يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمْ ۚ إِنَّ زَلْزَلَةَ السَّاعَةِ شَيْءٌ عَظِيمٌ
እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን (አላህን) ፍሩ። የሰዓቲቱ እንቅጥቃጤ በጣም ከባድ ነገር ነውና።
القرآن الكريمAfrica Academy
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።
يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمْ ۚ إِنَّ زَلْزَلَةَ السَّاعَةِ شَيْءٌ عَظِيمٌ
እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን (አላህን) ፍሩ። የሰዓቲቱ እንቅጥቃጤ በጣም ከባድ ነገር ነውና።
يَوْمَ تَرَوْنَهَا تَذْهَلُ كُلُّ مُرْضِعَةٍ عَمَّا أَرْضَعَتْ وَتَضَعُ كُلُّ ذَاتِ حَمْلٍ حَمْلَهَا وَتَرَى النَّاسَ سُكَارَىٰ وَمَا هُمْ بِسُكَارَىٰ وَلَٰكِنَّ عَذَابَ اللَّهِ شَدِيدٌ
በምታዩዋት ቀን ሁኔታው አጥቢ ሁሉ ያጠባችውን ልጅ ትዘነጋዋለች። እርጉዝ ሴት ሁሉ እርጉዝዋን ትጨነግፋለች። ሰዎቹንም በድንጋጤ ብርታት የሰከሩ መስለው ታያቸዋለህ። እነርሱ ከመጠጥ የሰከሩ ሆነው ሳይሆን ግን የአላህ ቅጣት ብርቱ ስለሆነ ነው።
وَمِنَ النَّاسِ مَنْ يُجَادِلُ فِي اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّبِعُ كُلَّ شَيْطَانٍ مَرِيدٍ
ከሰዎች መካከል ያለ ምንም ዕውቀት በአላህ ነገር የሚከራከር፤ ሞገደኛ ሰይጣንንም የሚከተል ሰው አለ።
كُتِبَ عَلَيْهِ أَنَّهُ مَنْ تَوَلَّاهُ فَأَنَّهُ يُضِلُّهُ وَيَهْدِيهِ إِلَىٰ عَذَابِ السَّعِيرِ
እነሆ የተከተለውን ሰው እርሱ ያጠመዋል። ወደ አቃጣይ እሳት ስቃይም ይመራዋል ማለት በእርሱ ላይ ተጽፏል። (ተወስኖበታል)
يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنْ كُنْتُمْ فِي رَيْبٍ مِنَ الْبَعْثِ فَإِنَّا خَلَقْنَاكُمْ مِنْ تُرَابٍ ثُمَّ مِنْ نُطْفَةٍ ثُمَّ مِنْ عَلَقَةٍ ثُمَّ مِنْ مُضْغَةٍ مُخَلَّقَةٍ وَغَيْرِ مُخَلَّقَةٍ لِنُبَيِّنَ لَكُمْ ۚ وَنُقِرُّ فِي الْأَرْحَامِ مَا نَشَاءُ إِلَىٰ أَجَلٍ مُسَمًّى ثُمَّ نُخْرِجُكُمْ طِفْلًا ثُمَّ لِتَبْلُغُوا أَشُدَّكُمْ ۖ وَمِنْكُمْ مَنْ يُتَوَفَّىٰ وَمِنْكُمْ مَنْ يُرَدُّ إِلَىٰ أَرْذَلِ الْعُمُرِ لِكَيْلَا يَعْلَمَ مِنْ بَعْدِ عِلْمٍ شَيْئًا ۚ وَتَرَى الْأَرْضَ هَامِدَةً فَإِذَا أَنْزَلْنَا عَلَيْهَا الْمَاءَ اهْتَزَّتْ وَرَبَتْ وَأَنْبَتَتْ مِنْ كُلِّ زَوْجٍ بَهِيجٍ
ሰዎች ሆይ! ከሞት በኋላ ከመቀስቀስ በመጠራጠር ጉዳይ እንደ ሆናችሁ የመጀመሪያውን (አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ። እኛም) ከአፈር ፈጠርናችሁ። ከዚያ ከፍትወት ጠብታ፤ ከዚያም ከረጋ ደም፤ ከዚያም ከቁራጭ ስጋ ፍጥረትዋ ሙሉ ከሆነችና ሙሉ ካልሆነች (ችሎታችንን) ለእናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ። የምንሻውንም እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ በማህጸን ውስጥ እናረጋዋለን። ከዚያም ህፃን ሆናችሁ እናወጣችኋለን። ከዚያም ሙሉ ጥንካሬያችሁን ትደርሱ ዘንድ (እናሳድጋችኋለን)። ከናንተም መካከል በወጣትነቱ የሚሞት ሰው አለ። ከናንተም መካከል ከዕውቀት በኋላ ምንንም ላያውቅ ወደ ጃጀ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አለ። ምድርንም ደረቅ ሆና ታያታለህ። በእርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ ትላወሳለች (ትነቃነቃለች)። ትነፋለችም። ውበት ካለው የእጽዋት አይነት ሁሉ ታበቅላለችም።
ذَٰلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّهُ يُحْيِي الْمَوْتَىٰ وَأَنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
ይህ ሁሉ አላህ ፍፁም እውነት፤ እርሱም ሙታንን ህያው የሚያደርግ፤ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ በመሆኑ ነው።
وَأَنَّ السَّاعَةَ آتِيَةٌ لَا رَيْبَ فِيهَا وَأَنَّ اللَّهَ يَبْعَثُ مَنْ فِي الْقُبُورِ
የሰዓቲቱም መከሰት ፈጽሞ ጥርጣሬ የሌለበት በመሆኑና አላህ በመቃብሮች ውስጥ ያለን ሁሉ የሚቀሰቅስ በመሆኑም ነው።
وَمِنَ النَّاسِ مَنْ يُجَادِلُ فِي اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَلَا هُدًى وَلَا كِتَابٍ مُنِيرٍ
