Prostration · as-Sajdah · سورة السجدة · 30 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

الم

አሊፍ፤ ላም፤ ሚይም፤

تَنْزِيلُ الْكِتَابِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِنْ رَبِّ الْعَالَمِينَ

የመጽሐፉ መወረድ ጥርጥር የለበትም። የወረደዉም ከዓለማቱ ጌታ ነው።

أَمْ يَقُولُونَ افْتَرَاهُ ۚ بَلْ هُوَ الْحَقُّ مِنْ رَبِّكَ لِتُنْذِرَ قَوْمًا مَا أَتَاهُمْ مِنْ نَذِيرٍ مِنْ قَبْلِكَ لَعَلَّهُمْ يَهْتَدُونَ

ይልቁንም «ቀጠፈው» ይላሉን? አይደለም። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱ ከጌታህ የሆነ እውነት ነው። በእርሱ ካንተ በፊት ከአስፈራሪ ነቢይ ያልመጣባቸውን ሕዝቦች ልታስፈራራበት ያወረደልህ ነው። እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና።

اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ ۖ مَا لَكُمْ مِنْ دُونِهِ مِنْ وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُونَ

አላህ ያ! ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ ከዚያም ለክብሩ በሚስማማ መልኩ በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ ነው። ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ወዳጅም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?

يُدَبِّرُ الْأَمْرَ مِنَ السَّمَاءِ إِلَى الْأَرْضِ ثُمَّ يَعْرُجُ إِلَيْهِ فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ أَلْفَ سَنَةٍ مِمَّا تَعُدُّونَ

ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር ያስተናብራል፤፤ ከዚያም ከምትቆጥሩት (ዘመን) ልኩ ሺህ ዓመት በሆነ ቀን ውስጥ ወደ እርሱ ይወጣል።

ذَٰلِكَ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ الْعَزِيزُ الرَّحِيمُ

ይህንን ያደረገው ሩቁንም ቅርቡንም ሁሉ አዋቂው፤ ሁሉን አሸናፊና አዛኙ ጌታ ነው።

الَّذِي أَحْسَنَ كُلَّ شَيْءٍ خَلَقَهُ ۖ وَبَدَأَ خَلْقَ الْإِنْسَانِ مِنْ طِينٍ

ያ የፈጠረውን ነገር ሁሉ ያሳመረው። የሰውንም ፍጥረት ከጭቃ የጀመረው ነው።

ثُمَّ جَعَلَ نَسْلَهُ مِنْ سُلَالَةٍ مِنْ مَاءٍ مَهِينٍ

ከዚያም ዘሮቹን ከነጠረ ከደካማ ውሃ የፈጠረ ነው።

ثُمَّ سَوَّاهُ وَنَفَخَ فِيهِ مِنْ رُوحِهِ ۖ وَجَعَلَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ ۚ قَلِيلًا مَا تَشْكُرُونَ

ከዚያም ቅርጹን አስተካከለው። በእርሱ ውስጥም ከመንፈሱ ነፋበት። ለናንተም ጆሮዎችን ዓይኖችንና ልቦችንም አደረገላችሁ። በጣም ጥቂትን ብቻ ታመሰግናላችሁ።

وَقَالُوا أَإِذَا ضَلَلْنَا فِي الْأَرْضِ أَإِنَّا لَفِي خَلْقٍ جَدِيدٍ ۚ بَلْ هُمْ بِلِقَاءِ رَبِّهِمْ كَافِرُونَ

«በምድርም ውስጥ በስብሰን በጠፋን ጊዜ እኛ በአዲስ መፈጠር ውስጥ እንሆናለን?» አሉ። በእውነቱ እነርሱ በጌታቸው መገናኘት ከሓዲያን ናቸው።

قُلْ يَتَوَفَّاكُمْ مَلَكُ الْمَوْتِ الَّذِي وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በእናንተ ላይ የተወከለው መልአከ ሞት ይገድላችኋል። ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ።» በላቸው።

