Mary · Maryam · سورة مريم · 98 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

كهيعص

ካፍ፤ ሃ፤ ያ፤ ዐይን፤ ሷድ፤

ذِكْرُ رَحْمَتِ رَبِّكَ عَبْدَهُ زَكَرِيَّا

ይህ ጌታህ ባርያውን ዘከሪያን በችሮታው ያወሳበት ነው።

إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ نِدَاءً خَفِيًّا

ጌታውን የሚስጢርን ጥሪ በተጣራ ጊዜ የሆነውን አስታውስ።

قَالَ رَبِّ إِنِّي وَهَنَ الْعَظْمُ مِنِّي وَاشْتَعَلَ الرَّأْسُ شَيْبًا وَلَمْ أَكُنْ بِدُعَائِكَ رَبِّ شَقِيًّا

(እንዲህም) አለ: «ጌታዬ ሆይ! እኔ አጥንቴም ደከመ። ራሴም በሽበት ተንቀለቀለ። ጌታዬ ሆይ! አንተንም በመለመኔ፤ ምንጊዜም ዕድለ ቢስ አልሆንኩም።

وَإِنِّي خِفْتُ الْمَوَالِيَ مِنْ وَرَائِي وَكَانَتِ امْرَأَتِي عَاقِرًا فَهَبْ لِي مِنْ لَدُنْكَ وَلِيًّا

«እኔም ከበኋላዬ (ከሞትኩ በኋላ) ዘመዶቼን (ከእምነት እንዳይወጡ) ፈራሁ። ሚስቴም መካን ነበረች። ስለዚህ ካንተ ዘንድ ለእኔ ልጅን ስጠኝ።

يَرِثُنِي وَيَرِثُ مِنْ آلِ يَعْقُوبَ ۖ وَاجْعَلْهُ رَبِّ رَضِيًّا

«የሚወርሰኝ ከየዕቁብ ቤተሰቦችም የእምነትን ሃላፊነት የሚወርስን ልጅ ስጠኝ። ጌታዬ ሆይ! ተወዳጅም አድርገው።» አለ።

يَا زَكَرِيَّا إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَامٍ اسْمُهُ يَحْيَىٰ لَمْ نَجْعَلْ لَهُ مِنْ قَبْلُ سَمِيًّا

«ዘከሪያ ሆይ! እኛ ስሙ የሕያ በሆነና ከዚያ በፊት ሞክሼን ባላደረግንለት ወንድ ልጅ እናበስርሃለን።» አለው።

قَالَ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي غُلَامٌ وَكَانَتِ امْرَأَتِي عَاقِرًا وَقَدْ بَلَغْتُ مِنَ الْكِبَرِ عِتِيًّا

«ጌታዬ ሆይ! ሚስቴ መካን እኔም ከእርጅና የተነሳ ድርቀትን የደረስኩ ስሆን እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለ።

قَالَ كَذَٰلِكَ قَالَ رَبُّكَ هُوَ عَلَيَّ هَيِّنٌ وَقَدْ خَلَقْتُكَ مِنْ قَبْلُ وَلَمْ تَكُ شَيْئًا

(ጅብሪልም) አለ: «ነገሩ ልክ እንደዚሁ ነው። ጌታህ ‹ከዚህ በፊት ምንም ያልነበርከውን የፈጠርኩህ ስሆን እርሱ በእኔ ላይ ቀላል ነው።› ብሏል።»

قَالَ رَبِّ اجْعَلْ لِي آيَةً ۚ قَالَ آيَتُكَ أَلَّا تُكَلِّمَ النَّاسَ ثَلَاثَ لَيَالٍ سَوِيًّا

እርሱም «ጌታዬ ሆይ! እንግዲያውስ ምልክት አድርግልኝ።» አለ። «ምልክትህ (ጤናማ ሆነህ ሳለህ) ሶስት ሌሊት ከነቀናቸው ሰዎችን ማነጋገር አለመቻልህ ነው።» አለው።

فَخَرَجَ عَلَىٰ قَوْمِهِ مِنَ الْمِحْرَابِ فَأَوْحَىٰ إِلَيْهِمْ أَنْ سَبِّحُوا بُكْرَةً وَعَشِيًّا