ከሰዎች መካከል ያለ ምንም ዕውቀት ያለ አንዳች ማስረጃም ያለ አብራሪ መጽሐፍም (ከአላህ መንገድ ሊያሳስት) በአላህ ነገር የሚከራከር (ሰው) አለ።
ثَانِيَ عِطْفِهِ لِيُضِلَّ عَنْ سَبِيلِ اللَّهِ ۖ لَهُ فِي الدُّنْيَا خِزْيٌ ۖ وَنُذِيقُهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ عَذَابَ الْحَرِيقِ
ጎኑን ያጠፈ ሆኖ ከአላህ መንገድ ሊያሳስት (ይከራከራል)። በቅርቢቱ ዓለም ለርሱ ውርደት አለው። በትንሳኤ ቀንም አቃጣይን (የእሳት) ቅጣት እናቀምሰዋለን።
ذَٰلِكَ بِمَا قَدَّمَتْ يَدَاكَ وَأَنَّ اللَّهَ لَيْسَ بِظَلَّامٍ لِلْعَبِيدِ
«ይህ እጆችህ ባስቀደሙት ኃጢአት ነው፣ አላህም ለባሮቹ ፈጽሞ በዳይ አይደለም።» (ይባላል።)
وَمِنَ النَّاسِ مَنْ يَعْبُدُ اللَّهَ عَلَىٰ حَرْفٍ ۖ فَإِنْ أَصَابَهُ خَيْرٌ اطْمَأَنَّ بِهِ ۖ وَإِنْ أَصَابَتْهُ فِتْنَةٌ انْقَلَبَ عَلَىٰ وَجْهِهِ خَسِرَ الدُّنْيَا وَالْآخِرَةَ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْخُسْرَانُ الْمُبِينُ
ከሰዎችም መካከል በሃይማኖት ጫፍ ላይ ሆኖ አላህን የሚገዛ ሰው አለ። እናም መልካም ነገር ካገኘው በእምነቱ ላይ ይረጋል። መከራ ካገኘው ግን በፊቱ ላይ ይገለበጣል (ይክዳል)። ይህ አይነቱ ሰው የቅርቢቱን ዓለምም ሆነ የመጨረሻይቱን ዓለም ከሰረ። ይህ ነው ግልጽ ኪሳራ ማለት።
يَدْعُو مِنْ دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُ وَمَا لَا يَنْفَعُهُ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الضَّلَالُ الْبَعِيدُ
ከአላህ ሌላ የማይጎዳውንና የማይጠቅመውን ይገዛል። ይህ እርሱ ከእውነት የራቀ ስህተት ነው።
يَدْعُو لَمَنْ ضَرُّهُ أَقْرَبُ مِنْ نَفْعِهِ ۚ لَبِئْسَ الْمَوْلَىٰ وَلَبِئْسَ الْعَشِيرُ
ያንን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ወደ እሱ የሚቀርብን ይገዛል። ረዳቱ ምንኛ ከፋ! ወዳጁም ምንኛ ከፋ!
إِنَّ اللَّهَ يُدْخِلُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَفْعَلُ مَا يُرِيدُ
አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትንና መልካም ስራዎችን የሰሩትን ሰዎች በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያስገባቸዋል። አላህም የሚሻውን ነገር ሁሉ በእርግጥ ይሰራልና።
مَنْ كَانَ يَظُنُّ أَنْ لَنْ يَنْصُرَهُ اللَّهُ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ فَلْيَمْدُدْ بِسَبَبٍ إِلَى السَّمَاءِ ثُمَّ لْيَقْطَعْ فَلْيَنْظُرْ هَلْ يُذْهِبَنَّ كَيْدُهُ مَا يَغِيظُ
አላህ (መልዕክተኛውን) ሙሐመድን በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም አይረዳዉም ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ ገመድን ወደ ሰማይ ይዘርጋና ከዚያ (ትንፋሹ እስኪቆረጥ) ይታነቅ። ይህ ተግባሩ ተንኮሉ የሚያስቆጨውን ነገር ያስወግደለት እንደሆነም ይመልከት።
وَكَذَٰلِكَ أَنْزَلْنَاهُ آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ وَأَنَّ اللَّهَ يَهْدِي مَنْ يُرِيدُ
ልክ እንደዚሁ (ቁርኣንን) የተብራሩ አናቅጽ አድርገን አወረድነው። አላህ የሚሻውን ሁሉ ይመራልና።
إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَالَّذِينَ هَادُوا وَالصَّابِئِينَ وَالنَّصَارَىٰ وَالْمَجُوسَ وَالَّذِينَ أَشْرَكُوا إِنَّ اللَّهَ يَفْصِلُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ
እነዚያ በአላህ ያመኑ እነዚያ አይሁዳውያን፤ ሳቢያኖች፤ ክርስቲያኖችም፤ መጁሶችም እነዚያም (ጣዖታትን በአላህ) ያጋሩ ሁሉ አላህ በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ በእርግጥ መስካሪ (አዋቂ) ነውና።
أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يَسْجُدُ لَهُ مَنْ فِي السَّمَاوَاتِ وَمَنْ فِي الْأَرْضِ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ وَالنُّجُومُ وَالْجِبَالُ وَالشَّجَرُ وَالدَّوَابُّ وَكَثِيرٌ مِنَ النَّاسِ ۖ وَكَثِيرٌ حَقَّ عَلَيْهِ الْعَذَابُ ۗ وَمَنْ يُهِنِ اللَّهُ فَمَا لَهُ مِنْ مُكْرِمٍ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَفْعَلُ مَا يَشَاءُ ۩
