وَالصَّافَّاتِ صَفًّا
መሰለፍን በሚሰለፉት፤
القرآن الكريمAfrica Academy
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።
وَالصَّافَّاتِ صَفًّا
መሰለፍን በሚሰለፉት፤
فَالزَّاجِرَاتِ زَجْرًا
(ደመና) መንዳትን በሚነዱት፤
فَالتَّالِيَاتِ ذِكْرًا
ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ።
إِنَّ إِلَٰهَكُمْ لَوَاحِدٌ
አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ብቻ ነው።
رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا وَرَبُّ الْمَشَارِقِ
እርሱ ያ በሰማያትና በምድር በመካከላቸው ያለውም ፍጡር ሁሉ ጌታ ነው። የምስራቆችም ጌታ ነው።
إِنَّا زَيَّنَّا السَّمَاءَ الدُّنْيَا بِزِينَةٍ الْكَوَاكِبِ
እኛ ቅርቢቱን ሰማይ በከዋክብት ጌጥ አጌጥናት (አስዋብናት)።
وَحِفْظًا مِنْ كُلِّ شَيْطَانٍ مَارِدٍ
አመጸኛ ከሆነ ሰይጣንም ሁሉ መጠበቅን ጠበቅናት።
لَا يَسَّمَّعُونَ إِلَى الْمَلَإِ الْأَعْلَىٰ وَيُقْذَفُونَ مِنْ كُلِّ جَانِبٍ
ወደ ላይኛው ሰራዊት አያደምጡም፤ ከየአቅጣጫውም ሁሉ ችቦ ይጣልባቸዋል፤ (ይቀጠቀጣሉ)።
دُحُورًا ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ وَاصِبٌ
የሚባረሩ ሲሆኑ (ይጣልባቸዋል)፤ ለእነርሱም ዘውታሪ ቅጣት አለባቸው።
إِلَّا مَنْ خَطِفَ الْخَطْفَةَ فَأَتْبَعَهُ شِهَابٌ ثَاقِبٌ
ንጥቂያን የነጠቀ ወዲያውኑም አብሪ ኮከብ የተከተለው ሲቀር (እርሱ ይሰማዋል)።
فَاسْتَفْتِهِمْ أَهُمْ أَشَدُّ خَلْقًا أَمْ مَنْ خَلَقْنَا ۚ إِنَّا خَلَقْنَاهُمْ مِنْ طِينٍ لَازِبٍ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጠይቃቸውም፤ እነርሱ በአፈጣጠር ይበልጥ የበረቱ ናቸውን? ወይስ እኛ (ከእነርሱ በፊት) የፈጠርነው (ሌላው ታላቅ) ፍጡር? እኛ ከሚጣበቅ ጭቃ ፈጠርናቸው።
بَلْ عَجِبْتَ وَيَسْخَرُونَ
ይልቁንም ማስተባበላቸው አስደነቀህ፤ በመደነቅህም ይሳለቃሉ።
وَإِذَا ذُكِّرُوا لَا يَذْكُرُونَ
በተገሰጹም ጊዜ አይገሰጹም።
وَإِذَا رَأَوْا آيَةً يَسْتَسْخِرُونَ
ተዓምርንም ባዩ ጊዜ ለመሳለቅ ይጣጣራሉ።
وَقَالُوا إِنْ هَٰذَا إِلَّا سِحْرٌ مُبِينٌ
አሉም: «ይህ ግልጽ ድግምት እንጂ ሌላ አይደለም።
أَإِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَامًا أَإِنَّا لَمَبْعُوثُونَ
«በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ የምንቀሰቀስ ነን?