እርሱም ከምኩራቡ ወደ ህዝቦቹ ወጣ። ጧትና ማታ ጌታችሁን አውሱ አጥሩትም በማለትም ወደ እነርሱ ጠቀሰ።

يَا يَحْيَىٰ خُذِ الْكِتَابَ بِقُوَّةٍ ۖ وَآتَيْنَاهُ الْحُكْمَ صَبِيًّا

«የሕያ ሆይ! መጽሐፉን በጥብቅ ያዝ።» አልነው። ጥበብንም በሕጻንነቱ ሰጠነው።

وَحَنَانًا مِنْ لَدُنَّا وَزَكَاةً ۖ وَكَانَ تَقِيًّا

ከእኛም የሆነን ርህራሄና ንጽህናንም (ሰጠነው)። ጥንቁቅም ነበር።

وَبَرًّا بِوَالِدَيْهِ وَلَمْ يَكُنْ جَبَّارًا عَصِيًّا

ለወላጆቹም በጎ ሠሪ ነበር። ትዕቢተኛና አመጸኛም አልነበረም።

وَسَلَامٌ عَلَيْهِ يَوْمَ وُلِدَ وَيَوْمَ يَمُوتُ وَيَوْمَ يُبْعَثُ حَيًّا

በተወለደበት ቀንና በሚሞትበት ቀን ህያው ሆኖ በሚነሳበትም ቀን ሰላም በእሱ ላይ ይሁን ።

وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ مَرْيَمَ إِذِ انْتَبَذَتْ مِنْ أَهْلِهَا مَكَانًا شَرْقِيًّا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መርየም ከቤተሰቧ ወደ ምስራቃዊ ስፍራ በተለየች ጊዜ የሆነውን ታሪኳን በመጽሐፉ ውስጥ አውሳ።

فَاتَّخَذَتْ مِنْ دُونِهِمْ حِجَابًا فَأَرْسَلْنَا إِلَيْهَا رُوحَنَا فَتَمَثَّلَ لَهَا بَشَرًا سَوِيًّا

ከእነርሱም መጋረጃን አደረገች። መንፈሳችንንም (መልዐኩ ጂብሪልን) ወደ እርሷ ላክን። ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት።

قَالَتْ إِنِّي أَعُوذُ بِالرَّحْمَٰنِ مِنْكَ إِنْ كُنْتَ تَقِيًّا

«ካንተ በአር-ረህማን እጠበቃለሁ። ጌታህን ፈሪ ከሆንክ (አትቅረበኝ)።» አለች።

قَالَ إِنَّمَا أَنَا رَسُولُ رَبِّكِ لِأَهَبَ لَكِ غُلَامًا زَكِيًّا

«እኔ ንጹሕ የሆነን ልጅ ላንቺ ልሰጥ የመጣሁ የጌታሽ መልዕክተኛ ነኝ።» አላት።

قَالَتْ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي غُلَامٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ وَلَمْ أَكُ بَغِيًّا

«በጋብቻ አንድም ሰው ያልነካኝ ሆኜ አመንዝራ ዝሙተኛ ሳልሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል!» አለች።

قَالَ كَذَٰلِكِ قَالَ رَبُّكِ هُوَ عَلَيَّ هَيِّنٌ ۖ وَلِنَجْعَلَهُ آيَةً لِلنَّاسِ وَرَحْمَةً مِنَّا ۚ وَكَانَ أَمْرًا مَقْضِيًّا

(መልአኩም) «ነገሩ ልክ እንደዚሁ ነው የሚፈጸመው። ጌታሽ ‹እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው። ለሰዎችም ተዓምር ከእኛም ችሮታ ልናደርገው ይህንን ሰራን፤ ነገሩ የተወሰነም ነው።› ብሏል።» አለ።

فَحَمَلَتْهُ فَانْتَبَذَتْ بِهِ مَكَانًا قَصِيًّا

ወዲያውኑም አረገዘችው። እርሱንም በሆድዋ ይዛው ወደ ሩቅ ስፍራ ገለል አለች።

فَأَجَاءَهَا الْمَخَاضُ إِلَىٰ جِذْعِ النَّخْلَةِ قَالَتْ يَا لَيْتَنِي مِتُّ قَبْلَ هَٰذَا وَكُنْتُ نَسْيًا مَنْسِيًّا

ምጡ ወደ ዘንባባይቱ ግንድ አስጠጋት። እርሷም «ወይኔ! ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩና የተረሳሁ በሆንኩ።» አለች።

فَنَادَاهَا مِنْ تَحْتِهَا أَلَّا تَحْزَنِي قَدْ جَعَلَ رَبُّكِ تَحْتَكِ سَرِيًّا

ከበታቿም እንዲህ ሲል ጠራት: «አትዘኝ። ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓልና።

وَهُزِّي إِلَيْكِ بِجِذْعِ النَّخْلَةِ تُسَاقِطْ عَلَيْكِ رُطَبًا جَنِيًّا

«የዘምባባይቱን ግንድ ወደ አንቺ ወዝውዢው። በአንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ያረግፍልሻልና።