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ጸሐይና፤ ጨረቃም፤ ከዋክብትም፤ ተራሮችም፤ ዛፎችም፤ ተንቀሳቃሾችም ፍጡራንና ከሰዎች ብዙዎችም ለእርሱ የሚሰግዱለት መሆኑን አታውቅምን? ብዙዉም በእርሱ ላይ የአላህ ቅጣት ተረጋገጠበት። አላህ የሚያዋርደው ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለዉም። አላህ የሻውን ይሰራልና።
هَٰذَانِ خَصْمَانِ اخْتَصَمُوا فِي رَبِّهِمْ ۖ فَالَّذِينَ كَفَرُوا قُطِّعَتْ لَهُمْ ثِيَابٌ مِنْ نَارٍ يُصَبُّ مِنْ فَوْقِ رُءُوسِهِمُ الْحَمِيمُ
እነዚህ በጌታቸው ጉዳይ የተከራከሩ ሁለት ባላጋራዎች ናቸው። እነዚያ በአላህ የካዱት የእሳት ልብሶች ተለክተውላቸዋል፤ እንዲቀልጥ ከራሶቻቸው ላይ የፈላ ውሃ ይምቧቧባቸዋል።
يُصْهَرُ بِهِ مَا فِي بُطُونِهِمْ وَالْجُلُودُ
በሆዶቻቸው ውስጥ ያለውና ቆዳዎቻቸው በእርሱ ይቀለጣል።
وَلَهُمْ مَقَامِعُ مِنْ حَدِيدٍ
ለእነርሱም (መቅጫ) ከብረት የሆኑ መዶሻዎች አሉ።
كُلَّمَا أَرَادُوا أَنْ يَخْرُجُوا مِنْهَا مِنْ غَمٍّ أُعِيدُوا فِيهَا وَذُوقُوا عَذَابَ الْحَرِيقِ
ከጭንቀት ብርታት የተነሳ ከእርሷ ለመውጣት በፈለጉ ቁጥር በእርሷ ውስጥ እንዲመለሱ ይደረጋሉ። «ያን በጣም የሚያቃጥለውን ቅጣት ቅመሱ።» (ይባላሉ።)
إِنَّ اللَّهَ يُدْخِلُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ يُحَلَّوْنَ فِيهَا مِنْ أَسَاوِرَ مِنْ ذَهَبٍ وَلُؤْلُؤًا ۖ وَلِبَاسُهُمْ فِيهَا حَرِيرٌ
አላህ እነዚያን በትክክል ያመኑትንና መልካም ስራዎችን የሰሩትን ሰዎች በስሮቻቸው ጅረት ወንዞች በሚፈሱባቸው ገነቶች ያስገባቸዋል። በእርሷ ውስጥ የወርቅ አንባሮችና ሉልን ይሸለማሉ። በእርሷ ውስጥ ልብሶቻቸዉም ከሐር የተሰሩ ናቸው።
وَهُدُوا إِلَى الطَّيِّبِ مِنَ الْقَوْلِ وَهُدُوا إِلَىٰ صِرَاطِ الْحَمِيدِ
ወደ መልካም ንግግር ተመሩ፣ ምስጉን ወደ ሆነው (ጌታ) መንገድም ተመሩ።
إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا وَيَصُدُّونَ عَنْ سَبِيلِ اللَّهِ وَالْمَسْجِدِ الْحَرَامِ الَّذِي جَعَلْنَاهُ لِلنَّاسِ سَوَاءً الْعَاكِفُ فِيهِ وَالْبَادِ ۚ وَمَنْ يُرِدْ فِيهِ بِإِلْحَادٍ بِظُلْمٍ نُذِقْهُ مِنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ
እነዚያ በአላህ የካዱና (ሰዎችን) ከአላህ መንገድና ከዚያም በውስጡ ነዋሪ ለሆኑትም ሆነ ከሩቅ ለሚመጡት (ሰዎች) እኩል ካደረግነው ከተከበረው መስጊድ የሚከለክሉ ሁሉ (አሳማሚ ቅጣት እንቀጣቸዋለን።) በእርሱም ውስጥ ከትክክለኛ መንገድ በመዘንበል ራሱን በዳይ ሆኖ (ማንኛውንም ነገር) የሚያስብ ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን።
وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَاهِيمَ مَكَانَ الْبَيْتِ أَنْ لَا تُشْرِكْ بِي شَيْئًا وَطَهِّرْ بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْقَائِمِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለኢብራሂም የቤቱን የከዕባን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት (እንዲህ) ባልነውም ጊዜ (የሆነውን አስታውስ): «በኔ ምንንም አታጋራ። ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት (ለኢባዳ) ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸዉም ለሚደፉት (ሩኩዕና ሱጁድ ለሚያደርጉት) ንጹህ አድርግላቸው።
وَأَذِّنْ فِي النَّاسِ بِالْحَجِّ يَأْتُوكَ رِجَالًا وَعَلَىٰ كُلِّ ضَامِرٍ يَأْتِينَ مِنْ كُلِّ فَجٍّ عَمِيقٍ
«ኢብራሂም ሆይ! በሰዎች መካከል የሐጅን ትእዛዝ አሰማ። እግረኞችና ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎች ሁሉ ላይም ሆነዉም ይመጡልሃልና።
لِيَشْهَدُوا مَنَافِعَ لَهُمْ وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَعْلُومَاتٍ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُمْ مِنْ بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۖ فَكُلُوا مِنْهَا وَأَطْعِمُوا الْبَائِسَ الْفَقِيرَ
«ለእነርሱ የሆኑ ጥቅሞችን ያገኙ ዘንድና በእነዚያ በታወቁ ቀናትም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ ይመጡልሃል። ከእርሷም ብሉ። ችግረኛ ድሀንም አብሉ።
ثُمَّ لْيَقْضُوا تَفَثَهُمْ وَلْيُوفُوا نُذُورَهُمْ وَلْيَطَّوَّفُوا بِالْبَيْتِ الْعَتِيقِ