وَلَوْ تَرَىٰ إِذِ الْمُجْرِمُونَ نَاكِسُو رُءُوسِهِمْ عِنْدَ رَبِّهِمْ رَبَّنَا أَبْصَرْنَا وَسَمِعْنَا فَارْجِعْنَا نَعْمَلْ صَالِحًا إِنَّا مُوقِنُونَ

አመጸኞችም በጌታቸው ዘንድ ራሶቻቸውን ያቀረቀሩ ሆነው፡‐ «ጌታችን ሆይ! አየን። ሰማንም። መልካምን እንሠራለንና (ወደ ምድረ ዓለም) መልሰን እኛ አረጋጋጮች ነን» የሚሉ ሲሆኑ ብታይ ኖሮ( አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር)።

وَلَوْ شِئْنَا لَآتَيْنَا كُلَّ نَفْسٍ هُدَاهَا وَلَٰكِنْ حَقَّ الْقَوْلُ مِنِّي لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ أَجْمَعِينَ

በሻንም ኖሮ ነፍስን ሁሉ ቅንነቷን(እምነቷን) በሰጠናት ነበር። ግን ገሀነምን ከአጋንንትና ከሰዎች የተሰበሰቡ ሆነው በእርግጥ እሞላለሁ ማለት ቃሉ ከእኔ ተረጋግጧል።

فَذُوقُوا بِمَا نَسِيتُمْ لِقَاءَ يَوْمِكُمْ هَٰذَا إِنَّا نَسِينَاكُمْ ۖ وَذُوقُوا عَذَابَ الْخُلْدِ بِمَا كُنْتُمْ تَعْمَلُونَ

ይህንንም ቀናችሁን መገናኘትን በመርሳታችሁ ምክንያት ቅጣትን ቅመሱ! እኛ ተውናችሁ። ትሰሩት በነበራችሁትም ጥፋት ዘውታሪን ቅጣት ቅመሱ ይባላሉ።

إِنَّمَا يُؤْمِنُ بِآيَاتِنَا الَّذِينَ إِذَا ذُكِّرُوا بِهَا خَرُّوا سُجَّدًا وَسَبَّحُوا بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ ۩

በአናቅጻችን የሚያምኑት እነዚያ በእርሷ በተገሰጹ ጊዜ ሰጋጆች ሆነው የሚወድቁትና እነርሱም የማይኮሩ ሆነው በጌታቸው ምስጋና (ተጎናጽፈው) የሚያወድሱት ሰዎች ብቻ ናቸው።

تَتَجَافَىٰ جُنُوبُهُمْ عَنِ الْمَضَاجِعِ يَدْعُونَ رَبَّهُمْ خَوْفًا وَطَمَعًا وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنْفِقُونَ

ጌታቸውን ፈርተውና ከጅለው የሚጠሩት ሆነው ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ቦታዎቻቸው ይርቃሉ። ከሰጠናቸዉም ጸጋ ይለግሳሉ።

فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَا أُخْفِيَ لَهُمْ مِنْ قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

ይሰሩት በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም።

أَفَمَنْ كَانَ مُؤْمِنًا كَمَنْ كَانَ فَاسِقًا ۚ لَا يَسْتَوُونَ

አማኝ የሆነ ሰው አመጸኛ እንደሆነ ሰው ነውን? አይስተካከሉም።

أَمَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فَلَهُمْ جَنَّاتُ الْمَأْوَىٰ نُزُلًا بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሰሩማ ለነሱ ይሰሩት በነበሩት ምክንያት መስተንግዶ ሲሆኑ መኖሪያ ገነቶች አሏቸው።

وَأَمَّا الَّذِينَ فَسَقُوا فَمَأْوَاهُمُ النَّارُ ۖ كُلَّمَا أَرَادُوا أَنْ يَخْرُجُوا مِنْهَا أُعِيدُوا فِيهَا وَقِيلَ لَهُمْ ذُوقُوا عَذَابَ النَّارِ الَّذِي كُنْتُمْ بِهِ تُكَذِّبُونَ

እነዚያ ያመጹትማ መኖሪያቸው እሳት ናት። ከእርሷ መውጣትን በፈለጉ ቁጥር በእርሷ ውስጥ ይመለሳሉ ለእነርሱም «ያንን በእርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁትን የእሳት ቅጣት ቅመሱ» ይባላሉ።