فَكُلِي وَاشْرَبِي وَقَرِّي عَيْنًا ۖ فَإِمَّا تَرَيِنَّ مِنَ الْبَشَرِ أَحَدًا فَقُولِي إِنِّي نَذَرْتُ لِلرَّحْمَٰنِ صَوْمًا فَلَنْ أُكَلِّمَ الْيَوْمَ إِنْسِيًّا

«ብይ፤ ጠጭም። ተደሰቺም ከሰዎች አንድንም ብታይ እኔ ለአዛኙ አምላክ ዝምታን ተስያለሁ። እናም ዛሬ ማንንም ሰው በፍጹም አላነጋግርም በይ።» አላት።

فَأَتَتْ بِهِ قَوْمَهَا تَحْمِلُهُ ۖ قَالُوا يَا مَرْيَمُ لَقَدْ جِئْتِ شَيْئًا فَرِيًّا

እርሱን ተሸክማው ወደ ዘመዶቿ መጣች (እንዲህም) አሏት: «መርየም ሆይ! ከባድ ነገርን በእርግጥ ፈጸምሽ።

يَا أُخْتَ هَارُونَ مَا كَانَ أَبُوكِ امْرَأَ سَوْءٍ وَمَا كَانَتْ أُمُّكِ بَغِيًّا

«አንቺ የሃሩን እህት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም። እናትሽም አመንዝራ ዝሙተኛ አልነበረችም።» አሏት።

فَأَشَارَتْ إِلَيْهِ ۖ قَالُوا كَيْفَ نُكَلِّمُ مَنْ كَانَ فِي الْمَهْدِ صَبِيًّا

እርሷም ወደ ህፃኑ አመለከተች። እነርሱም «በአንቀልባ ያለን ህፃን እንዴት እናናግራለን?» አሉ።

قَالَ إِنِّي عَبْدُ اللَّهِ آتَانِيَ الْكِتَابَ وَجَعَلَنِي نَبِيًّا

ህፃኑም አለ: «እኔ የአላህ አገልጋይ ነኝ፤ መጽሐፍን ሰጥቶኛል። ነብይም አድርጎኛል።

وَجَعَلَنِي مُبَارَكًا أَيْنَ مَا كُنْتُ وَأَوْصَانِي بِالصَّلَاةِ وَالزَّكَاةِ مَا دُمْتُ حَيًّا

«በየትም ስፍራ ብሆን የተባረኩኝ አድርጎኛል። በህይወትም እስካለሁ ሶላትንና ዘካን አዞኛል።

وَبَرًّا بِوَالِدَتِي وَلَمْ يَجْعَلْنِي جَبَّارًا شَقِيًّا

«ለእናቴም ታዛዥ አድርጎኛል። ትዕቢተኛ እድለቢስ አላደረገኝም።

وَالسَّلَامُ عَلَيَّ يَوْمَ وُلِدْتُ وَيَوْمَ أَمُوتُ وَيَوْمَ أُبْعَثُ حَيًّا

«በተወለድሁበት ቀን በምሞትበት ቀንና ሕያው ሆኜ በምቀሰቀስበትም ቀን ሰላም በእኔ ላይ ይስፈን።» አለ።

ذَٰلِكَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ الْحَقِّ الَّذِي فِيهِ يَمْتَرُونَ

የመርየም ልጅ ዒሳ ይሀው ነው፤ ያ በእርሱ የሚጠራጠሩበት እውነተኛ ቃል ይህ ነው።

مَا كَانَ لِلَّهِ أَنْ يَتَّخِذَ مِنْ وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُنْ فَيَكُونُ

ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባዉም። ከጉድለት ሁሉ ጠራ። አንድን ነገር በወሰነ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ሁን» ብቻ ነው። ወዲያዉም ይሆናል።

وَإِنَّ اللَّهَ رَبِّي وَرَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۚ هَٰذَا صِرَاطٌ مُسْتَقِيمٌ

(ዒሳ ለህዝቦቹ) «አላህ የእኔም ጌታዬ የእናንተም ጌታችሁ ነውና ተገዙት። ይህ ቀጥተኛው መንገድ ነው።» አለ።

فَاخْتَلَفَ الْأَحْزَابُ مِنْ بَيْنِهِمْ ۖ فَوَيْلٌ لِلَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ مَشْهَدِ يَوْمٍ عَظِيمٍ

ከመካከላቸዉም አንጃዎች በእርሱ ነገር ላይ ተለያዩ። ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከታላቁ ቀን መጋፈጥ ክስተት ወዮላቸው።

