سُورَةٌ أَنْزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا وَأَنْزَلْنَا فِيهَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
(ሙስሊሞች ሆይ!) (ይህ) ያወረድነውና በእናንተ ላይ (እንድትሰሩበት) የደነገግነው ምዕራፍ ነው። በርሷም ውስጥ ትገሰጹ ዘንድ ግልጽ አናቅጽን አውርደናል።
القرآن الكريمAfrica Academy
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።
سُورَةٌ أَنْزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا وَأَنْزَلْنَا فِيهَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
(ሙስሊሞች ሆይ!) (ይህ) ያወረድነውና በእናንተ ላይ (እንድትሰሩበት) የደነገግነው ምዕራፍ ነው። በርሷም ውስጥ ትገሰጹ ዘንድ ግልጽ አናቅጽን አውርደናል።
الزَّانِيَةُ وَالزَّانِي فَاجْلِدُوا كُلَّ وَاحِدٍ مِنْهُمَا مِائَةَ جَلْدَةٍ ۖ وَلَا تَأْخُذْكُمْ بِهِمَا رَأْفَةٌ فِي دِينِ اللَّهِ إِنْ كُنْتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۖ وَلْيَشْهَدْ عَذَابَهُمَا طَائِفَةٌ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ
ዝሙተኛይቱ ሴትና ዝሙተኛው ወንድ ከሁለቱ እያንዳንዳቸው (ያላገቡ እንደሆኑ) መቶ ግርፋትን ግረፏቸው። በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ እንደሆናችሁ በእነርሱ ላይ በደነገገው በአላህ ፍርድ ርህራሄ አትያዛችሁ። ሙስሊሞች ሆይ! ቅጣታቸውንም በምትፈጽሙበት ጊዜ ከአማኞች የተወሰኑ ቡድኖች ይገኙበት።
الزَّانِي لَا يَنْكِحُ إِلَّا زَانِيَةً أَوْ مُشْرِكَةً وَالزَّانِيَةُ لَا يَنْكِحُهَا إِلَّا زَانٍ أَوْ مُشْرِكٌ ۚ وَحُرِّمَ ذَٰلِكَ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ
ዝሙተኛ ወንድ ዝሙተኛን ሴት ወይም በአላህ አጋሪን ሴት እንጂ ሌላን አያገባም (አይፈልግም) ። ዝሙተኛይቱም ሴት ዝሙተኛ ወይም በአላህ አጋሪ ወንድ እንጂ ሌላ አያገባትም (አይፈልጋትም)። ይህም በአማኞች ላይ ተከልክሏል።
وَالَّذِينَ يَرْمُونَ الْمُحْصَنَاتِ ثُمَّ لَمْ يَأْتُوا بِأَرْبَعَةِ شُهَدَاءَ فَاجْلِدُوهُمْ ثَمَانِينَ جَلْدَةً وَلَا تَقْبَلُوا لَهُمْ شَهَادَةً أَبَدًا ۚ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْفَاسِقُونَ
እነዚያ ጥብቆችን ሴቶች በዝሙት የሚሰድቡ ከዚያ በሰደቡበት አራት ምስክሮች ያላመጡ ሰማንያ ግርፋት ግረፏቸው። ከእነርሱም ምስክርነትን ለሁልጊዜ አትቀበሉ። እነዚያም እነርሱ አመጸኞች ናቸው።
إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا مِنْ بَعْدِ ذَٰلِكَ وَأَصْلَحُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَحِيمٌ
እነዚያ ከዚህ በኋላ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩ ሲቀሩ። አላህ በጣም መሓሪና አዛኝ ነውና።
وَالَّذِينَ يَرْمُونَ أَزْوَاجَهُمْ وَلَمْ يَكُنْ لَهُمْ شُهَدَاءُ إِلَّا أَنْفُسُهُمْ فَشَهَادَةُ أَحَدِهِمْ أَرْبَعُ شَهَادَاتٍ بِاللَّهِ ۙ إِنَّهُ لَمِنَ الصَّادِقِينَ
እነዚያ ሚስቶቻቸውን (በዝሙት) የሚሰድቡ ለነሱም ከነፍሶቻቸው በስተቀር ምስክሮች የሌሏቸው የሆኑ የአንዳቸው ምስክርነት ከእውነተኞች ለመሆኑ በአላህ ስም አራት ጊዜ ምሎ መመስከር ነው።
وَالْخَامِسَةُ أَنَّ لَعْنَتَ اللَّهِ عَلَيْهِ إِنْ كَانَ مِنَ الْكَاذِبِينَ
አምስተኛይቱም ከውሸታሞች ቢሆን በእርሱ ላይ የአላህ እርግማን እንዲሰፍንበት (ምሎ መመስከር ነው)።
وَيَدْرَأُ عَنْهَا الْعَذَابَ أَنْ تَشْهَدَ أَرْبَعَ شَهَادَاتٍ بِاللَّهِ ۙ إِنَّهُ لَمِنَ الْكَاذِبِينَ
«እርሱም ከውሸታሞች ነው።» ብላ አራት ጊዜ በአላህ ስም መመስከሯ ከእርሷ ላይ ቅጣትን ይከላከልላታል።
وَالْخَامِسَةَ أَنَّ غَضَبَ اللَّهِ عَلَيْهَا إِنْ كَانَ مِنَ الصَّادِقِينَ
አምስተኛይቱም እርሱ ከእውነተኞች ቢሆን በርሷ ላይ የአላህ ቁጣ ይኑርባት ብላ መመስከሯ ነው።
وَلَوْلَا فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَتُهُ وَأَنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ حَكِيمٌ
(እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረና አላህ ጸጸትን ተቀባይና ጥበበኛ ባልሆነ ኖሮ (ውሸታሙን ሁሉ በዚሁ አለም ላይ ይገልጸው ነበር)።
إِنَّ الَّذِينَ جَاءُوا بِالْإِفْكِ عُصْبَةٌ مِنْكُمْ ۚ لَا تَحْسَبُوهُ شَرًّا لَكُمْ ۖ بَلْ هُوَ خَيْرٌ لَكُمْ ۚ لِكُلِّ امْرِئٍ مِنْهُمْ مَا اكْتَسَبَ مِنَ الْإِثْمِ ۚ وَالَّذِي تَوَلَّىٰ كِبْرَهُ مِنْهُمْ لَهُ عَذَابٌ عَظِيمٌ
እነዚያ መጥፎን ውሸት ያመጡ ከናንተው የሆኑ ቡድኖች ናቸው። ለእናንተ ክፉ ነገር እንደሆነ አታስቡት፤ በእውነቱ እርሱ ለእናንተ መልካም ነገር ነው። ከጭፍሮቹ ለእያንዳንዱ ሰው ከኃጢአት የሠራው ሥራ ዋጋ አለው። ያም ከእነርሱ ትልቁን ኃጢአት የተሸከመው ለእርሱ ከባድ ቅጣት አለው።
لَوْلَا إِذْ سَمِعْتُمُوهُ ظَنَّ الْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بِأَنْفُسِهِمْ خَيْرًا وَقَالُوا هَٰذَا إِفْكٌ مُبِينٌ
(ውሸቱን) በሰማችሁት ጊዜ አማኞችና ምዕመናት በነፍሶቻቸው ለምን ደግን ነገር አላሰቡም? ለምንስ «ይህ ግልጽ ቅጥፈት ነው።» አላሉም?
