١ الْحَمْدُ لِلَّهِ فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ جَاعِلِ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا أُولِي أَجْنِحَةٍ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۚ يَزِيدُ فِي الْخَلْقِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
1 ምስጋና ሁሉ ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ፤ መላእክትንም ባለ ሁለት ሁለት፤ ባለ ሶስት ሶስትና ባለ አራት አራት ክንፎች የሆኑ መልዕክተኞች አድራጊ ለሆነው አላህ ይገባው። በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል። አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና።
٢ مَا يَفْتَحِ اللَّهُ لِلنَّاسِ مِنْ رَحْمَةٍ فَلَا مُمْسِكَ لَهَا ۖ وَمَا يُمْسِكْ فَلَا مُرْسِلَ لَهُ مِنْ بَعْدِهِ ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
2 አላህ ለሰዎች ከችሮታ የሚከፍታትን ለእርሷ ምንም አጋጅ የላትም። የሚያግደዉም ከእርሱ በኋላ ለእርሱ ምንም ለቃቂ የለዉም። እርሱ ብቸኛ አሸናፊና ጥበበኛው ነውና።
٣ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ ۚ هَلْ مِنْ خَالِقٍ غَيْرُ اللَّهِ يَرْزُقُكُمْ مِنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ ۚ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ
3 እናንተ ሰዎች ሆይ! በእናንተ ላይ (ያለውን) የአላህን ጸጋ አስታውሱ። ከአላህ ሌላ ፈጣሪ አለን? ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣችሁ አለን? ከእርሱ በስተቀር አምላክ (ሰጪም) የለም። ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ።
٤ وَإِنْ يُكَذِّبُوكَ فَقَدْ كُذِّبَتْ رُسُلٌ مِنْ قَبْلِكَ ۚ وَإِلَى اللَّهِ تُرْجَعُ الْأُمُورُ
4 (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ካንተ በፊት የነበሩ ነብያትም ህዝቦቻቸው አስተባብለዋቸዋል። የሁሉ ነገር መመለሻ ወደ አላህ ብቻ ነው።
٥ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّ وَعْدَ اللَّهِ حَقٌّ ۖ فَلَا تَغُرَّنَّكُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا ۖ وَلَا يَغُرَّنَّكُمْ بِاللَّهِ الْغَرُورُ
5 እናንተ ሰዎች ሆይ! የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው። እናም የቅርቢቱም ህይወት አታታላችሁ። አታላዩም (ሰይጣን) በአላህ ላይ አያታላችሁ።
٦ إِنَّ الشَّيْطَانَ لَكُمْ عَدُوٌّ فَاتَّخِذُوهُ عَدُوًّا ۚ إِنَّمَا يَدْعُو حِزْبَهُ لِيَكُونُوا مِنْ أَصْحَابِ السَّعِيرِ
6 ሰይጣን ለእናንተ የለየለት ጠላት ነውና ስለዚህ እሱን ጠላት አድርጋችሁ ያዙት። ሰይጣን ተከታዮቹን የሚጠራው ከእሳት ጓዶች እንዲሆኑ ብቻ ነው።