«ከዚያም (እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን) ትርፍ አካላቸውንና እድፋቸውን ያስወግዱ። ስለቶቻቸውንም በትክክል ይሙሉ። በጥንታዊዉም ቤት በካዕባ ዙሪያ ይዙሩ።» አልን።
ذَٰلِكَ وَمَنْ يُعَظِّمْ حُرُمَاتِ اللَّهِ فَهُوَ خَيْرٌ لَهُ عِنْدَ رَبِّهِ ۗ وَأُحِلَّتْ لَكُمُ الْأَنْعَامُ إِلَّا مَا يُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ ۖ فَاجْتَنِبُوا الرِّجْسَ مِنَ الْأَوْثَانِ وَاجْتَنِبُوا قَوْلَ الزُّورِ
ይሀው ነው። የአላህንም ህግጋት የሚያከብር ሁሉ እርሱ እጌታው ዘንድ ለእርሱ በጣም የተሻለ መልካም ነው። የቤት እንስሳትም በእናንተ ላይ እርም መሆኑ ከሚነበብላችሁ በስተቀር ለእናንተ ተፈቅዳላችኋለች። ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ። ሐሰትንም ቃል ራቁ።
حُنَفَاءَ لِلَّهِ غَيْرَ مُشْرِكِينَ بِهِ ۚ وَمَنْ يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَكَأَنَّمَا خَرَّ مِنَ السَّمَاءِ فَتَخْطَفُهُ الطَّيْرُ أَوْ تَهْوِي بِهِ الرِّيحُ فِي مَكَانٍ سَحِيقٍ
ለአላህ ታዛዦች፤ በእርሱ የማታጋሩና ወደ ቀጥተኞች መንገድ የተዘነበላችሁ ሁኑ። በአላህ የሚያጋራ ሁሉ ከሰማይ እንደ ወደቀና በራሪ እንደምትነጥቀው ወይም ንፋስ በሩቅ ስፍራ እንደምትጥለው ነው።
ذَٰلِكَ وَمَنْ يُعَظِّمْ شَعَائِرَ اللَّهِ فَإِنَّهَا مِنْ تَقْوَى الْقُلُوبِ
(ነገሩ) ይህ ነው። የአላህን ሃይማኖታዊ ምልክቶች የሚያከብር ሁሉ ይህ ድርጊቱ አላህን ከሚፈሩ ልቦች የሚፈጸም ጥንቃቄ ነው።
لَكُمْ فِيهَا مَنَافِعُ إِلَىٰ أَجَلٍ مُسَمًّى ثُمَّ مَحِلُّهَا إِلَى الْبَيْتِ الْعَتِيقِ
ለእናንተ በእርሷ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ጥቅሞች አሏችሁ። ከዚያም የ(ሀድዩ) ማረጃ ስፍራ እጥንታዊው ቤት አጠገብ ነው።
وَلِكُلِّ أُمَّةٍ جَعَلْنَا مَنْسَكًا لِيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُمْ مِنْ بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۗ فَإِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ
ከቤት እንስሳት በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ብቻ ያወሱ ዘንድ ለህዝቦች ሁሉ (ወደ አላህ) መስዋዕት ማቅረብን ሀይማኖታዊ ሥርአቶችን ደነገግን። አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው። እርሱንም ብቻ ታዘዙ። ለአላህ ተዋራጆችንም በመልካም ነገር አብስራቸው።
الَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَالصَّابِرِينَ عَلَىٰ مَا أَصَابَهُمْ وَالْمُقِيمِي الصَّلَاةِ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنْفِقُونَ
እነዚያን አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚጨነቁትን (የሚፈሩትን)፤ በደረሰባቸዉም መከራ ላይ ታጋሾችን፤ ሰላትንም አስተካክለው ሰጋጆችን፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ የሚለግሱትን በገነት አብስር።
وَالْبُدْنَ جَعَلْنَاهَا لَكُمْ مِنْ شَعَائِرِ اللَّهِ لَكُمْ فِيهَا خَيْرٌ ۖ فَاذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ عَلَيْهَا صَوَافَّ ۖ فَإِذَا وَجَبَتْ جُنُوبُهَا فَكُلُوا مِنْهَا وَأَطْعِمُوا الْقَانِعَ وَالْمُعْتَرَّ ۚ كَذَٰلِكَ سَخَّرْنَاهَا لَكُمْ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
ግመሎችንም ለእናንተ ከአላህ ሃይማኖት ምልክቶች አደረግናቸው። በእነርሱ ለእናንተ ብዙ መልካም ጥቅሞች አሏችሁ። በእርሷም ላይ ስታርዷት በሦስት እግሮቿ ቆማ የተሰለፈች ሆና የአላህን ስም አውሱ። ጎኖቻቸዉም በወደቁ ጊዜ ከእርሷ ብሉ። በግልጽ ለማኝንም ለልመና የሚያገዳድምንም አብሉ። ልክ እንደዚሁ ታመሰግኑ ዘንድ ለእናንተ ገራናት።
لَنْ يَنَالَ اللَّهَ لُحُومُهَا وَلَا دِمَاؤُهَا وَلَٰكِنْ يَنَالُهُ التَّقْوَىٰ مِنْكُمْ ۚ كَذَٰلِكَ سَخَّرَهَا لَكُمْ لِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ ۗ وَبَشِّرِ الْمُحْسِنِينَ
አላህን ስጋዎቿም ሆኑ ደሞቿ ፈጽሞ አይደርሰዉም። ግን ከእናንተ የሆነው ፍራቻ ይደርሰዋል። እንደዚሁ አላህን በመራችሁ ላይ ልታከብሩት ለእናንተ ገራት። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጎ ሰሪዎችንም አብስር።