لَوْلَا جَاءُوا عَلَيْهِ بِأَرْبَعَةِ شُهَدَاءَ ۚ فَإِذْ لَمْ يَأْتُوا بِالشُّهَدَاءِ فَأُولَٰئِكَ عِنْدَ اللَّهِ هُمُ الْكَاذِبُونَ
በእርሱ ላይ ለምን አራትን ምስክሮች አላመጡም? ምስክሮቹንም ባላመጡ ጊዜ እነዚያ አላህ ዘንድ ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው።
وَلَوْلَا فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَتُهُ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ لَمَسَّكُمْ فِي مَا أَفَضْتُمْ فِيهِ عَذَابٌ عَظِيمٌ
በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም በእናንተ ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ በውስጡ በገባችሁበት ወሬ ምክንያት ታላቅ ቅጣት በእርግጥ በደረሰባችሁ ነበር።
إِذْ تَلَقَّوْنَهُ بِأَلْسِنَتِكُمْ وَتَقُولُونَ بِأَفْوَاهِكُمْ مَا لَيْسَ لَكُمْ بِهِ عِلْمٌ وَتَحْسَبُونَهُ هَيِّنًا وَهُوَ عِنْدَ اللَّهِ عَظِيمٌ
በምላሶቻችሁም በምትቀባበሉት ጊዜ ለእናንተም በእርሱ እውቀት በሌላችሁ ነገር በአፎቻችሁ በተናገራችሁና አላህ ዘንድ ከባድ ኃጢአት ሆኖ ሳለ ቀላል አድርጋችሁ ባሰባችሁት ጊዜ (ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር)።
وَلَوْلَا إِذْ سَمِعْتُمُوهُ قُلْتُمْ مَا يَكُونُ لَنَا أَنْ نَتَكَلَّمَ بِهَٰذَا سُبْحَانَكَ هَٰذَا بُهْتَانٌ عَظِيمٌ
በሰማችሁትም ጊዜ: «በዚህ ጉዳይ ልንናገር ለእኛ አይገባንም። (አላህ ሆይ!) ጥራት ይገባህ። ይህ ከባድ ቅጥፈት ነው።» አትሉም ነበርን?
يَعِظُكُمُ اللَّهُ أَنْ تَعُودُوا لِمِثْلِهِ أَبَدًا إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ
አማኞች እንደሆናችሁ ወደዚህ መሰል ተግባር ብጤው በፍጹም እንዳትመለሱ አላህ ይገስጻችኋል።
وَيُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ ۚ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ
ለእናንተም አላህ አናቅጽን ይገልጽላችኋል። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው።
إِنَّ الَّذِينَ يُحِبُّونَ أَنْ تَشِيعَ الْفَاحِشَةُ فِي الَّذِينَ آمَنُوا لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ ۚ وَاللَّهُ يَعْلَمُ وَأَنْتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
እነዚያ በነዚያ በትክክል በአላህ ባመኑት ሰዎች መካከል መጥፎ ወሬ እንድትስፋፋ የሚወዱ ለእነርሱ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም አሳማሚ ቅጣት አላቸው። አላህ ሁሉን ነገር ያውቃል እናንተ ግን አታውቁም።
وَلَوْلَا فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَتُهُ وَأَنَّ اللَّهَ رَءُوفٌ رَحِيمٌ
በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታውና እዝነቱ ባልነበረ አላህም ሩህሩህና አዛኝ ባልሆነ ኖሮ (ቶሎ ባጠፋችሁ ነበር)።
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ وَمَنْ يَتَّبِعْ خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ فَإِنَّهُ يَأْمُرُ بِالْفَحْشَاءِ وَالْمُنْكَرِ ۚ وَلَوْلَا فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَتُهُ مَا زَكَىٰ مِنْكُمْ مِنْ أَحَدٍ أَبَدًا وَلَٰكِنَّ اللَّهَ يُزَكِّي مَنْ يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሰይጣንን እርምጃዎች አትከተሉ። የሰይጣንን እርምጃዎች የሚከተል ሰው (ኃጢአትን ተሸከመ)። እርሱ በመጥፎና በሚጠላ ነገር ያዛልና፤ በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከናንተ አንድም ፈጽሞ (ከወንጀል) ባልጠራ ነበር። ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያጠራል። አላህ ሁሉንም ሰሚ ሁሉንም አዋቂ ነው።
وَلَا يَأْتَلِ أُولُو الْفَضْلِ مِنْكُمْ وَالسَّعَةِ أَنْ يُؤْتُوا أُولِي الْقُرْبَىٰ وَالْمَسَاكِينَ وَالْمُهَاجِرِينَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۖ وَلْيَعْفُوا وَلْيَصْفَحُوا ۗ أَلَا تُحِبُّونَ أَنْ يَغْفِرَ اللَّهُ لَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَحِيمٌ
ከናንተም መካከል የችሮታና የሀብት ባለቤቶች የሆኑት ክፍሎች ለቅርብ ዘመዶችና ለድሆችና በአላህም መንገድ ለተሰደዱ ሰዎች ምንንም ነገር ላይሰጡ አይማሉ። ይቅርታም ያድርጉ። ጥፋተኞቹንም ይለፉ። አላህ ለእናንተ ሊምር አትወዱምን ? አላህ መሓሪና አዛኝ ነው።
إِنَّ الَّذِينَ يَرْمُونَ الْمُحْصَنَاتِ الْغَافِلَاتِ الْمُؤْمِنَاتِ لُعِنُوا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَلَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ
እነዚያ ጥብቆቹንና ከዝሙት ዘንጊዎቹን ምዕምናት የሚሰድቡ ሰዎች ሁሉ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ተረገሙ። ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አለባቸው።
يَوْمَ تَشْهَدُ عَلَيْهِمْ أَلْسِنَتُهُمْ وَأَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُمْ بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
በእነርሱ ላይ ምላሶቻቸው እጆቻቸውና እግሮቻቸው ይሰሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን (ከባድ ቅጣት አለላቸው)።
يَوْمَئِذٍ يُوَفِّيهِمُ اللَّهُ دِينَهُمُ الْحَقَّ وَيَعْلَمُونَ أَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ الْمُبِينُ
በዚያም ቀን አላህ ተገቢ ዋጋቸውን ይሞላላቸዋል። አላህም ፍፁም ግልፅ እውነት መሆኑን ያውቃሉ።
الْخَبِيثَاتُ لِلْخَبِيثِينَ وَالْخَبِيثُونَ لِلْخَبِيثَاتِ ۖ وَالطَّيِّبَاتُ لِلطَّيِّبِينَ وَالطَّيِّبُونَ لِلطَّيِّبَاتِ ۚ أُولَٰئِكَ مُبَرَّءُونَ مِمَّا يَقُولُونَ ۖ لَهُمْ مَغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ
መጥፎዎቹ ሴቶች ለመጥፎዎቹ ወንዶች፤መጥፎዎቹ ወንዶችም ለመጥፎዎቹ ሴቶች ብቻ የተገቡ ናቸው። ጥሩዎቹ ሴቶችም ለጥሩዎቹ ወንዶች፤ ጥሩዎቹ ወንዶችም ለጥሩዎቹ ሴቶች ብቻ የሚገቡ ናቸው። እነዚህ ጥሩዎቹም መጥፎዎቹ ከሚሉት ነገር ንጹህ የተደረጉ ናቸው። ለእነርሱ ምህረትና መልካም ሲሳይ አለላቸው።
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَدْخُلُوا بُيُوتًا غَيْرَ بُيُوتِكُمْ حَتَّىٰ تَسْتَأْنِسُوا وَتُسَلِّمُوا عَلَىٰ أَهْلِهَا ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከምታስፈቅዱና በባለቤቶቹ ላይ ሰላምታን እስከምታቀርቡ ድረስ በሌላ ሰዎች ቤቶች አትግቡ። ይህ ጉዳይ ለእናንተም መልካም ነው። እናንተ ትገነዘቡ ዘንድ በዚህ ታዘዛችሁ።
فَإِنْ لَمْ تَجِدُوا فِيهَا أَحَدًا فَلَا تَدْخُلُوهَا حَتَّىٰ يُؤْذَنَ لَكُمْ ۖ وَإِنْ قِيلَ لَكُمُ ارْجِعُوا فَارْجِعُوا ۖ هُوَ أَزْكَىٰ لَكُمْ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ
በውስጧም አንድንም ሰው ባታገኙ ለእናንተ እስከሚፈቀድላችሁ ድረስ አትግቧት። «ተመለሱ» ከተባላችሁም ተመለሱ። እርሱ ለእናንተ የተሻለ ነው። አላህ የምትሠሩትን ሁሉ አዋቂ ነው።
لَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌ أَنْ تَدْخُلُوا بُيُوتًا غَيْرَ مَسْكُونَةٍ فِيهَا مَتَاعٌ لَكُمْ ۚ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا تُبْدُونَ وَمَا تَكْتُمُونَ
መኖሪያ ያልሆኑን ቤቶች ግን በውስጣቸው ለእናንተ ጥቅም ካላችሁ ሳታስፈቅዱ ብትገቡ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም። አላህም የምትገልጹትንም ሆነ የምትደብቁትን ሁሉ ያውቃል።
قُلْ لِلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا مِنْ أَبْصَارِهِمْ وَيَحْفَظُوا فُرُوجَهُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَزْكَىٰ لَهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا يَصْنَعُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለአማኞች ንገራቸው አይኖቻቸውን (ያልተፈቀደላቸዉን) ከማየት ይከልክሉ። ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ። ይህ ለእነርሱ የተሻለ ነው። አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና።