٧ الَّذِينَ كَفَرُوا لَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ ۖ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ لَهُمْ مَغْفِرَةٌ وَأَجْرٌ كَبِيرٌ
7 እነዚያ በአላህ የካዱት ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው። እነዚያም በአላህ ያመኑትና በጎ ስራዎችንም የሰሩት ሁሉ ለእነርሱ በአላህ ዘንድ ምህረትና ታላቅ ምንዳ አለላቸው።
٨ أَفَمَنْ زُيِّنَ لَهُ سُوءُ عَمَلِهِ فَرَآهُ حَسَنًا ۖ فَإِنَّ اللَّهَ يُضِلُّ مَنْ يَشَاءُ وَيَهْدِي مَنْ يَشَاءُ ۖ فَلَا تَذْهَبْ نَفْسُكَ عَلَيْهِمْ حَسَرَاتٍ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ بِمَا يَصْنَعُونَ
8 መጥፎ ሥራው የተሸለመለትና መልካም አድርጎ ያየው ሰው (አላህ እንዳቀናው ሰው ነውን?) አላህም የሚሻውን ሰው ያጠምማል። የሚሻውንም ያቀናል። ስለዚህ በእነርሱ ላይ (ባለመቅናታቸው) ስለመቆላጨት ነፍስህ አትጥፋ። አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነውና።
٩ وَاللَّهُ الَّذِي أَرْسَلَ الرِّيَاحَ فَتُثِيرُ سَحَابًا فَسُقْنَاهُ إِلَىٰ بَلَدٍ مَيِّتٍ فَأَحْيَيْنَا بِهِ الْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَا ۚ كَذَٰلِكَ النُّشُورُ
9 አላህም ያ ንፋሶችን የላከ ነው። ከዚያም ዳመናዎችን ትቀሰቅሳለች። ወደ ሙት (ድርቅ) አገርም እንነዳዋለን። በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው እናደርጋታለን። ሙታንንም መቀስቀስ ልክ እንደዚሁ ነው።
١٠ مَنْ كَانَ يُرِيدُ الْعِزَّةَ فَلِلَّهِ الْعِزَّةُ جَمِيعًا ۚ إِلَيْهِ يَصْعَدُ الْكَلِمُ الطَّيِّبُ وَالْعَمَلُ الصَّالِحُ يَرْفَعُهُ ۚ وَالَّذِينَ يَمْكُرُونَ السَّيِّئَاتِ لَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ ۖ وَمَكْرُ أُولَٰئِكَ هُوَ يَبُورُ
10 ማሸነፍን የሚፈልግ ሰው አሸናፊነት ለአላህ ብቻ ነው። (እርሱን በመገዛት ይፈልገው)። መልካም ንግግር ወደ እርሱ (ወደ አላህ) ይወጣል። በጎ ስራም ከፍ ያደርገዋል። እነዚያ መጥፎ ስራዎችን የሚዶልቱ ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አለባቸው ። የእነዚያም ተንኮል እርሱ ይጠፋል።
١١ وَاللَّهُ خَلَقَكُمْ مِنْ تُرَابٍ ثُمَّ مِنْ نُطْفَةٍ ثُمَّ جَعَلَكُمْ أَزْوَاجًا ۚ وَمَا تَحْمِلُ مِنْ أُنْثَىٰ وَلَا تَضَعُ إِلَّا بِعِلْمِهِ ۚ وَمَا يُعَمَّرُ مِنْ مُعَمَّرٍ وَلَا يُنْقَصُ مِنْ عُمُرِهِ إِلَّا فِي كِتَابٍ ۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ
11 አላህም ከአፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ፈጠራችሁ። ከዚያም ጥንዶች አደረጋችሁ። የትኛዋም ሴት አታረግዝም አትወልድምም በእውቀቱ ቢሆን እንጂ። እድሜው ከሚረዝምለትም አንድም አይረዝምለትም ከእድሜዉም አይጎድልበትም በመጽሀፉ ውስጥ ያለ ቢሆን እንጂ። ይህ በአላህ ላይ ገር ነው።