وَلَنُذِيقَنَّهُمْ مِنَ الْعَذَابِ الْأَدْنَىٰ دُونَ الْعَذَابِ الْأَكْبَرِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

ይመለሱ ዘንድ ከትልቁ ቅጣት በፊት (በዚህ ዓለም) ትንሹን ቅጣት በእርግጥ እናቀምሳቸዋለን።

وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنْ ذُكِّرَ بِآيَاتِ رَبِّهِ ثُمَّ أَعْرَضَ عَنْهَا ۚ إِنَّا مِنَ الْمُجْرِمِينَ مُنْتَقِمُونَ

በጌታዉም አናቅጽ ከተገሰጸና ከዚያም ከተዋት ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው? (የለም) እኛ ከአመጸኞቹ ተበቃዮች ነን።

وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ فَلَا تَكُنْ فِي مِرْيَةٍ مِنْ لِقَائِهِ ۖ وَجَعَلْنَاهُ هُدًى لِبَنِي إِسْرَائِيلَ

ሙሳን መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱን ከመገናኘትህም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን። ለኢስራኢል ልጆችም መሪ አደረግነው።

وَجَعَلْنَا مِنْهُمْ أَئِمَّةً يَهْدُونَ بِأَمْرِنَا لَمَّا صَبَرُوا ۖ وَكَانُوا بِآيَاتِنَا يُوقِنُونَ

በታገሱና በተዓምራታችን የሚያረጋግጡ በሆኑም ጊዜ ከእነርሱ በትዕዛዛችን የሚመሩ መሪዎችን አደረግን።

إِنَّ رَبَّكَ هُوَ يَفْصِلُ بَيْنَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ فِيمَا كَانُوا فِيهِ يَخْتَلِفُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ በዚያ ይለያዩበት በነበሩት ነገር ሁሉ በትንሳኤ ቀን በመካከላቸው በፍርድ ይለያል።

أَوَلَمْ يَهْدِ لَهُمْ كَمْ أَهْلَكْنَا مِنْ قَبْلِهِمْ مِنَ الْقُرُونِ يَمْشُونَ فِي مَسَاكِنِهِمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ ۖ أَفَلَا يَسْمَعُونَ

ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሰዎች ብዙዎችን ያጠፋን መሆናችን በመኖሪያዎቻቸው የሚሄዱ ሲሆኑ እነርሱ አልተገለጸላቸዉምን? በዚህ ውስጥ አያሌ ምልክቶች አሉበት። አይሰሙምን?

أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّا نَسُوقُ الْمَاءَ إِلَى الْأَرْضِ الْجُرُزِ فَنُخْرِجُ بِهِ زَرْعًا تَأْكُلُ مِنْهُ أَنْعَامُهُمْ وَأَنْفُسُهُمْ ۖ أَفَلَا يُبْصِرُونَ

እኛ ውሃን ወደ ደረቅ ምድር የምንነዳ እንስሶቻቸውና እነርሱ ራሳቸው ከእርሱ የሚበሉለትንም አዝመራ በእርሱ የምናወጣ መሆናችንን አያዩምን? አይመለከቱምን?

وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَٰذَا الْفَتْحُ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ

«ከእውነተኞችም እንደ ሆናችሁ ይህ ፍርድ መቼ ነው።» ይላሉ።

قُلْ يَوْمَ الْفَتْحِ لَا يَنْفَعُ الَّذِينَ كَفَرُوا إِيمَانُهُمْ وَلَا هُمْ يُنْظَرُونَ

«በፍርዱ ቀን እነዚያን የካዱትን ሰዎች እምነታቸው አይጠቅማቸዉም። እነርሱም ጊዜ አይሰጣቸዉም።» በላቸው።

فَأَعْرِضْ عَنْهُمْ وَانْتَظِرْ إِنَّهُمْ مُنْتَظِرُونَ

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን ተዋቸው። ተጠባበቅም። እነርሱም ተጠባባቂዎች ናቸውና።