أَوَآبَاؤُنَا الْأَوَّلُونَ
«የቀድሞዎቹ አባቶቻችንም እንደዚሁ ይቀሰቀሳሉን?» (ይላሉ።)
قُلْ نَعَمْ وَأَنْتُمْ دَاخِرُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አዎን! እናንተ ወራዶች ሆናችሁ (ትነሳላችሁ)።» በላቸው።
فَإِنَّمَا هِيَ زَجْرَةٌ وَاحِدَةٌ فَإِذَا هُمْ يَنْظُرُونَ
እርሷም አንዲት ጩኸት ብቻ ናት። እነርሱም ወዲያውኑ ምን እንደሚፈጸምባቸው ያያሉ።
وَقَالُوا يَا وَيْلَنَا هَٰذَا يَوْمُ الدِّينِ
«ዋ ጥፋታችን! ይህ የፍርዱ ቀን ነው።» (ይላሉም)
هَٰذَا يَوْمُ الْفَصْلِ الَّذِي كُنْتُمْ بِهِ تُكَذِّبُونَ
«ይህ ያ በእርሱ ታስተባብሉት የነበራችሁት መለያው ቀን ነው።» ይባላሉ።
احْشُرُوا الَّذِينَ ظَلَمُوا وَأَزْوَاجَهُمْ وَمَا كَانُوا يَعْبُدُونَ
(ለመላዕክቶችም) «እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ከአላህ ሌላ ይገዟቸው የነበሩትንም (ጣዖታት) በአንድ ሰብስቡ።
مِنْ دُونِ اللَّهِ فَاهْدُوهُمْ إِلَىٰ صِرَاطِ الْجَحِيمِ
ከአላህ ውጭ (ይገዟቸው የነበሩትን ሰብስቡ)። ከዚያም ወደ ገሀነም መንገድ ምሯቸው።
وَقِفُوهُمْ ۖ إِنَّهُمْ مَسْئُولُونَ
«እነርሱ ተጠያቂዎች ናቸውና አቁሟቸዉም።» (ይባላል።)
مَا لَكُمْ لَا تَنَاصَرُونَ
ለነርሱም «ምን ሆናችሁ ነው የማትረዳዱት?» ይባላሉ።
بَلْ هُمُ الْيَوْمَ مُسْتَسْلِمُونَ
በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ (ማምለጫ የሌላቸው ወራዳዎች) ናቸው።
وَأَقْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ يَتَسَاءَلُونَ
እርስ በራሳቸውም የሚወቃቀሱም ሆነው ይመጣሉ።
قَالُوا إِنَّكُمْ كُنْتُمْ تَأْتُونَنَا عَنِ الْيَمِينِ
(ተከታዮቹ ለአስከታዮቻቸው) «እናንተ በጉልበት ትመጡብን ነበር» ይላሉ።
قَالُوا بَلْ لَمْ تَكُونُوا مُؤْمِنِينَ
(አስከታዮቹም) ይላሉ፡- «አይደለም ፈጽሞ አማኞች አልነበራችሁም።
وَمَا كَانَ لَنَا عَلَيْكُمْ مِنْ سُلْطَانٍ ۖ بَلْ كُنْتُمْ قَوْمًا طَاغِينَ
«ለእኛም በናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልነበረንም። በእርግጥ እናንተ ጠማሞች ህዝቦች ነበራችሁና ነው እንጂ።
فَحَقَّ عَلَيْنَا قَوْلُ رَبِّنَا ۖ إِنَّا لَذَائِقُونَ
«በእኛም ላይ የጌታችን ቃል ተረጋገጠ፤ እኛ በእርግጥ (ቅጣቱን) ቀማሾች ነን።
فَأَغْوَيْنَاكُمْ إِنَّا كُنَّا غَاوِينَ
«እኛ ጠማሞች ስለ ነበርን ወደ ጥመት ጠራናችሁም።» ይላሉ።
فَإِنَّهُمْ يَوْمَئِذٍ فِي الْعَذَابِ مُشْتَرِكُونَ
ስለዚህ እነርሱ በዚያ ቀን በቅጣቱ ተጋሪዎች ናቸው።
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَفْعَلُ بِالْمُجْرِمِينَ
እኛ በአመጸኞች ሁሉ እንደዚሁ እንሰራለን።
إِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ يَسْتَكْبِرُونَ
እነርሱ «ከአላህ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም» በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበሩ።
وَيَقُولُونَ أَئِنَّا لَتَارِكُو آلِهَتِنَا لِشَاعِرٍ مَجْنُونٍ
«እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው ነን እንዴ?» ይሉ ነበር።
بَلْ جَاءَ بِالْحَقِّ وَصَدَّقَ الْمُرْسَلِينَ
አይደለም እውነቱን ሃይማኖት አመጣ፤ መልዕክተኞቹንም እውነተኝነታቸውን አረጋገጠ።
إِنَّكُمْ لَذَائِقُو الْعَذَابِ الْأَلِيمِ