١٢ وَمَا يَسْتَوِي الْبَحْرَانِ هَٰذَا عَذْبٌ فُرَاتٌ سَائِغٌ شَرَابُهُ وَهَٰذَا مِلْحٌ أُجَاجٌ ۖ وَمِنْ كُلٍّ تَأْكُلُونَ لَحْمًا طَرِيًّا وَتَسْتَخْرِجُونَ حِلْيَةً تَلْبَسُونَهَا ۖ وَتَرَى الْفُلْكَ فِيهِ مَوَاخِرَ لِتَبْتَغُوا مِنْ فَضْلِهِ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
12 ሁለቱ ባህሮች አይስተካከሉም ይህ ጣፋጭ፤ ጥምን ቆራጭ መጠጡ በገር ተዋጭ ነው። ይህኛው ደግሞ ጨው መርጋጋ ነው። ከሁሉም እርጥብ ስጋን ትበላላችሁ። የምትለብሷትንም ጌጥ ታወጣላችሁ። ከችሮታው ልትፈልጉና ልታመሰግኑትም መርከቦችን በእርሱ ውስጥ ውሃውን ቀዳጆች ሆነው ሲንሻለሉ ታያለህ።
١٣ يُولِجُ اللَّيْلَ فِي النَّهَارِ وَيُولِجُ النَّهَارَ فِي اللَّيْلِ وَسَخَّرَ الشَّمْسَ وَالْقَمَرَ كُلٌّ يَجْرِي لِأَجَلٍ مُسَمًّى ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ لَهُ الْمُلْكُ ۚ وَالَّذِينَ تَدْعُونَ مِنْ دُونِهِ مَا يَمْلِكُونَ مِنْ قِطْمِيرٍ
13 ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል። ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል። ጸሀይንና ጨረቃንም ገራ። ሁሉም እስከ ተወሰነለት ጊዜ ድረስ ይሮጣል ። ይህን የሚያደርገው ጌታችሁ አላህ ብቻ ነው ። ንግስናው የእሱ ብቻ ነው። እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን ያህል እንኳን አይኖራቸዉም።
١٤ إِنْ تَدْعُوهُمْ لَا يَسْمَعُوا دُعَاءَكُمْ وَلَوْ سَمِعُوا مَا اسْتَجَابُوا لَكُمْ ۖ وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ يَكْفُرُونَ بِشِرْكِكُمْ ۚ وَلَا يُنَبِّئُكَ مِثْلُ خَبِيرٍ
14 ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም። ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ ባልመለሱላችሁም ነበር። በትንሳኤም ቀን እነርሱን በአላህ ማጋራታችሁን ይክዳሉ። እንደ ውስጠ አዋቂው አላህ ማንም አይነግርህም።
١٥ يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنْتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ ۖ وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ
15 እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ ሁል ጊዜ ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ። አላህም እርሱ ተብቃቂውና ምስጉኑ ነው።
١٦ إِنْ يَشَأْ يُذْهِبْكُمْ وَيَأْتِ بِخَلْقٍ جَدِيدٍ
16 (አላህ) ቢሻ ያስወግዳችሁና አዲስን ፍጡር ያመጣል (ይፈጥራል)።
١٧ وَمَا ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ بِعَزِيزٍ
17 ይህም በአላህ ላይ ምንም አስቸጋሪ አይደለም።