وَقُلْ لِلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ ۖ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا لِبُعُولَتِهِنَّ أَوْ آبَائِهِنَّ أَوْ آبَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ أَبْنَائِهِنَّ أَوْ أَبْنَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي أَخَوَاتِهِنَّ أَوْ نِسَائِهِنَّ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُنَّ أَوِ التَّابِعِينَ غَيْرِ أُولِي الْإِرْبَةِ مِنَ الرِّجَالِ أَوِ الطِّفْلِ الَّذِينَ لَمْ يَظْهَرُوا عَلَىٰ عَوْرَاتِ النِّسَاءِ ۖ وَلَا يَضْرِبْنَ بِأَرْجُلِهِنَّ لِيُعْلَمَ مَا يُخْفِينَ مِنْ زِينَتِهِنَّ ۚ وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለምዕመናት (ሴቶችም) ንገራቸው አይኖቻቸውን ይከልክሉ። ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ። ጌጣቸውንም ግልጽ ከሆነው በስተቀር ሆን ብለው አይግለጡ። ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ያጣፉ። (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው (ሙስሊም ሴቶች) ወይም በእጆቻቸው ለያዙት (ባሪያ) ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለሆኑ ተከታዮች ወይም ለእነዚያ በሴቶች ሀፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ህጻኖች ካልሆነ በስተቀር አይግለጹ። ከጌጣቸዉም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ። ምዕመናኖች ሆይ! ከገሀነም ቅጣት ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ ተጸጸቱ።
وَأَنْكِحُوا الْأَيَامَىٰ مِنْكُمْ وَالصَّالِحِينَ مِنْ عِبَادِكُمْ وَإِمَائِكُمْ ۚ إِنْ يَكُونُوا فُقَرَاءَ يُغْنِهِمُ اللَّهُ مِنْ فَضْلِهِ ۗ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ
(ሙስሊሞች ሆይ!) ከናንተ መካከል ትዳር የሌላቸውን ሰዎች አጋቡ። ከወንዶች ባሮቻችሁና ከሴቶች ባሮቻችሁም ለጋብቻ ብቁ የሆኑትን ክፍሎች አጋቡ። ድሆች ከሆኑም አላህ ከችሮታው ያከብራቸዋል። አላህ ስጦታው ሰፊና ሁሉን አዋቂ ነውና።
وَلْيَسْتَعْفِفِ الَّذِينَ لَا يَجِدُونَ نِكَاحًا حَتَّىٰ يُغْنِيَهُمُ اللَّهُ مِنْ فَضْلِهِ ۗ وَالَّذِينَ يَبْتَغُونَ الْكِتَابَ مِمَّا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ فَكَاتِبُوهُمْ إِنْ عَلِمْتُمْ فِيهِمْ خَيْرًا ۖ وَآتُوهُمْ مِنْ مَالِ اللَّهِ الَّذِي آتَاكُمْ ۚ وَلَا تُكْرِهُوا فَتَيَاتِكُمْ عَلَى الْبِغَاءِ إِنْ أَرَدْنَ تَحَصُّنًا لِتَبْتَغُوا عَرَضَ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۚ وَمَنْ يُكْرِهْهُنَّ فَإِنَّ اللَّهَ مِنْ بَعْدِ إِكْرَاهِهِنَّ غَفُورٌ رَحِيمٌ
እነዚያም የማግቢያን ጣጣ የማያገኙ ሰዎች አላህ ከችሮታው እስከሚያከብራቸው ድረስ ራሳቸውን (ከዝሙት) ይጠብቁ። እነዚያንም እጆቻችሁ ከጨበጧቸው አገልጋዮች መካከል ገንዘብ ሰጥተው ነጻ ለመውጣት መጻጻፍን የሚፈልጉትን ከእነርሱ መልካም ነገርን ብታውቁ (ብታዩ) ተጻጻፏቸው። አላህ ከሰጣችሁ ገንዘብም ስጧቸው። ሴቶች ባሮቻችሁንም መጠበቅን ከፈለጉ የቅርቢቱን ህይወት ጥቅም ለመፈለግ ብላችሁ በዝሙት ተግባር ላይ አታስገድዷቸው። የሚያስገድዳቸዉም ሰው አላህ ከመገደዳቸው በኋላ ለተገደዱት መሓሪና አዛኝ ነውና።
وَلَقَدْ أَنْزَلْنَا إِلَيْكُمْ آيَاتٍ مُبَيِّنَاتٍ وَمَثَلًا مِنَ الَّذِينَ خَلَوْا مِنْ قَبْلِكُمْ وَمَوْعِظَةً لِلْمُتَّقِينَ
(ሰዎች ሆይ!) ወደ እናንተ አብራሪ የሆኑን አናቅጽ ከእነዚያ ከበፊታችሁ ካለፉትም ምሳሌዎች ዓይነት ምሳሌን ለጥንቁቆችም መገሰጫን በእርግጥ አወረድን።
اللَّهُ نُورُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ مَثَلُ نُورِهِ كَمِشْكَاةٍ فِيهَا مِصْبَاحٌ ۖ الْمِصْبَاحُ فِي زُجَاجَةٍ ۖ الزُّجَاجَةُ كَأَنَّهَا كَوْكَبٌ دُرِّيٌّ يُوقَدُ مِنْ شَجَرَةٍ مُبَارَكَةٍ زَيْتُونَةٍ لَا شَرْقِيَّةٍ وَلَا غَرْبِيَّةٍ يَكَادُ زَيْتُهَا يُضِيءُ وَلَوْ لَمْ تَمْسَسْهُ نَارٌ ۚ نُورٌ عَلَىٰ نُورٍ ۗ يَهْدِي اللَّهُ لِنُورِهِ مَنْ يَشَاءُ ۚ وَيَضْرِبُ اللَّهُ الْأَمْثَالَ لِلنَّاسِ ۗ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