እናንተ አሳማሚውን ቅጣት እርግጥ ቀማሾች ናችሁ።
وَمَا تُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كُنْتُمْ تَعْمَلُونَ
ትሰሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም።
إِلَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ
ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ቅጣትን አይቀምሱም።
أُولَٰئِكَ لَهُمْ رِزْقٌ مَعْلُومٌ
እነዚያ ለእነርሱ የታወቀ ሲሳይ አለላቸው።
فَوَاكِهُ ۖ وَهُمْ مُكْرَمُونَ
ፍራፍሬዎች (አሉላቸው) እነርሱም የተከበሩ ናቸው።
فِي جَنَّاتِ النَّعِيمِ
በድሎት ገነቶች ውስጥ።
عَلَىٰ سُرُرٍ مُتَقَابِلِينَ
ፊት ለፊት የሚተያዩ ሲሆኑ በአልጋዎች ላይ ይንፈላሰሳሉ።
يُطَافُ عَلَيْهِمْ بِكَأْسٍ مِنْ مَعِينٍ
ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዙ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል።
بَيْضَاءَ لَذَّةٍ لِلشَّارِبِينَ
ነጭ ለጠጪዎች ጣፋጭ ከሆነች፤
لَا فِيهَا غَوْلٌ وَلَا هُمْ عَنْهَا يُنْزَفُونَ
በእርሷ ውስጥም የራስ ምታት የለባትም። እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም።
وَعِنْدَهُمْ قَاصِرَاتُ الطَّرْفِ عِينٌ
እነርሱ ዘንድ ዓይናቸውን በባሎቻቸው ላይ ብቻ አሳጣሪዎች የሆኑ ዓይናማ ሴቶች አሉ።
كَأَنَّهُنَّ بَيْضٌ مَكْنُونٌ
እነርሱ ልክ የተሸፈነ (የሰጎን) እንቁላል ይመስላሉ።
فَأَقْبَلَ بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ يَتَسَاءَلُونَ
የሚጠያያቁም ሆነው ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይመጣሉ።
قَالَ قَائِلٌ مِنْهُمْ إِنِّي كَانَ لِي قَرِينٌ
ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ (እንዲህ) ይላል: «እኔ ጓደኛ ነበረኝ።
يَقُولُ أَإِنَّكَ لَمِنَ الْمُصَدِّقِينَ
(እንዲህ) የሚል: ‹በእርግጥ አንተ ከሚያምኑት ነህን?
أَإِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَامًا أَإِنَّا لَمَدِينُونَ
«በሞትንና ዐፈርና አጥንቶችም በሆንን ጊዜ እኛ በእርግጥ እኛ እንመረመራለን?።» የሚልም።
قَالَ هَلْ أَنْتُمْ مُطَّلِعُونَ
እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል።
فَاطَّلَعَ فَرَآهُ فِي سَوَاءِ الْجَحِيمِ
ይመለከታልም በገሀነም መካከልም ጓደኛውን ያየዋል።
قَالَ تَاللَّهِ إِنْ كِدْتَ لَتُرْدِينِ
ይላል «በአላህ እምላለሁ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር።
وَلَوْلَا نِعْمَةُ رَبِّي لَكُنْتُ مِنَ الْمُحْضَرِينَ
«የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር።» (ይላል)
أَفَمَا نَحْنُ بِمَيِّتِينَ
(የገነት ሰዎች ይላሉ)፡«እኛ (ከእንግዲህ) የምንሞት አይደለንም አይደል?»
إِلَّا مَوْتَتَنَا الْأُولَىٰ وَمَا نَحْنُ بِمُعَذَّبِينَ
«የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር እኛም የምንቀጣ አይደለንም» ይላሉ።
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ
ይህ ለገነት ሰዎች የተወሳው እርሱ በእርግጥ ታላቅ እድል ነው።
لِمِثْلِ هَٰذَا فَلْيَعْمَلِ الْعَامِلُونَ
ለዚህ ብጤ ሰሪዎች ሁሉ ይስሩ።
أَذَٰلِكَ خَيْرٌ نُزُلًا أَمْ شَجَرَةُ الزَّقُّومِ
በመስተንግዶነት ይህ ይበልጣልን? ወይስ የዘቁም ዛፍ?