إِنَّ اللَّهَ يُدَافِعُ عَنِ الَّذِينَ آمَنُوا ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ خَوَّانٍ كَفُورٍ
አላህ ከእነዚያ በእርሱ ካመኑት ላይ ይከላከልላቸዋል። አላህ ከዳተኛንና ውለታ ቢስን ሁሉ አይወድምና።
أُذِنَ لِلَّذِينَ يُقَاتَلُونَ بِأَنَّهُمْ ظُلِمُوا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ نَصْرِهِمْ لَقَدِيرٌ
ለእነዚያ በከሓዲያን ጦርነት ለተከፈተባቸው (አማኞች) የተበደሉ በመሆናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው። አላህ እነርሱን በመርዳት ላይ በእርግጥ ቻይ ነውና።
الَّذِينَ أُخْرِجُوا مِنْ دِيَارِهِمْ بِغَيْرِ حَقٍّ إِلَّا أَنْ يَقُولُوا رَبُّنَا اللَّهُ ۗ وَلَوْلَا دَفْعُ اللَّهِ النَّاسَ بَعْضَهُمْ بِبَعْضٍ لَهُدِّمَتْ صَوَامِعُ وَبِيَعٌ وَصَلَوَاتٌ وَمَسَاجِدُ يُذْكَرُ فِيهَا اسْمُ اللَّهِ كَثِيرًا ۗ وَلَيَنْصُرَنَّ اللَّهُ مَنْ يَنْصُرُهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ
ለእነዚያ «ጌታችን አላህ ነው።» ከማለታቸው በስተቀር ያለ አግባብ ከየቀያቸው የተባረሩ ለሆኑት (መጋደል ተፈቀደላቸው)። አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ ባልነበረ ኖሮ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችና በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም በተፈረሱ ነበር። አላህም ሃይማኖቱን የሚረዳውን ሁሉ በእርግጥ ይረዳዋል። አላህ ብርቱና ሁሉን አሸናፊ ነውና።
الَّذِينَ إِنْ مَكَّنَّاهُمْ فِي الْأَرْضِ أَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ وَأَمَرُوا بِالْمَعْرُوفِ وَنَهَوْا عَنِ الْمُنْكَرِ ۗ وَلِلَّهِ عَاقِبَةُ الْأُمُورِ
እነርሱ ማለት እነዚያ በምድር ላይ ብናስመቻቸው (የበላይነትን ሰጥተን ባጎናጸፍናቸው ኖሮ) ሶላትን እንደሚገባ የሚያስተካክሉ፤ ዘካንም የሚሰጡ፤ በደግ ነገርም የሚያዝዙ፤ ከመጥፎ ነገርም የሚከለክሉ ናቸው። የነገሮች ሁሉ መጨረሻ ወደ አላህ ብቻ ነው።
وَإِنْ يُكَذِّبُوكَ فَقَدْ كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ وَعَادٌ وَثَمُودُ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ከእነርሱ በፊት የኑሕ ህዝቦች፣ የዓድና የሰሙድም በእርግጥ አስተባብለዋል።
وَقَوْمُ إِبْرَاهِيمَ وَقَوْمُ لُوطٍ
የኢብራሂምም ህዝቦች የሉጥም ህዝቦች እንደዚሁ አስተባብለዋል፤
وَأَصْحَابُ مَدْيَنَ ۖ وَكُذِّبَ مُوسَىٰ فَأَمْلَيْتُ لِلْكَافِرِينَ ثُمَّ أَخَذْتُهُمْ ۖ فَكَيْفَ كَانَ نَكِيرِ
የመድየንም ሰዎች እንዲሁ አስተባብለዋል። ሙሳም ተስተባብሏል። ለከሓዲያንም ጊዜን ሰጠኋቸው። ከዚያ ያዝኳቸው። ቅጣቴም እንዴት ነበረ (ተመልከቱ)።
فَكَأَيِّنْ مِنْ قَرْيَةٍ أَهْلَكْنَاهَا وَهِيَ ظَالِمَةٌ فَهِيَ خَاوِيَةٌ عَلَىٰ عُرُوشِهَا وَبِئْرٍ مُعَطَّلَةٍ وَقَصْرٍ مَشِيدٍ
ከከተሞች መካከል በደለኛ ሆነው ያጠፋናቸው እና በጣሪያዎቻቸው ላይ ወዳቂ የሆኑ ብዙ ናቸው። ከተራቆተም የውሃ ጉድጓድ ከተገነባም ህንፃ ያጠፋነው ብዙ ነው።
أَفَلَمْ يَسِيرُوا فِي الْأَرْضِ فَتَكُونَ لَهُمْ قُلُوبٌ يَعْقِلُونَ بِهَا أَوْ آذَانٌ يَسْمَعُونَ بِهَا ۖ فَإِنَّهَا لَا تَعْمَى الْأَبْصَارُ وَلَٰكِنْ تَعْمَى الْقُلُوبُ الَّتِي فِي الصُّدُورِ
ለእነርሱም የሚያውቁባቸው ልቦች፤ ወይም የሚሰሙባቸው ጆሮዎች ይኖሯቸው ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን? እነሆ ዓይኖች አይታወሩም። እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ናቸው የሚታወሩት።
وَيَسْتَعْجِلُونَكَ بِالْعَذَابِ وَلَنْ يُخْلِفَ اللَّهُ وَعْدَهُ ۚ وَإِنَّ يَوْمًا عِنْدَ رَبِّكَ كَأَلْفِ سَنَةٍ مِمَّا تَعُدُّونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) አላህ ቀጠሮውን በፍጹም የማይጥስ ሲሆን ቅጣትን እንድታመጣ ያቻኩሉሃል (ያጣድፉሃል)። በጌታህ ዘንድ አንዱ ቀን ከምትቆጥሩት ቀን እንደ አንድ ሺህ ዓመት የሚመጥን ነው።
وَكَأَيِّنْ مِنْ قَرْيَةٍ أَمْلَيْتُ لَهَا وَهِيَ ظَالِمَةٌ ثُمَّ أَخَذْتُهَا وَإِلَيَّ الْمَصِيرُ
ከከተማ በዳይ ሆና ጊዜ የሰጠኋትና ከዚያ የያዝኳት የቀጣኋት ብዙ ናት። የመጨረሻው መመለሻም ወደ እኔ ብቻ ነው።