አላህ የሰማያትና የምድር ብርሃን (አብሪ) ነው፤ የብርሃኑ ምሳሌ በውስጡ መብራት እንዳለባት ዝግ መስኮት፤ መብራቱ በብርጭቆ ውስጥ የሆነ፤ ብርጭቆው ደግሞ እንደ ሉል የሚያበራ ኮከብ የምትመስል ምስራቃዊም ምዕራባዊም ካልሆነች፤ ከተባረከች የወይራ ዛፍ ዘይቷ እሳት ባይነካዉም እንኳ ሊያበራ የሚቀርብ ከሆነች ዘይት የሚቃጠል እንደሆነ መብራት ነው። ይህ በብርሃን ላይ የሆነ ብርሃን ነው። አላህ ወደ ብርሃኑ የሚሻውን ሰው ይመራል። አላህም ለሰዎች ምሳሌዎችን ያቀርባል። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ ነውና።
فِي بُيُوتٍ أَذِنَ اللَّهُ أَنْ تُرْفَعَ وَيُذْكَرَ فِيهَا اسْمُهُ يُسَبِّحُ لَهُ فِيهَا بِالْغُدُوِّ وَالْآصَالِ
አላህ እንዲከበሩና ስሙ በውስጣቸው እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ (አወድሱት)። በውስጧ (ቤቶች ውስጥ) በጧትና በማታ ለርሱ ያጠሩታል።
رِجَالٌ لَا تُلْهِيهِمْ تِجَارَةٌ وَلَا بَيْعٌ عَنْ ذِكْرِ اللَّهِ وَإِقَامِ الصَّلَاةِ وَإِيتَاءِ الزَّكَاةِ ۙ يَخَافُونَ يَوْمًا تَتَقَلَّبُ فِيهِ الْقُلُوبُ وَالْأَبْصَارُ
አላህን ከማውሳትና ሶላትን ከመስገድ ዘካንም ከመስጠት ንግድም ሽያጭም የማያዘናጋቸው ልቦችና ዓይኖች በእርሱ የሚገላበጡበትን ቀን የሚፈሩ የሆኑ ሰዎች ያጠሩታል።
لِيَجْزِيَهُمُ اللَّهُ أَحْسَنَ مَا عَمِلُوا وَيَزِيدَهُمْ مِنْ فَضْلِهِ ۗ وَاللَّهُ يَرْزُقُ مَنْ يَشَاءُ بِغَيْرِ حِسَابٍ
አላህም የሰሩትን ስራ መልካሙን ሊመነዳቸው ከችሮታዉም ሊጨምርላቸው ያጠሩታል። አላህም ለሚሻው ሁሉ ያለ ግምት ይሰጣል።
وَالَّذِينَ كَفَرُوا أَعْمَالُهُمْ كَسَرَابٍ بِقِيعَةٍ يَحْسَبُهُ الظَّمْآنُ مَاءً حَتَّىٰ إِذَا جَاءَهُ لَمْ يَجِدْهُ شَيْئًا وَوَجَدَ اللَّهَ عِنْدَهُ فَوَفَّاهُ حِسَابَهُ ۗ وَاللَّهُ سَرِيعُ الْحِسَابِ
እነዚያም በአላህ የካዱት ሰዎች መልካም ስራዎቻቸው በበረሃ ሜዳ እንዳለ ሲሪብዱ ነው። ሲሪብዱ ውሃ የጠማው ሰው እንደውሃ አስቦት በቀረበው ጊዜ ምንም ነገር ሆኖ እንደማያገኘው ነው፤ አላህንም እስፍራው ዘንድ ያገኘዋል። ምርመራውንም ይሞላለታል፤ አላህም ምርመራው ፈጣን ነው።
أَوْ كَظُلُمَاتٍ فِي بَحْرٍ لُجِّيٍّ يَغْشَاهُ مَوْجٌ مِنْ فَوْقِهِ مَوْجٌ مِنْ فَوْقِهِ سَحَابٌ ۚ ظُلُمَاتٌ بَعْضُهَا فَوْقَ بَعْضٍ إِذَا أَخْرَجَ يَدَهُ لَمْ يَكَدْ يَرَاهَا ۗ وَمَنْ لَمْ يَجْعَلِ اللَّهُ لَهُ نُورًا فَمَا لَهُ مِنْ نُورٍ
ወይም መጥፎ ስራዎቻቸው ከበላዩ ማዕበል ከበላዩ ደመና ያለበት ማዕበል በሚሸፍነው ጥልቅ ባህር ውስጥ እንዳሉ ጨለማዎች ነው። እነዚያ ከፊላቸው ከከፊሉ በላይ ድርብርብ የሆኑ ጨለማዎች ናቸው። በዚህች የተሞከረ ሰው እጁን ባወጣ ጊዜ ሊያያት አይደርስም። አላህ ለእርሱ ብርሃንን ያላደረገለት ሰው ሁሉ ለእርሱ ምንጊዜም ምንም ብርሃን የለዉም።
أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يُسَبِّحُ لَهُ مَنْ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَالطَّيْرُ صَافَّاتٍ ۖ كُلٌّ قَدْ عَلِمَ صَلَاتَهُ وَتَسْبِيحَهُ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِمَا يَفْعَلُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማያትና በምድር ላይ ያለ ሁሉ በራሪዎችም ክንፎቻቸውን በአየር ላይ ያንሳፈፉ ሆነው ለእርሱ የሚያጠሩ መሆናቸውን አላወቅህምን? ሁሉም ስግደቱንና ማጥራቱን በእርግጥ አወቀ። አላህ የሚሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነውና።
وَلِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِلَى اللَّهِ الْمَصِيرُ
የሰማያትም ሆነ የምድር ግዛት የአላህ ነው። መመለሻም ወደ አላህ ነው።
أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يُزْجِي سَحَابًا ثُمَّ يُؤَلِّفُ بَيْنَهُ ثُمَّ يَجْعَلُهُ رُكَامًا فَتَرَى الْوَدْقَ يَخْرُجُ مِنْ خِلَالِهِ وَيُنَزِّلُ مِنَ السَّمَاءِ مِنْ جِبَالٍ فِيهَا مِنْ بَرَدٍ فَيُصِيبُ بِهِ مَنْ يَشَاءُ وَيَصْرِفُهُ عَنْ مَنْ يَشَاءُ ۖ يَكَادُ سَنَا بَرْقِهِ يَذْهَبُ بِالْأَبْصَارِ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ደመናን የሚነዳ መሆኑን አላየህምን? ከዚያም ከፊሉን ከከፊሉ ያገናኛል፤ ከዚያም የተደራረበ ያደርገዋል፤ ዝናቡንም ከመካከሉ የሚወጣ ሆኖ ታየዋለህ፤ ከሰማይም ከደመናም በውስጡ ካሉት ጋራዎችም በረዶን ያወርዳል። በእርሱም የሚሻውን ሰው በጉዳት ይነካል። ከሻዉም ሰው ላይ ይመልሰዋል። የብልጭታው ብርሃን ዓይኖችን ሊወስድ ይቀርባል።