إِنَّا جَعَلْنَاهَا فِتْنَةً لِلظَّالِمِينَ
እኛ ለበዳዮች ፈተና አድርገናታል።
إِنَّهَا شَجَرَةٌ تَخْرُجُ فِي أَصْلِ الْجَحِيمِ
እርሷ ከገሀነም አዘቅት ውስጥ የምትወጣ ዛፍ ናት፤
طَلْعُهَا كَأَنَّهُ رُءُوسُ الشَّيَاطِينِ
እንቡጧ ልክ የሰይጣናት ራሶች ይመስላል።
فَإِنَّهُمْ لَآكِلُونَ مِنْهَا فَمَالِئُونَ مِنْهَا الْبُطُونَ
እነርሱ ከእርሷ በይዎች ናቸው። ሆዶችንም ከእርሷ ሞይዎች ናቸው።
ثُمَّ إِنَّ لَهُمْ عَلَيْهَا لَشَوْبًا مِنْ حَمِيمٍ
ከዚያ ለእነርሱ በእርሷ ላይ ከፈላ ውሃ ቅልቅልን መጠጥ አላቸው።
ثُمَّ إِنَّ مَرْجِعَهُمْ لَإِلَى الْجَحِيمِ
ከዚያም መመለሻቸው ወደ ተጋጋመች እሳት ነው።
إِنَّهُمْ أَلْفَوْا آبَاءَهُمْ ضَالِّينَ
እነርሱ አባቶቻቸውን የተሳሳቱ ሆነው አግኝተዋል።
فَهُمْ عَلَىٰ آثَارِهِمْ يُهْرَعُونَ
እነርሱም በፈለጎቻቸው ላይ ይገሰግሳሉና።
وَلَقَدْ ضَلَّ قَبْلَهُمْ أَكْثَرُ الْأَوَّلِينَ
ከእነርሱም በፊት የነበሩት የቀድሞዎቹ ህዝቦች አብዛሀኞቻቸው በእርግጥ ተሳስተዋል።
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا فِيهِمْ مُنْذِرِينَ
በውስጣቸዉም አስፈራሪዎችን በእርግጥ ልከናል።
فَانْظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُنْذَرِينَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የተስፈራሪዎቹም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት!
إِلَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ
ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ።
وَلَقَدْ نَادَانَا نُوحٌ فَلَنِعْمَ الْمُجِيبُونَ
ኑህም በእርግጥ ጠራን። ምንኛ ያማርን ምላሽ ሰጪ ነን?
وَنَجَّيْنَاهُ وَأَهْلَهُ مِنَ الْكَرْبِ الْعَظِيمِ
እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳንን።
وَجَعَلْنَا ذُرِّيَّتَهُ هُمُ الْبَاقِينَ
ዘሮቹንም እነርሱን ብቻ ቀሪዎች አደረግን።
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِي الْآخِرِينَ
በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ህዝቦች ውስጥ መልካምን ዝና ተውን።
سَلَامٌ عَلَىٰ نُوحٍ فِي الْعَالَمِينَ
«በዓለማት ውስጥ ሰላም በኑህ ላይ ይሁን።»
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
እኛ ልክ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን።
إِنَّهُ مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ
እርሱ ከአማኞች ባሮቻችን ነውና።
ثُمَّ أَغْرَقْنَا الْآخَرِينَ
ከዚያም ሌሎችን አሰመጥን።
وَإِنَّ مِنْ شِيعَتِهِ لَإِبْرَاهِيمَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! ) ኢብራሂምም በእርግጥ ከወገኖቹ አንዱ ነው።
إِذْ جَاءَ رَبَّهُ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ
ወደ ጌታው በቅን ልብ በመጣ ጊዜ የሆነውን (አስታውስ)።
إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِ مَاذَا تَعْبُدُونَ
ለአባቱና ለህዝቦቹ ባለ ጊዜ: «ምንን ትገዛላችሁ?
أَئِفْكًا آلِهَةً دُونَ اللَّهِ تُرِيدُونَ
«ለቅጥፈት ብላችሁ ከአላህ ሌላ አማልክትን ትሻላችሁን?
فَمَا ظَنُّكُمْ بِرَبِّ الْعَالَمِينَ
«በዓለማቱ ጌታስ ሀሳባችሁ ምንድ ነው?»