قُلْ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّمَا أَنَا لَكُمْ نَذِيرٌ مُبِينٌ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ለእናንተ ግልጽ አስፈራሪ ብቻ ነኝ።» በላቸው።
فَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ مَغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ
እነዚያም በትክክል ያመኑና መልካም ስራዎችን የሰሩ ለእነርሱ ምህረትና ያማረ ሲሳይ አላቸው።
وَالَّذِينَ سَعَوْا فِي آيَاتِنَا مُعَاجِزِينَ أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَحِيمِ
እነዚያ ከአላህ የሚያመልጡ መስሏቸው አናቅጻችንን በመንቀፍ የተጉ ሁሉ እነርሱ የእሳት ጓዶች ናቸው።
وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ مِنْ رَسُولٍ وَلَا نَبِيٍّ إِلَّا إِذَا تَمَنَّىٰ أَلْقَى الشَّيْطَانُ فِي أُمْنِيَّتِهِ فَيَنْسَخُ اللَّهُ مَا يُلْقِي الشَّيْطَانُ ثُمَّ يُحْكِمُ اللَّهُ آيَاتِهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት አንድንም መልዕክተኛ ወይም ነብይ አላክንም ባነበበ ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ውስጥ የማጥመሚያን ሀሳብ የሚጥል ቢሆን እንጂ። ወዲያዉም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ማጥመሚያ ቃል ያስወግዳል። ከዚያም አላህ አናቅጽን ያጠነክራል (ያጸናል)። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።
لِيَجْعَلَ مَا يُلْقِي الشَّيْطَانُ فِتْنَةً لِلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِمْ مَرَضٌ وَالْقَاسِيَةِ قُلُوبُهُمْ ۗ وَإِنَّ الظَّالِمِينَ لَفِي شِقَاقٍ بَعِيدٍ
ሰይጣን የሚጥለውን ነገር ለእነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ላለባቸውና ልቦቻቸው ደረቆች ለሆኑት ፈተና ሊያደርግ (ይህንን አደረገ)። በዳዮችም ከእውነት በራቀ ጭቅጭቅ (ውዝግብ) ውስጥ ናቸው።
وَلِيَعْلَمَ الَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ أَنَّهُ الْحَقُّ مِنْ رَبِّكَ فَيُؤْمِنُوا بِهِ فَتُخْبِتَ لَهُ قُلُوبُهُمْ ۗ وَإِنَّ اللَّهَ لَهَادِ الَّذِينَ آمَنُوا إِلَىٰ صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ
እነዚያም እውቀትን የተሰጡት እርሱ (ቁርኣን) ከጌታህ የሆነ እውነት መሆኑን እንዲያውቁና በእርሱ እንዲያምኑ ልቦቻቸዉም ለእርሱ እንዲተናነሱ (ይህንን አደረገ)። አላህም እነዚያን በትክክል ያመኑትን ሁሉ ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ መሪ ነው።
وَلَا يَزَالُ الَّذِينَ كَفَرُوا فِي مِرْيَةٍ مِنْهُ حَتَّىٰ تَأْتِيَهُمُ السَّاعَةُ بَغْتَةً أَوْ يَأْتِيَهُمْ عَذَابُ يَوْمٍ عَقِيمٍ
እነዚያ የካዱት ሰዎች ሰዓቲቱ በድንገት እስከምትመጣባቸው ወይም ከደግ ነገር መካን የሆነው ቀን ቅጣት እስከሚመጣባቸው ድረስ በቁርኣን ጉዳይ ከመጠራጠር አያቆሙም።
الْمُلْكُ يَوْمَئِذٍ لِلَّهِ يَحْكُمُ بَيْنَهُمْ ۚ فَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فِي جَنَّاتِ النَّعِيمِ
በዚያ ቀን ንግስናው የአላህ ብቻ ነው። በመካከላቸውም ይፈርዳል። እነዚያም ያመኑትና መልካም ስራዎችን የሰሩት በመደሰቻ ገነቶች ውስጥ ናቸው።
وَالَّذِينَ كَفَرُوا وَكَذَّبُوا بِآيَاتِنَا فَأُولَٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُهِينٌ
እነዚያም የካዱትና በአናቅጻችንም ያስተባበሉት ሁሉ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው።
وَالَّذِينَ هَاجَرُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ ثُمَّ قُتِلُوا أَوْ مَاتُوا لَيَرْزُقَنَّهُمُ اللَّهُ رِزْقًا حَسَنًا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ لَهُوَ خَيْرُ الرَّازِقِينَ
እነዚያም ለአላህ ሀይማኖት ሲሉ የተሰደዱና ከዚያም ሲታገሉ የተገደሉ ወይም የሞቱ አላህ መልካምን ሲሳይ በእርግጥ ይሰጣቸዋል። አላህም እርሱ ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው።
لَيُدْخِلَنَّهُمْ مُدْخَلًا يَرْضَوْنَهُ ۗ وَإِنَّ اللَّهَ لَعَلِيمٌ حَلِيمٌ
የሚወዱትን መግቢያ ገነትን በእርግጥ ያስገባቸዋል። አላህም በእርግጥ አዋቂና ታጋሽ ነውና።