يُقَلِّبُ اللَّهُ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَعِبْرَةً لِأُولِي الْأَبْصَارِ
አላህ ሌሊትንና ቀንን ያገላብጣል፤ በዚህም ለአስተዋዮች በእርግጥ ማስረጃ አለበት።
وَاللَّهُ خَلَقَ كُلَّ دَابَّةٍ مِنْ مَاءٍ ۖ فَمِنْهُمْ مَنْ يَمْشِي عَلَىٰ بَطْنِهِ وَمِنْهُمْ مَنْ يَمْشِي عَلَىٰ رِجْلَيْنِ وَمِنْهُمْ مَنْ يَمْشِي عَلَىٰ أَرْبَعٍ ۚ يَخْلُقُ اللَّهُ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
አላህም ተንቀሳቃሽን ሁሉ ከውሃ ፈጠረ። ከእነርሱም መካከል በሆዱ ላይ የሚሄድ አለ፤ ከእነርሱም መካከል በሁለት እግሮቹ ላይ የሚሄድ አለ፤ ከእነርሱም መካከል በአራት እግሩ የሚሄድ አለ። አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።
لَقَدْ أَنْزَلْنَا آيَاتٍ مُبَيِّنَاتٍ ۚ وَاللَّهُ يَهْدِي مَنْ يَشَاءُ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ
አብራሪን አናቅጽ በእርግጥ አወረድን፤ አላህ የሚሻውን ወደ ቀጥተኛ መንገድ ይመራዋል።
وَيَقُولُونَ آمَنَّا بِاللَّهِ وَبِالرَّسُولِ وَأَطَعْنَا ثُمَّ يَتَوَلَّىٰ فَرِيقٌ مِنْهُمْ مِنْ بَعْدِ ذَٰلِكَ ۚ وَمَا أُولَٰئِكَ بِالْمُؤْمِنِينَ
(አስመሳዮች) «በአላህና በመልዕክተኛው አምነናል ታዘናልም» ይላሉ። ከዚያም ከዚህ በኋላ ከእነርሱ ከፊሉ ይሸሻል። እነዚያም ትክክለኛ አማኞች አይደሉም።
وَإِذَا دُعُوا إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ لِيَحْكُمَ بَيْنَهُمْ إِذَا فَرِيقٌ مِنْهُمْ مُعْرِضُونَ
ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛዉም በመካከላቸው ለሚከሰቱ ጉዳዮች ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ ከእነርሱ መካከል ከፊሉ ወዲያውኑ ይሸሻሉ።
وَإِنْ يَكُنْ لَهُمُ الْحَقُّ يَأْتُوا إِلَيْهِ مُذْعِنِينَ
እውነቱም (ሐቁ) ለእነርሱ ቢሆን ወደ እርሱ ታዛዦች ሆነው ይመጣሉ።
أَفِي قُلُوبِهِمْ مَرَضٌ أَمِ ارْتَابُوا أَمْ يَخَافُونَ أَنْ يَحِيفَ اللَّهُ عَلَيْهِمْ وَرَسُولُهُ ۚ بَلْ أُولَٰئِكَ هُمُ الظَّالِمُونَ
በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ አለን? ወይስ በነብይነቱ ተጠራጠሩን? ወይስ አላህና መልዕክተኛው በእነርሱ ላይ የሚበድሉ መሆንን ይፈራሉን? ይልቁንም እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው።
إِنَّمَا كَانَ قَوْلَ الْمُؤْمِنِينَ إِذَا دُعُوا إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ لِيَحْكُمَ بَيْنَهُمْ أَنْ يَقُولُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا ۚ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ
የምዕምናን ቃል ግን የነበረው ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው በመካከላቸው ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ «ሰማን ታዘዝንም» ማለት ብቻ ነው። እነዚህ ማለት እነዚያ የፈለጉትን የሚያገኙቱ ናቸው።
وَمَنْ يُطِعِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَيَخْشَ اللَّهَ وَيَتَّقْهِ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْفَائِزُونَ
አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ፤ አላህንም የሚፈራና ቁጣውን የሚጠነቀቀው፤ ፍላጎታቸውን የሚያገኙ እነዚያ እነርሱ ናቸው።
وَأَقْسَمُوا بِاللَّهِ جَهْدَ أَيْمَانِهِمْ لَئِنْ أَمَرْتَهُمْ لَيَخْرُجُنَّ ۖ قُلْ لَا تُقْسِمُوا ۖ طَاعَةٌ مَعْرُوفَةٌ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለዘመቻ ብታዛቸው በእርግጥ እንደሚወጡ የጠነከሩ መሓላዎቻቸውን በአላህ ስም ይምላሉ፤ «አትማሉ። የታወቀ (የንፍቅና) መታዘዝ ነውና። አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።» በላቸው።