١٨ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ۚ وَإِنْ تَدْعُ مُثْقَلَةٌ إِلَىٰ حِمْلِهَا لَا يُحْمَلْ مِنْهُ شَيْءٌ وَلَوْ كَانَ ذَا قُرْبَىٰ ۗ إِنَّمَا تُنْذِرُ الَّذِينَ يَخْشَوْنَ رَبَّهُمْ بِالْغَيْبِ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ ۚ وَمَنْ تَزَكَّىٰ فَإِنَّمَا يَتَزَكَّىٰ لِنَفْسِهِ ۚ وَإِلَى اللَّهِ الْمَصِيرُ
18 ኃጢአትን ተሸካሚም ነፍስ የሌላውን ሸክም አትሸከምም። የራሷ ወንጀል የከበዳትም ነፍስ እርዳታ እንዲደረግላት ብትጠራ ተጠሪው የቅርብ ዝምድና ባለቤት ቢሆንም እንኳን ከእርሷ አንድን ነገር የሚሸከምላት አታገኝም። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምታስጠነቅቀው እነዚያን ጌታቸውን፤ በሩቅ የሚፈሩትን ሶላትንም አስተካክለው የሚሰግዱትን ብቻ ነው። ከወንጀልም የተጥራራ ሁሉ የሚጥራራው ለራሱ ብቻ ነው። መመለሻዉም ወደ አላህ ብቻ ነው።
١٩ وَمَا يَسْتَوِي الْأَعْمَىٰ وَالْبَصِيرُ
19 እውርና የሚያይ አይስተካከሉም፤
٢٠ وَلَا الظُّلُمَاتُ وَلَا النُّورُ
20 ጨለማዎችና ብርሃንም፤
٢١ وَلَا الظِّلُّ وَلَا الْحَرُورُ
21 ጥላና ሐሩርም።
٢٢ وَمَا يَسْتَوِي الْأَحْيَاءُ وَلَا الْأَمْوَاتُ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُسْمِعُ مَنْ يَشَاءُ ۖ وَمَا أَنْتَ بِمُسْمِعٍ مَنْ فِي الْقُبُورِ
22 ህያውና ሙታንም አይስተካከሉም። አላህ የሚሻውን ሰው ያሰማል። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ግን በመቃብር ውስጥ ያሉትን አሰሚ አይደለህም።
٢٣ إِنْ أَنْتَ إِلَّا نَذِيرٌ
23 አንተ አስጠንቃቂ እንጂ ሌላ አይደለህም።
٢٤ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ بِالْحَقِّ بَشِيرًا وَنَذِيرًا ۚ وَإِنْ مِنْ أُمَّةٍ إِلَّا خَلَا فِيهَا نَذِيرٌ
24 እኛ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን በእውነቱ መምሪያ ላክንህ። ማንኛይቱም ህዝብ በውስጧ አስፈራሪ ያላለፈባት የለችም።
٢٥ وَإِنْ يُكَذِّبُوكَ فَقَدْ كَذَّبَ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ جَاءَتْهُمْ رُسُلُهُمْ بِالْبَيِّنَاتِ وَبِالزُّبُرِ وَبِالْكِتَابِ الْمُنِيرِ
25 (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቢያስተባብሉህም ከእነዚህ ከበፊታቸው የነበሩትም ህዝቦች በእርግጥ ነብያትን አስተባብለዋል። መልዕክተኞቻቸው በግልጽ ማስረጃዎች፣ በጹሁፎችም አብራሪ በሆነ መጽሐፍም መጥተዋቸዋል።
٢٦ ثُمَّ أَخَذْتُ الَّذِينَ كَفَرُوا ۖ فَكَيْفَ كَانَ نَكِيرِ
26 ከዚያም እነዚያን የካዱትን ቀጣኋቸው። ቅጣቴም እንዴት ነበር! (በስፍራው ነው የተገባ ነበር)።
٢٧ أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ أَنْزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَخْرَجْنَا بِهِ ثَمَرَاتٍ مُخْتَلِفًا أَلْوَانُهَا ۚ وَمِنَ الْجِبَالِ جُدَدٌ بِيضٌ وَحُمْرٌ مُخْتَلِفٌ أَلْوَانُهَا وَغَرَابِيبُ سُودٌ