ذَٰلِكَ وَمَنْ عَاقَبَ بِمِثْلِ مَا عُوقِبَ بِهِ ثُمَّ بُغِيَ عَلَيْهِ لَيَنْصُرَنَّهُ اللَّهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَعَفُوٌّ غَفُورٌ
(ነገሩ) ይህ ነው። ያ በተበደለበት ብጤ (መጠን) የተበቀለና ከዚያ በእርሱ ላይ ግፍ የተዋለበት ሰው አላህ በእርግጥ ይረዳዋል። አላህ ይቅር ባይና መሓሪ ነውና።
ذَٰلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ يُولِجُ اللَّيْلَ فِي النَّهَارِ وَيُولِجُ النَّهَارَ فِي اللَّيْلِ وَأَنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ
ይህ የሆነው አላህ ሌሊትን በቀን ውስጥ የሚያስገባ፤ ቀንንም በሌሊት ውስጥ የሚያስገባ (ቻይ) ፤ ሁሉንም ሰሚ፤ ሁሉንም ተመልካች በመሆኑ ነው።
ذَٰلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدْعُونَ مِنْ دُونِهِ هُوَ الْبَاطِلُ وَأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ
ይህ የሆነው አላህም ፍፁም እውነት በመሆኑ፤ ከርሱም ሌላ የሚገዙት ነገር ፍጹም ውሸት በመሆኑና አላህም ከፍተኛውና ታላቁ በመሆኑ ነው።
أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ أَنْزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَتُصْبِحُ الْأَرْضُ مُخْضَرَّةً ۗ إِنَّ اللَّهَ لَطِيفٌ خَبِيرٌ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ከሰማይ ውሃን ማውረዱንና ከዚያ ምድር የምትለመልም መሆኗን አላየህምን? አላህ ፍጹም ሩህሩህና ውስጠ አዋቂ ነውና።
لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ وَإِنَّ اللَّهَ لَهُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ
በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው። አላህ እርሱ ተብቃቂዉና ምስጉኑ ነውና።
أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ سَخَّرَ لَكُمْ مَا فِي الْأَرْضِ وَالْفُلْكَ تَجْرِي فِي الْبَحْرِ بِأَمْرِهِ وَيُمْسِكُ السَّمَاءَ أَنْ تَقَعَ عَلَى الْأَرْضِ إِلَّا بِإِذْنِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ بِالنَّاسِ لَرَءُوفٌ رَحِيمٌ
አላህ በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ ለእናንተ የገራላችሁ መርከቦችንም በባህር ውስጥ በትእዛዙ የሚንሻለሉ ሲሆኑ የገራላችሁ መሆኑን፤ ሰማይንም በፈቃዱ ካልሆነ በምድር ላይ እንዳትወድቅ የሚይዛት መሆኑን አላየህምን? አላህ ለሰዎች በእርግጥ ሩህሩህና አዛኝ ነውና።
وَهُوَ الَّذِي أَحْيَاكُمْ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يُحْيِيكُمْ ۗ إِنَّ الْإِنْسَانَ لَكَفُورٌ
እርሱም ያ ህያው ያደረጋችሁ ነው። ከዚያም ይገድላችኋል። ከዚያም ህያው ያደርጋችኋል። ሰው በእርግጥ በጣም ከሓዲ ነው።
لِكُلِّ أُمَّةٍ جَعَلْنَا مَنْسَكًا هُمْ نَاسِكُوهُ ۖ فَلَا يُنَازِعُنَّكَ فِي الْأَمْرِ ۚ وَادْعُ إِلَىٰ رَبِّكَ ۖ إِنَّكَ لَعَلَىٰ هُدًى مُسْتَقِيمٍ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለየህዝቡ ሁሉ እነርሱ የሚሰሩበት የሆነን ስርዓተ ሃይማኖት አድርገናል። ስለዚህ በነገሩ አይከራከሩህ። ወደ ጌታህ መንገድም ጥራ። አንተ በእርግጥ በቅኑ መመርያ ላይ ነህና።
وَإِنْ جَادَلُوكَ فَقُلِ اللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا تَعْمَلُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢከራከሩህም (እንዲህ) በላቸው: «አላህ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነው።
اللَّهُ يَحْكُمُ بَيْنَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فِيمَا كُنْتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ
«አላህ በትንሳኤ ቀን በዚያ በእርሱ ትለያዩበት (ትወዛገቡበት) በነበራችሁት ሁሉ በመካከላችሁ ይፈርዳል።» (በላቸው)
أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ ۗ إِنَّ ذَٰلِكَ فِي كِتَابٍ ۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ በእርግጥ የሚያውቅ መሆኑን አታውቅምን? ይህ በመጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ እውነት ነው። ይህም በአላህ ላይ ገር ነው።
وَيَعْبُدُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ سُلْطَانًا وَمَا لَيْسَ لَهُمْ بِهِ عِلْمٌ ۗ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ نَصِيرٍ
ከአላህ ሌላም ምንም ማስረጃን ያላወረደበትንና ለእነርሱም በእርሱ እውቀት የሌላቸውን ነገር ያመልካሉ፤ ለበዳዮች ምንም ረዳት የላቸዉም።
وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ تَعْرِفُ فِي وُجُوهِ الَّذِينَ كَفَرُوا الْمُنْكَرَ ۖ يَكَادُونَ يَسْطُونَ بِالَّذِينَ يَتْلُونَ عَلَيْهِمْ آيَاتِنَا ۗ قُلْ أَفَأُنَبِّئُكُمْ بِشَرٍّ مِنْ ذَٰلِكُمُ ۗ النَّارُ وَعَدَهَا اللَّهُ الَّذِينَ كَفَرُوا ۖ وَبِئْسَ الْمَصِيرُ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አናቅጻችን የተብራሩ ሆነው በእነርሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ በእነዚያ በአላህ በካዱት ሰዎች ፊት ላይ ጥላቻን ታውቃለህ። በእነዚያ አናቅጻችንን በሚያነቡት ላይም በኃይል ሊተናኮሏቸው ይቃረባሉ። ይልቅ ከዚህ የከፋን ነገር ልንገራችሁን? እርሷም እሳት ናት። አላህ ለእነዚያ በርሱ ለካዱት ሰዎች ሁሉ ቀጥሯታል። መመለሻነቷ ምን ይከፋ በላቸው።
يَا أَيُّهَا النَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌ فَاسْتَمِعُوا لَهُ ۚ إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ لَنْ يَخْلُقُوا ذُبَابًا وَلَوِ اجْتَمَعُوا لَهُ ۖ وَإِنْ يَسْلُبْهُمُ الذُّبَابُ شَيْئًا لَا يَسْتَنْقِذُوهُ مِنْهُ ۚ ضَعُفَ الطَّالِبُ وَالْمَطْلُوبُ
ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምሳሌ ተገለጸላችሁ። ለእርሱም አድምጡት፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ጣዖታት ሁሉ ዝንብን ለመፍጠር ቢሰበሰቡ ፈጽሞ መፍጠር እንኳ አይችሉም። አንዳችም ነገር ዝንብ ቢነጥቃቸው ከእርሱ አያስጥሉትም። ፈላጊዉም (አምላኪው) ተፈላጊዉም (ተመላኪው) ደከሙ።
مَا قَدَرُوا اللَّهَ حَقَّ قَدْرِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ
አላህን ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም። አላህ በጣም ሀያልና ሁሉን አሸናፊ ነውና።
اللَّهُ يَصْطَفِي مِنَ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا وَمِنَ النَّاسِ ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ
አላህ ከመላእክት ውስጥ መልዕክተኞችን ይመርጣል። ከሰዎችም መካከል እንደዚሁ መልዕክተኞችን ይመርጣል። አላህ ሁሉን ሰሚ ሁሉን ተመልካች ነው።
يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ ۗ وَإِلَى اللَّهِ تُرْجَعُ الْأُمُورُ
በስተፊታቸዉም ሆነ በስተኋላቸው ያለን ሁሉ ያውቃል። ወደ አላህም ነገሮች ሁሉ ይመለሳሉ።
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ارْكَعُوا وَاسْجُدُوا وَاعْبُدُوا رَبَّكُمْ وَافْعَلُوا الْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ ۩
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በስግደታችሁ አጎንብሱ። በግንባራችሁም ላይ ተደፉ። (ሩኩዕና ሱጁድ አድርጉ) ጌታችሁንም በትክክል ተገዙት። በጎንም ነገር ስሩ። ልትድኑ ይከጀልላችኋልና።
وَجَاهِدُوا فِي اللَّهِ حَقَّ جِهَادِهِ ۚ هُوَ اجْتَبَاكُمْ وَمَا جَعَلَ عَلَيْكُمْ فِي الدِّينِ مِنْ حَرَجٍ ۚ مِلَّةَ أَبِيكُمْ إِبْرَاهِيمَ ۚ هُوَ سَمَّاكُمُ الْمُسْلِمِينَ مِنْ قَبْلُ وَفِي هَٰذَا لِيَكُونَ الرَّسُولُ شَهِيدًا عَلَيْكُمْ وَتَكُونُوا شُهَدَاءَ عَلَى النَّاسِ ۚ فَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَاعْتَصِمُوا بِاللَّهِ هُوَ مَوْلَاكُمْ ۖ فَنِعْمَ الْمَوْلَىٰ وَنِعْمَ النَّصِيرُ
በአላህም ሃይማኖት ተገቢውን ትግል ታገሉ። እርሱ መርጧችኋል። በናንተም ላይ በሃይማኖቱ ውስጥ ምንም ችግር አላደረገባችሁም። የአባታችሁን የኢብራሂምን ሃይማኖት ተከተሉ። እርሱ (አላህ) ከዚህ በፊት በነበሩት መጽሐፍትም ሆነ በዚህ ቁርኣን ሙስሊሞች ብሎ ሰይሟችኋል። (ይሄዉም) መልዕክተኛው በእናንተ ላይ መስካሪ እንዲሆን እና እናንተም በሰዎች ላይ መስካሪዎች እንድትሆኑ ነው። ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ። ዘካንም በአግባቡ ለተገቢው ስጡ። በአላህም ተጠበቁ። እርሱ ረዳታችሁ ነውና። እርሱ ምን ያማረ ጠባቂ፤ ምን ያማረም ረዳት ነው።