قُلْ أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ ۖ فَإِنْ تَوَلَّوْا فَإِنَّمَا عَلَيْهِ مَا حُمِّلَ وَعَلَيْكُمْ مَا حُمِّلْتُمْ ۖ وَإِنْ تُطِيعُوهُ تَهْتَدُوا ۚ وَمَا عَلَى الرَّسُولِ إِلَّا الْبَلَاغُ الْمُبِينُ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ሙስሊሞች ሆይ!) «አላህንና መልዕክተኛውንም ታዘዙ። ብትሸሹም (አትጎዱትም)። በእርሱ ላይ ያለበት የተገደደውን ማድረስ ብቻ ነው። በእናንተም ላይ ያለባችሁ የተገደዳችሁትን መታዘዝ ብቻ ነው። ብትታዘዙትም ወደ ቀናው መንገድ ትመራላችሁ በመልዕክተኛው ላይ ግልጽ ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትምና።» በላቸው።
وَعَدَ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنْكُمْ وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَيَسْتَخْلِفَنَّهُمْ فِي الْأَرْضِ كَمَا اسْتَخْلَفَ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ وَلَيُمَكِّنَنَّ لَهُمْ دِينَهُمُ الَّذِي ارْتَضَىٰ لَهُمْ وَلَيُبَدِّلَنَّهُمْ مِنْ بَعْدِ خَوْفِهِمْ أَمْنًا ۚ يَعْبُدُونَنِي لَا يُشْرِكُونَ بِي شَيْئًا ۚ وَمَنْ كَفَرَ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْفَاسِقُونَ
አላህ እነዚያን ከናንተ መካከል በትክክል ያመኑትንና መልካም ስራዎችን የሰሩትን እነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን እንደተካቸው ሁሉ በምድር ላይ በእርግጥ ሊተካቸው፤ ለእነርሱም ያንን የወደደላቸውን ሃይማኖታቸውን ሊያደላድልላቸው፤ ከፍርሃታቸዉም በኋላ ደህናነትን ሊለውጥላቸው የተስፋን ቃል ሰጥቷቸዋል። በእኔ ምንንም የማያጋሩ ሆነው ሊገዙኝ ነው፤ ከዚያም በኋላ በሱ የካዱ ሰዎች እነዚያ አመጸኞች ማለት እነርሱ ብቻ ናቸው።
وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ
(ሙስሊሞች ሆይ!) ይታዘንላችሁ ዘንድ ሶላትን አስተካክላችሁ ስገዱ፣ ዘካንም ስጡ፣ መልዕክተኛውንም ታዘዙ።
لَا تَحْسَبَنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا مُعْجِزِينَ فِي الْأَرْضِ ۚ وَمَأْوَاهُمُ النَّارُ ۖ وَلَبِئْسَ الْمَصِيرُ
እነዚያን በአላህ የካዱትን በምድር ውስጥ የሚያቅቱ አድርገህ አታስብ፤ መኖሪያቸውም እሳት ናት። ገሀነም በእርግጥም ምንኛ ትከፋ።
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لِيَسْتَأْذِنْكُمُ الَّذِينَ مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ وَالَّذِينَ لَمْ يَبْلُغُوا الْحُلُمَ مِنْكُمْ ثَلَاثَ مَرَّاتٍ ۚ مِنْ قَبْلِ صَلَاةِ الْفَجْرِ وَحِينَ تَضَعُونَ ثِيَابَكُمْ مِنَ الظَّهِيرَةِ وَمِنْ بَعْدِ صَلَاةِ الْعِشَاءِ ۚ ثَلَاثُ عَوْرَاتٍ لَكُمْ ۚ لَيْسَ عَلَيْكُمْ وَلَا عَلَيْهِمْ جُنَاحٌ بَعْدَهُنَّ ۚ طَوَّافُونَ عَلَيْكُمْ بَعْضُكُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያ እጆቻችሁ የጨበጧቸው ባሮች እነዚያም ከናንተ መካከል ለአካለ መጠን ያልደረሱት (ህፃናት) በሶስት ጊዜ: ከጎህ ስግደት በፊት፤ በቀትር ልብሶቻችሁን በምታወልቁበት ጊዜና ከምሽት ስግደትም በኋላ ወደ እናንተ ለመግባት ሲፈልጉ ያስፈቅዷችሁ። እነዚህ የእናንተ ሶስት የሐፍረተ ገላ መግለጫ ጊዜያቶች ናቸውና። ከእነዚህ በኋላ ግን በእናንተም ሆነ በነሱ ላይ (ያለፈቃድ በመግባት) ኃጢአት የለም። እናንተን ለማገልገል በዙሪያችሁ ዟሪዎች ናቸውና። ከፊላችሁ በከፊሉ ላይ ዟሪ ነውና፤ ልክ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ ህግጋቱን ይገልጽላችኋል። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነውና።
وَإِذَا بَلَغَ الْأَطْفَالُ مِنْكُمُ الْحُلُمَ فَلْيَسْتَأْذِنُوا كَمَا اسْتَأْذَنَ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ ۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ
ከናንተም መካከል ሕፃናቶቹ ለአቅመ አዳም በደረሱ ጊዜ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት ታላላቆች እንዳስፈቀዷችሁ ያስፈቅዱ። ልክ እንደዚሁ አላህ ለእናንተ አንቀፆቹን ያብራራል። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው።
وَالْقَوَاعِدُ مِنَ النِّسَاءِ اللَّاتِي لَا يَرْجُونَ نِكَاحًا فَلَيْسَ عَلَيْهِنَّ جُنَاحٌ أَنْ يَضَعْنَ ثِيَابَهُنَّ غَيْرَ مُتَبَرِّجَاتٍ بِزِينَةٍ ۖ وَأَنْ يَسْتَعْفِفْنَ خَيْرٌ لَهُنَّ ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