أَسْمِعْ بِهِمْ وَأَبْصِرْ يَوْمَ يَأْتُونَنَا ۖ لَٰكِنِ الظَّالِمُونَ الْيَوْمَ فِي ضَلَالٍ مُبِينٍ

ወደ እኛ በሚመጡ ቀን ምን ያህል ሰሚ ምን ያህል ተመልካች አደረጋቸው። ግን አመጸኞች በዳዮች ዛሬ በዚህች ዓለም በግልጽ ስህተትና ጥመት ውስጥ ናቸው።

وَأَنْذِرْهُمْ يَوْمَ الْحَسْرَةِ إِذْ قُضِيَ الْأَمْرُ وَهُمْ فِي غَفْلَةٍ وَهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሚፈረድበት ጊዜ የቁጭትን ቀን አስፈራራቸው እነርሱ አሁን በመዘንጋት ላይ ናቸው። እነርሱ አያምኑምና።

إِنَّا نَحْنُ نَرِثُ الْأَرْضَ وَمَنْ عَلَيْهَا وَإِلَيْنَا يُرْجَعُونَ

ምድርንና በእርሷም ላይ ያለውን ፍጡር ሁሉ እኛ እንወርሳለን። ወደ እኛም ይመለሳሉ።

وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِبْرَاهِيمَ ۚ إِنَّهُ كَانَ صِدِّيقًا نَبِيًّا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመጽሐፉ ውስጥ ኢብራሂምን አውሳ። እርሱም በጣም እውነተኛ ነብይ ነበርና።

إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ لِمَ تَعْبُدُ مَا لَا يَسْمَعُ وَلَا يُبْصِرُ وَلَا يُغْنِي عَنْكَ شَيْئًا

ለአባቱ (እንዲህ) ባለው ጊዜ የሆነውን አስታውስ: «አባቴ ሆይ! የማይሰማንና የማያይን ላንተም ምንንም የማይጠቅምህን (የማይፈይድህን) ጣዖት ለምን ታመልካለህን?

يَا أَبَتِ إِنِّي قَدْ جَاءَنِي مِنَ الْعِلْمِ مَا لَمْ يَأْتِكَ فَاتَّبِعْنِي أَهْدِكَ صِرَاطًا سَوِيًّا

«አባቴ ሆይ! እኔ አንተ ያልደረሰህን እውቀት መጥቶልኛልና ተከተለኝ። ቀጥተኛውን መንገድ እመራሃለሁና።

يَا أَبَتِ لَا تَعْبُدِ الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّ الشَّيْطَانَ كَانَ لِلرَّحْمَٰنِ عَصِيًّا

«አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አትገዛ (አታምልክ)። ሰይጣን ለአር-ረህማን አመጸኛ ነውና።

يَا أَبَتِ إِنِّي أَخَافُ أَنْ يَمَسَّكَ عَذَابٌ مِنَ الرَّحْمَٰنِ فَتَكُونَ لِلشَّيْطَانِ وَلِيًّا

«አባቴ ሆይ! እኔ የአር-ረህማን ቅጣት ሊያገኝህ እና ከዚያ የሰይጣን ጓደኛ ልትሆን እፈራለሁ።»

قَالَ أَرَاغِبٌ أَنْتَ عَنْ آلِهَتِي يَا إِبْرَاهِيمُ ۖ لَئِنْ لَمْ تَنْتَهِ لَأَرْجُمَنَّكَ ۖ وَاهْجُرْنِي مَلِيًّا

አባቱም «ኢብራሂም ሆይ! አንተ አምላኮቼን ትተህ የምትዞር ነህን? ከዚህ ተግባርህ ባትከለከል በእርግጥ እወግርሃለሁ። ረዥም ጊዜንም ተወኝ።» አለ።

قَالَ سَلَامٌ عَلَيْكَ ۖ سَأَسْتَغْفِرُ لَكَ رَبِّي ۖ إِنَّهُ كَانَ بِي حَفِيًّا

ኢብራሂምም አለ: «ደህና ሁን (ሰላም ላንተ ይሁን)። ከጌታዬ ምህረትን እለምንልሃለሁ። እርሱ ለእኔ በጣም ሩህሩህ ነውና።

وَأَعْتَزِلُكُمْ وَمَا تَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ وَأَدْعُو رَبِّي عَسَىٰ أَلَّا أَكُونَ بِدُعَاءِ رَبِّي شَقِيًّا

«እናንተንና ከአላህ ሌላ የምትገዙትን ሁሉ እርቃለሁ። ጌታዬንም ብቻ እገዛለሁ፤ ጌታዬን በመገዛት ዕድለ ቢስ አለመሆኔን እከጅላለሁ (ተስፋ አደርጋለሁ)።» አለ።