27 (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ከሰማይ ውሃን ማውረዱን አላየህምን? በእርሱም መልካቸው የተለያዩ ፍሬዎችን አወጣን። ከጋራዎችም መልካቸው የተለያዩ ነጮችም፤ ቀዮችም፤ በጣም ጥቁሮችም የሆኑ መንገዶች አሉ።
٢٨ وَمِنَ النَّاسِ وَالدَّوَابِّ وَالْأَنْعَامِ مُخْتَلِفٌ أَلْوَانُهُ كَذَٰلِكَ ۗ إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ غَفُورٌ
28 ከሰዎችም፤ ከተንቀሳቃሾችም፤ ከቤት እንስሳዎችም እንደዚሁ መልኮቻቸው የተለያዩ አሉ። አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት አዋቂዎቹ ብቻ ናቸው። አላህ አሸናፊና መሃሪ ነው።
٢٩ إِنَّ الَّذِينَ يَتْلُونَ كِتَابَ اللَّهِ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَأَنْفَقُوا مِمَّا رَزَقْنَاهُمْ سِرًّا وَعَلَانِيَةً يَرْجُونَ تِجَارَةً لَنْ تَبُورَ
29 እነዚያ የአላህን መጽሐፍ የሚያነቡ፣ ሶላትን አስተካክለው የሰገዱ፤ ከሰጠናቸዉም ሲሳይ በምስጢርም ሆነ በግልጽ የለገሱ የማትከስርን ንግድ ተስፋ ያደርጋሉ።
٣٠ لِيُوَفِّيَهُمْ أُجُورَهُمْ وَيَزِيدَهُمْ مِنْ فَضْلِهِ ۚ إِنَّهُ غَفُورٌ شَكُورٌ
30 ምንዳዎቻቸውን ሊሞላላቸው ከችሮታዉም ሊጨምርላቸው ተስፋ ያደርጋሉ። እርሱ በጣም መሃሪና አመስጋኝ ነውና።
٣١ وَالَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ مِنَ الْكِتَابِ هُوَ الْحَقُّ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ بِعِبَادِهِ لَخَبِيرٌ بَصِيرٌ
31 (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያ ከመጽሐፉ ወደ አንተ ያወረድነው ከበፊቱ ላለው አረጋጋጭ ሲሆን እርሱ እውነት ነው። አላህ በእርግጥ በባሮቹ ውስጠ አዋቂና ተመልካች ነው።
٣٢ ثُمَّ أَوْرَثْنَا الْكِتَابَ الَّذِينَ اصْطَفَيْنَا مِنْ عِبَادِنَا ۖ فَمِنْهُمْ ظَالِمٌ لِنَفْسِهِ وَمِنْهُمْ مُقْتَصِدٌ وَمِنْهُمْ سَابِقٌ بِالْخَيْرَاتِ بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَضْلُ الْكَبِيرُ
32 ከዚያ እነዚያ ከባሮቻችን የመረጥናቸውን መጽሐፉን አወረስናቸው ። ከእነርሱም ነፍሱን በዳይ አለ። ከእነርሱም መካከለኛ አለ። ከእነርሱም በአላህ ፈቃድ በበጎ ስራዎች ቀዳሚ አለ። ያንኑ ማውረስ እርሱ ታላቅ ችሮታ ነው።
٣٣ جَنَّاتُ عَدْنٍ يَدْخُلُونَهَا يُحَلَّوْنَ فِيهَا مِنْ أَسَاوِرَ مِنْ ذَهَبٍ وَلُؤْلُؤًا ۖ وَلِبَاسُهُمْ فِيهَا حَرِيرٌ
33 የመኖሪያ ገነቶችን በውስጧ የወርቅ አንባሮችን ሉልንም የሚሸለሙ ሆነው ይገቡበታል። በእርሷ ውስጥ አልባሳታቸዉም ሀር ነው።
٣٤ وَقَالُوا الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي أَذْهَبَ عَنَّا الْحَزَنَ ۖ إِنَّ رَبَّنَا لَغَفُورٌ شَكُورٌ
34 ይላሉም «ምስጋና ሁሉ ለዚያ ከእኛ ላይ ሐዘንን ላስወገደልን ለአላህ ይገባው። ጌታችን በጣም መሃሪና አመስጋኝ ነውና።