(ሙስሊሞች ሆይ!) እነዚያ ጋብቻን የማይፈልጉት ባልቴቶች በጌጥ የተገለጹ ሳይሆኑ የላይ ልብሶቻቸውን ቢጥሉ በእርሱ ኃጢአት የለባቸዉም። ግን መጠበቃቸው ለእነርሱ የተሻለ ነው። አላህም ለሚባለው ሁሉ ሰሚ ለሁሉም አዋቂ ነው።
لَيْسَ عَلَى الْأَعْمَىٰ حَرَجٌ وَلَا عَلَى الْأَعْرَجِ حَرَجٌ وَلَا عَلَى الْمَرِيضِ حَرَجٌ وَلَا عَلَىٰ أَنْفُسِكُمْ أَنْ تَأْكُلُوا مِنْ بُيُوتِكُمْ أَوْ بُيُوتِ آبَائِكُمْ أَوْ بُيُوتِ أُمَّهَاتِكُمْ أَوْ بُيُوتِ إِخْوَانِكُمْ أَوْ بُيُوتِ أَخَوَاتِكُمْ أَوْ بُيُوتِ أَعْمَامِكُمْ أَوْ بُيُوتِ عَمَّاتِكُمْ أَوْ بُيُوتِ أَخْوَالِكُمْ أَوْ بُيُوتِ خَالَاتِكُمْ أَوْ مَا مَلَكْتُمْ مَفَاتِحَهُ أَوْ صَدِيقِكُمْ ۚ لَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌ أَنْ تَأْكُلُوا جَمِيعًا أَوْ أَشْتَاتًا ۚ فَإِذَا دَخَلْتُمْ بُيُوتًا فَسَلِّمُوا عَلَىٰ أَنْفُسِكُمْ تَحِيَّةً مِنْ عِنْدِ اللَّهِ مُبَارَكَةً طَيِّبَةً ۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
(ከሰዎች ጋር በመብላት) በዕውር (አይነስውር) ላይ ኃጢአት የለበትም። በአንካሳም ላይ ኃጢአት የለበትም። በበሽተኛም ላይ ኃጢአት የለበትም። በነፍሶቻችሁም ላይ ከቤቶቻችሁ ወይም ከአባቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከእናቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከወንድሞቻችሁ ቤቶች ወይም ከእህቶቻችሁ ቤቶች፤ ወይም ከአባት ወንድሞች አጎቶቻችሁ ቤቶች፤ ወይም ከአባት እህቶች አክስቶቻችሁ ቤቶች ወይም ከእናት ወንድሞች የሹሞቻችሁ ቤቶች፤ ወይም ከእናት እህቶች የሹሜዎቻችሁ ቤቶች ወይም መክፈቻዎችን ከያዛችሁት ቤት ወይም ከወዳጃችሁ ቤት ብትበሉ ኃጢአት የለባችሁም። ተሰብስባችሁ ወይም ተለያይታችሁ ብትበሉ በእናንተ ላይ ምንም ኃጢአት የለባችሁም። ቤቶችንም በገባችሁ ጊዜ ከአላህ ዘንድ የሆነችን የተባረከች መልካም ሰላምታ በነፍሶቻችሁ ላይ ሰላም በሉ። ልክ እንደዚህ አላህ አናቅጽን ለእናንተ ያብራራል፤ ታውቁ ዘንድ።
إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَإِذَا كَانُوا مَعَهُ عَلَىٰ أَمْرٍ جَامِعٍ لَمْ يَذْهَبُوا حَتَّىٰ يَسْتَأْذِنُوهُ ۚ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَأْذِنُونَكَ أُولَٰئِكَ الَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ۚ فَإِذَا اسْتَأْذَنُوكَ لِبَعْضِ شَأْنِهِمْ فَأْذَنْ لِمَنْ شِئْتَ مِنْهُمْ وَاسْتَغْفِرْ لَهُمُ اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَحِيمٌ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ትክክለኛ አማኞች ማለት እነዚያ በአላህና በመልዕክተኛው ያመኑት። ከመልዕክተኛው ጋር በሚሰበሰብ ጉዳይ ላይ በሆኑ ጊዜ እስከሚያስፈቅዱት ድረስ የማይሄዱት ብቻ ናቸው። እነዚያ የሚያስፈቅዱህ እነርሱ እነዚያ በትክክል በአላህና በመልዕክተኛው የሚያምኑት ናቸው። ለግል ጉዳያቸዉም ፈቃድ በጠየቁህ ጊዜ ከእነርሱ ላሻኸው ሰው ፍቀድለት። ለእነርሱም ከአላህ ምህረትን ለምንላቸው። አላህ መሓሪና አዛኝ ነውና።
لَا تَجْعَلُوا دُعَاءَ الرَّسُولِ بَيْنَكُمْ كَدُعَاءِ بَعْضِكُمْ بَعْضًا ۚ قَدْ يَعْلَمُ اللَّهُ الَّذِينَ يَتَسَلَّلُونَ مِنْكُمْ لِوَاذًا ۚ فَلْيَحْذَرِ الَّذِينَ يُخَالِفُونَ عَنْ أَمْرِهِ أَنْ تُصِيبَهُمْ فِتْنَةٌ أَوْ يُصِيبَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
አማኞች ሆይ በመካከላችሁ የመልዕክተኛውን ጥሪ ከፊላችሁ ከፊሉን እንደመጥራት አታድርጉት። ከናንተ ውስጥ እነዚያን እየተከለሉ በመሽሎክሎክ የሚወጡትን አላህ በእርግጥ ያውቃቸዋል። እነዚያም ትእዛዙን የሚጥሱ ሁሉ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ።
أَلَا إِنَّ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ قَدْ يَعْلَمُ مَا أَنْتُمْ عَلَيْهِ وَيَوْمَ يُرْجَعُونَ إِلَيْهِ فَيُنَبِّئُهُمْ بِمَا عَمِلُوا ۗ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
(ሙስሊሞች ሆይ! አስተዉሉ) በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ብቻ ነው። እናንተ በእርሱ ላይ ያላችሁበትን ሁኔታ በእርግጥ ያውቃል። ወደ እርሱ የሚመለሱበትን ቀንም ያውቃል። ከዚያ የሰሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል። አላህም ነገሩን ሁሉ አዋቂ ነውና።