فَلَمَّا اعْتَزَلَهُمْ وَمَا يَعْبُدُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ وَهَبْنَا لَهُ إِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ ۖ وَكُلًّا جَعَلْنَا نَبِيًّا

እነርሱንና ከአላህ ሌላ የሚገዙትን በራቀ ጊዜ ኢስሐቅንና የዕቁብን ሰጠነው። ሁለቱንም ነብይ አደረግናቸው።

وَوَهَبْنَا لَهُمْ مِنْ رَحْمَتِنَا وَجَعَلْنَا لَهُمْ لِسَانَ صِدْقٍ عَلِيًّا

ለእነርሱም ከችሮታችን ሰጠናቸው። ለእነርሱም ከፍ ያለ ምስጉን ዝናን አደረግንላቸው።

وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ مُوسَىٰ ۚ إِنَّهُ كَانَ مُخْلَصًا وَكَانَ رَسُولًا نَبِيًّا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመጽሐፉ ውስጥ ሙሳን አውሳ። እርሱ ምርጥ ነበርና። መልዕክተኛ ነብይም ነበርና።

وَنَادَيْنَاهُ مِنْ جَانِبِ الطُّورِ الْأَيْمَنِ وَقَرَّبْنَاهُ نَجِيًّا

ከጡር ጋራ በስተቀኝ ጎን በኩልም ጠራነው። በሚስጥር ያነጋገርነውም ስንሆን አቀረብነው።

وَوَهَبْنَا لَهُ مِنْ رَحْمَتِنَا أَخَاهُ هَارُونَ نَبِيًّا

ከእዝነታችንም (ከችሮታችንም) ወንድሙን ሃሩንን ነብይ አደረግንለት።

وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِسْمَاعِيلَ ۚ إِنَّهُ كَانَ صَادِقَ الْوَعْدِ وَكَانَ رَسُولًا نَبِيًّا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመጽሐፉ ውስጥ ኢስማዒልንም አውሳ። እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበርና። መልዕክተኛ ነብይም ነበር።

وَكَانَ يَأْمُرُ أَهْلَهُ بِالصَّلَاةِ وَالزَّكَاةِ وَكَانَ عِنْدَ رَبِّهِ مَرْضِيًّا

ቤተሰቦቹንም በሶላትና በዘካ ያዝ ነበር። በጌታዉም ዘንድ ተወዳጅ ነበር።

وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِدْرِيسَ ۚ إِنَّهُ كَانَ صِدِّيقًا نَبِيًّا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመጽሐፉ ውስጥ ኢድሪስንም አውሳ። እርሱ እውነተኛ ነብይ ነበርና።

وَرَفَعْنَاهُ مَكَانًا عَلِيًّا

(ኢድሪስን) ወደ ከፍተኛም ስፍራ አነሳነው።

أُولَٰئِكَ الَّذِينَ أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيْهِمْ مِنَ النَّبِيِّينَ مِنْ ذُرِّيَّةِ آدَمَ وَمِمَّنْ حَمَلْنَا مَعَ نُوحٍ وَمِنْ ذُرِّيَّةِ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْرَائِيلَ وَمِمَّنْ هَدَيْنَا وَاجْتَبَيْنَا ۚ إِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُ الرَّحْمَٰنِ خَرُّوا سُجَّدًا وَبُكِيًّا ۩

እነዚህ (አሥሩ) እነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ችሮታውን የለገሰላቸው ከነብያት ከአዳም ዘር ከኑሕ ጋር በመርከቢቱ ላይ ከጫንናቸዉም ዘሮች ከኢብራሂምና ከኢስራኢልም ዘሮች ከመራናቸውና ከመረጥናቸዉም የሆኑት የአር-ረህማን አናቅጽ በእነርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ ሰጋጆችና አልቃሾች ሆነው ወደ መሬት የሚወድቁ (የሚደፉ) ናቸው።

فَخَلَفَ مِنْ بَعْدِهِمْ خَلْفٌ أَضَاعُوا الصَّلَاةَ وَاتَّبَعُوا الشَّهَوَاتِ ۖ فَسَوْفَ يَلْقَوْنَ غَيًّا

ከእነርሱም በኋላ ሶላትን ያጎደሉ ከንቱ ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ትውልዶች ተተኩ። ክስረትን (ቅጣትን፤ ይህም በገሀነም ውስጥ «ገይ» የሚባል ሸለቆ ነው ተብሏል) በእርግጥ ያገኛሉ።