فَنَظَرَ نَظْرَةً فِي النُّجُومِ
በከዋክብት መመልከትን ተመለከተ።
فَقَالَ إِنِّي سَقِيمٌ
«እኔ በሽተኛ ነኝ» አለ።
فَتَوَلَّوْا عَنْهُ مُدْبِرِينَ
እነርሱም ከእርሱ የሸሹ ሆነው ሄዱ።
فَرَاغَ إِلَىٰ آلِهَتِهِمْ فَقَالَ أَلَا تَأْكُلُونَ
ከዚያ እሱ ወደ አማልዕክቶቻቸው ተዘነበለ፤ (እንዲህ) አለም፡- «አትበሉም እንዴ?
مَا لَكُمْ لَا تَنْطِقُونَ
«ምንም የማትናገሩበትስ ምን ምክኒያት አላችሁ?»
فَرَاغَ عَلَيْهِمْ ضَرْبًا بِالْيَمِينِ
በቀኝ (እጁ) የሚመታቸዉም ሆኖ በእነርሱ ላይ በድብቅ ተዘነበለ።
فَأَقْبَلُوا إِلَيْهِ يَزِفُّونَ
ወደ እርሱም ሰዎቹ እየሮጡ መጡ።
قَالَ أَتَعْبُدُونَ مَا تَنْحِتُونَ
አለ: «የምትጠርቡትን ትገዛላችሁን?
وَاللَّهُ خَلَقَكُمْ وَمَا تَعْمَلُونَ
«አላህ እናንተንም ሆነ የምትሰሩትን ሁሉ የፈጠረ ሲሆን» አላቸው።
قَالُوا ابْنُوا لَهُ بُنْيَانًا فَأَلْقُوهُ فِي الْجَحِيمِ
«ለእርሱም ግንብን ገንቡ በእሳት ነበልባል ውስጥ ጣሉትም።» አሉ።
فَأَرَادُوا بِهِ كَيْدًا فَجَعَلْنَاهُمُ الْأَسْفَلِينَ
በእርሱ ላይ ተንኮልን አስቡ ወራዶችም አደረግናቸው።
وَقَالَ إِنِّي ذَاهِبٌ إِلَىٰ رَبِّي سَيَهْدِينِ
አለም፡- «እኔ ወደ ጌታየ ሂያጅ ነኝ፤ በእርግጥ ይመራኛልና።
رَبِّ هَبْ لِي مِنَ الصَّالِحِينَ
«ጌታየ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ።»
فَبَشَّرْنَاهُ بِغُلَامٍ حَلِيمٍ
ታጋሽ በሆነ ልጅም አበሰርነው።
فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ السَّعْيَ قَالَ يَا بُنَيَّ إِنِّي أَرَىٰ فِي الْمَنَامِ أَنِّي أَذْبَحُكَ فَانْظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَا أَبَتِ افْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِي إِنْ شَاءَ اللَّهُ مِنَ الصَّابِرِينَ
ከእርሱ ጋርም (ለስራ) በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በህልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፤ ተመልከትም፤ ምን ትላለህ?» አለው። «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ስራ፤ አላህ ቢሻ ከታጋሾች ሆኜ ታገኘኛለህ።» አለ።
فَلَمَّا أَسْلَمَا وَتَلَّهُ لِلْجَبِينِ
ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)።
وَنَادَيْنَاهُ أَنْ يَا إِبْرَاهِيمُ
ጠራነዉም: «ኢብራሂም ሆይ!
