩት ተንኮልም በጭንቀት ውስጥ አትሁን።
إِنَّ اللَّهَ مَعَ الَّذِينَ اتَّقَوْا وَالَّذِينَ هُمْ مُحْسِنُونَ
አላህ ከእነዚያ እነርሱ ከሚፈሩትና ከእነዚያም እነርሱ መልካም ሠሪ ከሆኑት ሰዎች ጋር ነው።