إِلَّا مَنْ تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ صَالِحًا فَأُولَٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ وَلَا يُظْلَمُونَ شَيْئًا

ግና ከእነርሱ የተጸጸቱ በአላህ ያመኑ በጎንም ስራ የሰሩ ሰዎች ወደ ገነት ይገባሉ። አንዳችንም አይበደሉም።

جَنَّاتِ عَدْنٍ الَّتِي وَعَدَ الرَّحْمَٰنُ عِبَادَهُ بِالْغَيْبِ ۚ إِنَّهُ كَانَ وَعْدُهُ مَأْتِيًّا

የመኖሪያን ገነቶች ያችን አር-ረህማን ለባሮቹ በሩቅ ሆነው ሳሉ ተስፋ ቃል የገባላቸውን ይገባሉ። እርሱ ተስፋው ሁልጊዜም ተፈጻሚ ነውና።

لَا يَسْمَعُونَ فِيهَا لَغْوًا إِلَّا سَلَامًا ۖ وَلَهُمْ رِزْقُهُمْ فِيهَا بُكْرَةً وَعَشِيًّا

በእርሷ ሰላምን እንጂ ውድቅን ነገር አይሰሙም። ለእነርሱም በእርሷ ውስጥ ጧትም ማታም ሲሳያቸው አላቸው።

تِلْكَ الْجَنَّةُ الَّتِي نُورِثُ مِنْ عِبَادِنَا مَنْ كَانَ تَقِيًّا

ይህ ያቺ ከባሮቻችን ጥንቁቆች ለሆኑት ሁሉ የምናወርሳት ገነት ናት።

وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلَّا بِأَمْرِ رَبِّكَ ۖ لَهُ مَا بَيْنَ أَيْدِينَا وَمَا خَلْفَنَا وَمَا بَيْنَ ذَٰلِكَ ۚ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيًّا

(ጂብሪልም ለነቢዩ) «በጌታህ ትእዛዝ እንጂ አንወርድም። በፊታችን፤ በኋላችንና በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው። ጌታህም ረሺ አይደለም።» አለ።

رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا فَاعْبُدْهُ وَاصْطَبِرْ لِعِبَادَتِهِ ۚ هَلْ تَعْلَمُ لَهُ سَمِيًّا

እርሱ የሰማያትና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና ተገዛው። እርሱን በመገዛትም ላይ ታገሥ። ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን?

وَيَقُولُ الْإِنْسَانُ أَإِذَا مَا مِتُّ لَسَوْفَ أُخْرَجُ حَيًّا

ሰው «በሞትኩ ጊዜ ወደ ፊት ህያው ሆኜ ከመቃብር እወጣለሁን?» ይላል።

أَوَلَا يَذْكُرُ الْإِنْسَانُ أَنَّا خَلَقْنَاهُ مِنْ قَبْلُ وَلَمْ يَكُ شَيْئًا

ሰው ከዚህ በፊት ምንም ነገር ያልነበረ ሲሆን የፈጠርነው መሆኑን አያስታውስምን?

فَوَرَبِّكَ لَنَحْشُرَنَّهُمْ وَالشَّيَاطِينَ ثُمَّ لَنُحْضِرَنَّهُمْ حَوْلَ جَهَنَّمَ جِثِيًّا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጌታህ እንምላለን ከሰይጣናት ጋር በእርግጥ እንሰበስባቸዋለን። ከዚያም በገሀነም ዙሪያ የተንበረከኩ ሆነው እናቀርባቸዋለን።

ثُمَّ لَنَنْزِعَنَّ مِنْ كُلِّ شِيعَةٍ أَيُّهُمْ أَشَدُّ عَلَى الرَّحْمَٰنِ عِتِيًّا

ከዚያም ከየቡድኖቹ ሁሉ ከእነርሱ ያንን በአር-ረህማን ላይ በድፍረት በጣም ብርቱ የሆነውን መዝዘን እናወጣለን።

ثُمَّ لَنَحْنُ أَعْلَمُ بِالَّذِينَ هُمْ أَوْلَىٰ بِهَا صِلِيًّا

ከዚያም እነዚያን በእርሷ ለመቃጠል ይበልጥ ተገቢ የሆኑትን ሰዎች እኛ በእርግጥ አዋቂዎች ነን።

وَإِنْ مِنْكُمْ إِلَّا وَارِدُهَا ۚ كَانَ عَلَىٰ رَبِّكَ حَتْمًا مَقْضِيًّا

(ሰዎች ሆይ!) ከናንተ መካከል ወደ ገሀነም የማይወርድ አንድም የለም። መውረዱም ጌታህ የፈረደው ግዴታና አይቀሬ ዉሳኔ ነው።

ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوْا وَنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا

ከዚያም እነዚያን አላህን የፈሩትን ብቻ እናድናለን። አመጸኞችን ደግሞ የተንበረከኩ ሆነው በውስጧ እንተዋቸዋለን።

وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ قَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِلَّذِينَ آمَنُوا أَيُّ الْفَرِيقَيْنِ خَيْرٌ مَقَامًا وَأَحْسَنُ نَدِيًّا

በእነርሱም ላይ አናቅጻችን ግልጽ ማስረጃዎች ሆነው በተነበቡላቸው ጊዜ እነዚያ የካዱት ለእነዚያ ላመኑት «ከሁለቱ ክፍሎች መኖሪያው የበለጠውና ሸንጎዉም ይበልጥ የሚያምረው ማንኛው ነው?» ይላሉ።

وَكَمْ أَهْلَكْنَا قَبْلَهُمْ مِنْ قَرْنٍ هُمْ أَحْسَنُ أَثَاثًا وَرِئْيًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች እነርሱ በቁሳቁስና በእይታ በጣም ያማሩትን ብዙዎችን አጥፍተናል።

قُلْ مَنْ كَانَ فِي الضَّلَالَةِ فَلْيَمْدُدْ لَهُ الرَّحْمَٰنُ مَدًّا ۚ حَتَّىٰ إِذَا رَأَوْا مَا يُوعَدُونَ إِمَّا الْعَذَابَ وَإِمَّا السَّاعَةَ فَسَيَعْلَمُونَ مَنْ هُوَ شَرٌّ مَكَانًا وَأَضْعَفُ جُنْدًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በስህተት ውስጥ የሆነውን አዛኙ አምላክ ለእርሱ ጥመትን ይጨምርለት (ማዘግየትን ያዘግየው።) የሚዛትባቸውንም ቅጣትን ወይም ሰዓቲቱን ባዩ ጊዜ እርሱ ስፍራው መጥፎና ሰራዊቱ ደካማ ማን እንደሆነ በእርግጥ ያውቃሉ።» በላቸው።

وَيَزِيدُ اللَّهُ الَّذِينَ اهْتَدَوْا هُدًى ۗ وَالْبَاقِيَاتُ الصَّالِحَاتُ خَيْرٌ عِنْدَ رَبِّكَ ثَوَابًا وَخَيْرٌ مَرَدًّا

እነዚያንም የቀኑትን ሰዎች አላህ ቅንነትን ይጨምርላቸዋል። መልካም ቀሪ ስራዎች በጌታህ ዘንድ በምንዳ በላጭ ናቸው። በመመለሻነትም የተሻሉ ናቸው።

أَفَرَأَيْتَ الَّذِي كَفَرَ بِآيَاتِنَا وَقَالَ لَأُوتَيَنَّ مَالًا وَوَلَدًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን በአናቅጻችን የካደውንና «(በትንሣኤ ቀን) ገንዘብም ሆነ ልጅ በእርግጥ እሰጣለሁ» ያለውን አየህን?

أَطَّلَعَ الْغَيْبَ أَمِ اتَّخَذَ عِنْدَ الرَّحْمَٰنِ عَهْدًا

ሩቁን ምስጢር አወቀን ? ወይስ አዛኙ አምላክ ዘንድ ቃል ኪዳንን ያዘ?

كَلَّا ۚ سَنَكْتُبُ مَا يَقُولُ وَنَمُدُّ لَهُ مِنَ الْعَذَابِ مَدًّا

ከዚህ አቋሙ ይታቀብ። አይሰጠዉም። የሚለውን ሁሉ በእርግጥ እንጽፋለን። ለእርሱም ከቅጣት ጭማሬን እንጨምርለታለን።

وَنَرِثُهُ مَا يَقُولُ وَيَأْتِينَا فَرْدًا

አለኝ የሚለውንም ሁሉ እንወርሰዋለን ወደ እኛም ብቻውን ሆኖ ይመጣል።

وَاتَّخَذُوا مِنْ دُونِ اللَّهِ آلِهَةً لِيَكُونُوا لَهُمْ عِزًّا

ከአላህ ሌላ አማልክትን ለእነርሱ መከበሪያ አማላጅ እንዲሆኗቸው ያዙ።

كَلَّا ۚ سَيَكْفُرُونَ بِعِبَادَتِهِمْ وَيَكُونُونَ عَلَيْهِمْ ضِدًّا

ከዚህ ተግባራቸው ይከልከሉ (ይታቀቡ)። መገዛታቸውን በእርግጥ ወደፊት ይከዷቸዋል። በእነርሱም ላይ ተቃራኒ (ባላጋራ) ይሆኑባቸዋል።