قَدْ صَدَّقْتَ الرُّؤْيَا ۚ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
«ራዕዩን በርግጥ እውን አደረግክ።» እኛ ልክ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን።
إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ الْبَلَاءُ الْمُبِينُ
ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው።
وَفَدَيْنَاهُ بِذِبْحٍ عَظِيمٍ
በታላቅ የእርድ መስዋዕትም ቤዛ አደረግንለት።
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِي الْآخِرِينَ
በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ህዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት።
سَلَامٌ عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ
ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን።
كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
ልክ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን።
إِنَّهُ مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ
እርሱ በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ነው።
وَبَشَّرْنَاهُ بِإِسْحَاقَ نَبِيًّا مِنَ الصَّالِحِينَ
በኢስሐቅም አበሰርነው። ከመልካሞች የሆነ ነብይ ሲሆን።
وَبَارَكْنَا عَلَيْهِ وَعَلَىٰ إِسْحَاقَ ۚ وَمِنْ ذُرِّيَّتِهِمَا مُحْسِنٌ وَظَالِمٌ لِنَفْسِهِ مُبِينٌ
በእርሱና በኢስሐቅ ላይም ባረክን። ከሁለቱም ዘሮች በጎ ሰሪ አለ። ነፍሱን በግልጽ በዳይም አለ።
وَلَقَدْ مَنَنَّا عَلَىٰ مُوسَىٰ وَهَارُونَ
በሙሳና በሀሩን ላይ በእርግጥ ለገስን።
وَنَجَّيْنَاهُمَا وَقَوْمَهُمَا مِنَ الْكَرْبِ الْعَظِيمِ
እነርሱንም ሆነ ህዝቦቻቸውንም ከታላቅ ጭንቅ አዳንን።
وَنَصَرْنَاهُمْ فَكَانُوا هُمُ الْغَالِبِينَ
ረዳናቸውም፤ እነርሱ አሸናፊዎቹ ሆኑ።
وَآتَيْنَاهُمَا الْكِتَابَ الْمُسْتَبِينَ
በጣም የተብራራውንም መጽሐፍ ሰጠናቸው።
وَهَدَيْنَاهُمَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ
ቀጥተኛውንም መንገድ መራናቸው።
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِمَا فِي الْآخِرِينَ
በሁለቱም ላይ በኋለኞቹ ህዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንላቸው።
سَلَامٌ عَلَىٰ مُوسَىٰ وَهَارُونَ
ሰላም በሙሳና በሀሩን ላይ ይሁን።
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
እኛ ልክ እንደዚሁ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ እንመነዳለን።
إِنَّهُمَا مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ
ሁለቱም በእርግጥ ካመኑት ባሮቻችን ናቸው።
وَإِنَّ إِلْيَاسَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ
ኢልያስም በእርግጥ ከመልዕክተኞቹ ነው።
إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ أَلَا تَتَّقُونَ
ለህዝቦቹም ባለ ጊዜ (አስታውስ) «አላህን አትፈሩምን?
أَتَدْعُونَ بَعْلًا وَتَذَرُونَ أَحْسَنَ الْخَالِقِينَ
«በዕል የተባለውን ጣዖት ትገዛላችሁ? ከቅርፅ ሰጪዎች ሁሉ በላጭ የሆነውን አምላክ ትተዋላችሁን?
اللَّهَ رَبَّكُمْ وَرَبَّ آبَائِكُمُ الْأَوَّلِينَ
«አላህን ጌታችሁና የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁንም ጌታ ትተዋላችሁን?»
فَكَذَّبُوهُ فَإِنَّهُمْ لَمُحْضَرُونَ
አስተባበሉትም ስለዚህ እነርሱ ለቅጣት የሚጣዱ ናቸው።
إِلَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ
ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ብቻ ሲቀሩ።
وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِي الْآخِرِينَ
በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ህዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን ተውንለት።
سَلَامٌ عَلَىٰ إِلْ يَاسِينَ
ሰላም በኢልያስ ላይ ይሁን፤
إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
እኛ ልክ እንደዚሁ መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን።
إِنَّهُ مِنْ عِبَادِنَا الْمُؤْمِنِينَ
እርሱ በእርግጥ ከምዕመናን ባሮቻችን ነው።
وَإِنَّ لُوطًا لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ
ሉጥም በእርግጥ ከመልዕክተኞቹ ነው።
إِذْ نَجَّيْنَاهُ وَأَهْلَهُ أَجْمَعِينَ
እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉንም በአዳናቸው ጊዜ (የሆነዉን አስታውስ)።
إِلَّا عَجُوزًا فِي الْغَابِرِينَ
በቅጣቱ ውስጥ ከቀሪዎቹ የሆነችው አሮጊት ብቻ ስትቀር።
ثُمَّ دَمَّرْنَا الْآخَرِينَ
ከዚያም ሌሎቹን አጠፋን።
وَإِنَّكُمْ لَتَمُرُّونَ عَلَيْهِمْ مُصْبِحِينَ
(የመካ ሰዎች ሆይ!)፤ እናንተም በእነርሱ (መኖሪያዎች) ላይ ያነጋችሁ ስትሆኑ ታልፋላችሁ።
وَبِاللَّيْلِ ۗ أَفَلَا تَعْقِلُونَ
በሌሊትም ታልፋላችሁ። ልብ አታደርጉምን?