٣٥ الَّذِي أَحَلَّنَا دَارَ الْمُقَامَةِ مِنْ فَضْلِهِ لَا يَمَسُّنَا فِيهَا نَصَبٌ وَلَا يَمَسُّنَا فِيهَا لُغُوبٌ
35 እርሱም ያ ከችሮታው የዘላለም መኖሪያን አገር ያሰፈረን ነው። በእርሷም ውስጥ መከራ አይነካንም። በእርሷም ውስጥ ድካም አይነካንም።»
٣٦ وَالَّذِينَ كَفَرُوا لَهُمْ نَارُ جَهَنَّمَ لَا يُقْضَىٰ عَلَيْهِمْ فَيَمُوتُوا وَلَا يُخَفَّفُ عَنْهُمْ مِنْ عَذَابِهَا ۚ كَذَٰلِكَ نَجْزِي كُلَّ كَفُورٍ
36 እነዚያ በአላህ የካዱት ለእነርሱ የገሀነም እሳት አለላቸው። ይሞቱ ዘንድም በእነርሱ ላይ ሞት አይፈረድም። ከቅጣቷም ከእነርሱ አይቀለልላቸዉም። ልክ እንደዚሁ ከሓዲያንን ሁሉ እንመነዳለን።
٣٧ وَهُمْ يَصْطَرِخُونَ فِيهَا رَبَّنَا أَخْرِجْنَا نَعْمَلْ صَالِحًا غَيْرَ الَّذِي كُنَّا نَعْمَلُ ۚ أَوَلَمْ نُعَمِّرْكُمْ مَا يَتَذَكَّرُ فِيهِ مَنْ تَذَكَّرَ وَجَاءَكُمُ النَّذِيرُ ۖ فَذُوقُوا فَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ نَصِيرٍ
37 እነርሱም በእርሷ ውስጥ እርዳታን በመፈለግ በኃይል ይጮሃሉ። «ጌታችን ሆይ! ከእዚያ እንሠራው ከነበርነው ሌላ በጎ ሥራን እንሠራ ዘንድ አውጣን» (ይላሉ)። «በእርሱ ውስጥ ያስታወሰ ሰው የሚገሰጽበትን እድሜ አላቆየናችሁምን? አስጠንቃቂዉም መጥቶላችኋል። (አስተባብላችኋልም)። ስለዚህ ቅመሱ። ለበደለኞችም ምንም ረዳት የላቸዉም» ይባላሉ።
٣٨ إِنَّ اللَّهَ عَالِمُ غَيْبِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ إِنَّهُ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ
38 አላህ የሰማያትንና የምድርን ምስጢር በእርግጥ አዋቂ ነው። እርሱ በልቦች ውስጥ ያለን ሁሉ እንኳ አዋቂ ነውና።
٣٩ هُوَ الَّذِي جَعَلَكُمْ خَلَائِفَ فِي الْأَرْضِ ۚ فَمَنْ كَفَرَ فَعَلَيْهِ كُفْرُهُ ۖ وَلَا يَزِيدُ الْكَافِرِينَ كُفْرُهُمْ عِنْدَ رَبِّهِمْ إِلَّا مَقْتًا ۖ وَلَا يَزِيدُ الْكَافِرِينَ كُفْرُهُمْ إِلَّا خَسَارًا
39 (ሰዎች ሆይ!) እርሱ ያ በምድር ውስጥ ምትኮች ያደረጋችሁ ነው። የካደም ክህደቱ በእርሱው ላይ ብቻ ነው። ከሓዲያንም ክህደታቸው ከጌታቸው ዘንድ መጠላትን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸዉም። ከሓዲያንም ክህደታቸው ክስረትን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸዉም።
٤٠ قُلْ أَرَأَيْتُمْ شُرَكَاءَكُمُ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ أَرُونِي مَاذَا خَلَقُوا مِنَ الْأَرْضِ أَمْ لَهُمْ شِرْكٌ فِي السَّمَاوَاتِ أَمْ آتَيْنَاهُمْ كِتَابًا فَهُمْ عَلَىٰ بَيِّنَتٍ مِنْهُ ۚ بَلْ إِنْ يَعِدُ الظَّالِمُونَ بَعْضُهُمْ بَعْضًا إِلَّا غُرُورًا