أَلَمْ تَرَ أَنَّا أَرْسَلْنَا الشَّيَاطِينَ عَلَى الْكَافِرِينَ تَؤُزُّهُمْ أَزًّا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰይጣናትን በከሓዲያን ላይ በመጥፎ ሥራ የሚገፋፏቸው ሲሆኑ የላክንባቸው መሆናችንን አላየህምን።

فَلَا تَعْجَلْ عَلَيْهِمْ ۖ إِنَّمَا نَعُدُّ لَهُمْ عَدًّا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱም መቀጣት ላይ አትቸኩል። ለእነርሱ ቀንን እንቆጥርላቸዋለንና።

يَوْمَ نَحْشُرُ الْمُتَّقِينَ إِلَى الرَّحْمَٰنِ وَفْدًا

ትክክለኛ አማኞችን የተከበሩ ቡድኖች ሆነው ወደ አዛኙ አምላክ የምንሰበስብበትንና:

وَنَسُوقُ الْمُجْرِمِينَ إِلَىٰ جَهَنَّمَ وِرْدًا

ከሓዲያንን የተጠሙ ሆነው ወደገሀነም የምንነዳበትን ቀን አስታውስ።

لَا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِنْدَ الرَّحْمَٰنِ عَهْدًا

አዛኙ አምላክ ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ቢሆን እንጂ ሌሎች ማማለድን አይችሉም።

وَقَالُوا اتَّخَذَ الرَّحْمَٰنُ وَلَدًا

(ከሓዲያን) «አዛኙ አምላክ ልጅን ያዘ።» አሉ።

لَقَدْ جِئْتُمْ شَيْئًا إِدًّا

(አጋሪዎች ሆይ!) እጅግ ከባድና መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ።

تَكَادُ السَّمَاوَاتُ يَتَفَطَّرْنَ مِنْهُ وَتَنْشَقُّ الْأَرْضُ وَتَخِرُّ الْجِبَالُ هَدًّا

ከዚህ ንግግራቸው ሰማያት ሊቀደዱ፤ ምድርም ልትሰነጠቅ፤ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ።

أَنْ دَعَوْا لِلرَّحْمَٰنِ وَلَدًا

ይህም ለአዛኙ አምላክ ልጅ አለው ስላሉ ነው።

وَمَا يَنْبَغِي لِلرَّحْمَٰنِ أَنْ يَتَّخِذَ وَلَدًا

አዛኙ ጌታ ልጅን መያዝ አይገባዉም።

إِنْ كُلُّ مَنْ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ إِلَّا آتِي الرَّحْمَٰنِ عَبْدًا

በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ በትንሣኤ ቀን ለአዛኙ ጌታ (ለአር-ረህማን) ባሪያ ሆነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም።

لَقَدْ أَحْصَاهُمْ وَعَدَّهُمْ عَدًّا

አላህ በእርግጥ በዕውቀቱ ከቧቸዋል። መቁጠርንም ቆጥሯቸዋል።

وَكُلُّهُمْ آتِيهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فَرْدًا

ሁሉም በትንሳኤ ቀን ለየብቻ ሆነው ወደ እርሱ መጪዎች ናቸው።

إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ سَيَجْعَلُ لَهُمُ الرَّحْمَٰنُ وُدًّا

እነዚያ በአላህ ያመኑና በጎ ስራዎችን የሰሩ ሁሉ አር-ረህማን ለእነርሱ ውዴታን ይሰጣቸዋል።

فَإِنَّمَا يَسَّرْنَاهُ بِلِسَانِكَ لِتُبَشِّرَ بِهِ الْمُتَّقِينَ وَتُنْذِرَ بِهِ قَوْمًا لُدًّا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በምላስህም ቁርኣንን ያገራነው በእርሱ ጥንቁቆችን ልታበስርበትና በእርሱ ተከራካሪ ሕዝቦችን ልታስፈራራበት ዘንድ ነው።

وَكَمْ أَهْلَكْنَا قَبْلَهُمْ مِنْ قَرْنٍ هَلْ تُحِسُّ مِنْهُمْ مِنْ أَحَدٍ أَوْ تَسْمَعُ لَهُمْ رِكْزًا

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች ብዙ ትውልዶችን አጥፍተናል። ከእነርሱ አንድን እንኳ ታያለህን? ወይንስ ለእነርሱ ሹክሹክታን ትሰማለህን? (አታይም፣ አትሰማምም)።