40 (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን ተጋሪዎቻችሁ አያችሁን? ከምድር ምንን እንደ ፈጠሩ አሳዩኝ? ወይስ ለእነርሱ በሰማያት ውስጥ ሽርክና አላቸውን? ወይስ ለእነርሱ መፅሀፍ ሰጠናቸውና ከእርሱ በግልፅ አስረጂ ላይ ናቸውን? አይደለም በደለኞች ከፊላቸው ከፊሉን ማታለልን እንጂ አይቀጥሩም» በላቸው።
٤١ إِنَّ اللَّهَ يُمْسِكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ أَنْ تَزُولَا ۚ وَلَئِنْ زَالَتَا إِنْ أَمْسَكَهُمَا مِنْ أَحَدٍ مِنْ بَعْدِهِ ۚ إِنَّهُ كَانَ حَلِيمًا غَفُورًا
41 አላህ ሰማያትንና ምድርን እንዳይወገዱ ይይዛቸዋል። ቢወገዱም ከእርሱ ሌላ አንድም የሚይዛቸው የለም። እነሆ እርሱ ታጋሽና መሃሪ ነውና።
٤٢ وَأَقْسَمُوا بِاللَّهِ جَهْدَ أَيْمَانِهِمْ لَئِنْ جَاءَهُمْ نَذِيرٌ لَيَكُونُنَّ أَهْدَىٰ مِنْ إِحْدَى الْأُمَمِ ۖ فَلَمَّا جَاءَهُمْ نَذِيرٌ مَا زَادَهُمْ إِلَّا نُفُورًا
42 አስፈራሪም ቢመጣላቸው ከህዝቦች ሁሉ ከአንደኛዋ ይበልጥ የተመሩ ሊሆኑ የመሃላቸውን ዲካ አድርሰው በአላህ ማሉ። አስፈራሪም በመጣላቸው ጊዜ መበርገግን እንጂ ሌላ አልጨመረላቸዉም።
٤٣ اسْتِكْبَارًا فِي الْأَرْضِ وَمَكْرَ السَّيِّئِ ۚ وَلَا يَحِيقُ الْمَكْرُ السَّيِّئُ إِلَّا بِأَهْلِهِ ۚ فَهَلْ يَنْظُرُونَ إِلَّا سُنَّتَ الْأَوَّلِينَ ۚ فَلَنْ تَجِدَ لِسُنَّتِ اللَّهِ تَبْدِيلًا ۖ وَلَنْ تَجِدَ لِسُنَّتِ اللَّهِ تَحْوِيلًا
43 በምድር ላይ ኩራትንና በክፉ ተንኮል መዶለትንም እንጂ አልጨመረላቸዉም። ክፉ ተንኮልም በባለቤቱ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይሰፍርም። የቀድሞዎቹን ደንብ እንጂ ይጠብቃሉን? በመሆኑም ለአላህ ደንብ መለወጥን አታገኝም፤ ለአላህ ደንብም መዛወርን (መቀየር) አታገኝም።
٤٤ أَوَلَمْ يَسِيرُوا فِي الْأَرْضِ فَيَنْظُرُوا كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ وَكَانُوا أَشَدَّ مِنْهُمْ قُوَّةً ۚ وَمَا كَانَ اللَّهُ لِيُعْجِزَهُ مِنْ شَيْءٍ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ ۚ إِنَّهُ كَانَ عَلِيمًا قَدِيرًا
44 በምድር ላይ አይሄዱምና የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ አይመለከቱምን? ከእነርሱም በኃይል የበረቱ ነበሩ። አላህም በሰማያትም ሆነ በምድር ውስጥ ምንም ነገር የሚያቅተው አይደለም። እርሱ ሁሉን አዋቂና በሁሉ ላይ ቻይ ነውና።
٤٥ وَلَوْ يُؤَاخِذُ اللَّهُ النَّاسَ بِمَا كَسَبُوا مَا تَرَكَ عَلَىٰ ظَهْرِهَا مِنْ دَابَّةٍ وَلَٰكِنْ يُؤَخِّرُهُمْ إِلَىٰ أَجَلٍ مُسَمًّى ۖ فَإِذَا جَاءَ أَجَلُهُمْ فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِعِبَادِهِ بَصِيرًا
45 አላህ ሰዎችን በሰሩት ኃጢአት ሁሉ ቢቀጣ ኖሮ በምድር ወለል ላይ ምንንም ተንቀሳቃሽ ባልተወ ነበር። ግን እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ ያቆያቸዋል። ጊዜያቸዉም በመጣ ወቅት (በኃጢአታቸው ይቀጣቸዋል)። አላህ በባሮቹ ሁኔታ ሁሉ ተመልካች ነውና።