وَإِنَّ يُونُسَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ
ዩኑስም በእርግጥ ከመልዕክተኞቹ ነው።
إِذْ أَبَقَ إِلَى الْفُلْكِ الْمَشْحُونِ
ወደ ተሞላው መርከብ በኮበለለ ጊዜ አስታውስ።
فَسَاهَمَ فَكَانَ مِنَ الْمُدْحَضِينَ
እጣም ተጣጣለ፤ ከተሸነፉትም ሆነ።
فَالْتَقَمَهُ الْحُوتُ وَهُوَ مُلِيمٌ
እርሱም ተወቃሽ ሲሆን ዐሳ ነባሪው ዋጠው።
فَلَوْلَا أَنَّهُ كَانَ مِنَ الْمُسَبِّحِينَ
እርሱ ለጌታው ከአወዳሾቹ ባልሆነ ኖሮ
لَلَبِثَ فِي بَطْنِهِ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ
እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ በሆዱ ውስጥ በቆየ ነበር።
فَنَبَذْنَاهُ بِالْعَرَاءِ وَهُوَ سَقِيمٌ
እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው ባህር ዳርቻ ላይ ጣልነዉም።
وَأَنْبَتْنَا عَلَيْهِ شَجَرَةً مِنْ يَقْطِينٍ
በእርሱም ላይ በአጠገቡ ከቅል የሆነችን ዛፍ አበቀልን።
وَأَرْسَلْنَاهُ إِلَىٰ مِائَةِ أَلْفٍ أَوْ يَزِيدُونَ
ወደ መቶ ሺህ ሰዎችም ላክነው፤ ከቶውንም ይጨምራሉ።
فَآمَنُوا فَمَتَّعْنَاهُمْ إِلَىٰ حِينٍ
አመኑም። እስከ ጊዜው ድረስም አጣቀምናቸው።
فَاسْتَفْتِهِمْ أَلِرَبِّكَ الْبَنَاتُ وَلَهُمُ الْبَنُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመካን ሰዎች ጠይቃቸዉም: «ለጌታህ ሴት ልጆች ለእነርሱም ወንዶች ልጆች ይኖራሉን?
أَمْ خَلَقْنَا الْمَلَائِكَةَ إِنَاثًا وَهُمْ شَاهِدُونَ
«ወይስ እነርሱ የተገኙ (የሚመለከቱ) ሆነው መላዕክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን?»
أَلَا إِنَّهُمْ مِنْ إِفْكِهِمْ لَيَقُولُونَ
አስተውሉ! እነርሱ ከቅጥፈታቸው የተነሳ ይላሉ:
وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ
፡- «አላህ (መላዕክትን) ወለደ።» እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው።
أَصْطَفَى الْبَنَاتِ عَلَى الْبَنِينَ
በወንዶች ልጆች ላይ ይልቅ ሴቶች ልጆችን መረጠን?
مَا لَكُمْ كَيْفَ تَحْكُمُونَ
ምን ሆናችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ!
أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
አትገነዘቡምን?
أَمْ لَكُمْ سُلْطَانٌ مُبِينٌ
ወይስ ለእናንተ ግልጽ አስረጂ አላችሁን?
فَأْتُوا بِكِتَابِكُمْ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ
«እውነተኞች እንደሆናችሁ መጽሐፋችሁን አምጡ» (በላቸው)።
وَجَعَلُوا بَيْنَهُ وَبَيْنَ الْجِنَّةِ نَسَبًا ۚ وَلَقَدْ عَلِمَتِ الْجِنَّةُ إِنَّهُمْ لَمُحْضَرُونَ
በአላህና በአጋንንት መካከልም ዝምድናን አደረጉ። አጋንንትም ሆኑ ይህን ባዩች በእሳት የሚጣዱ መሆናቸውን በእርግጥ አውቀዋል።
سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ
አላህ ከሚሉት (ከሚገልጹት) ሁሉ ጠራ።
إِلَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ
ግን የተመረጡት የአላህ ባሮች (በአላህ ላይ አይዋሹም)።
فَإِنَّكُمْ وَمَا تَعْبُدُونَ
(ካሐዲያን ሆይ!) እናንተም የምትገዟቸዉም ሁሉ፤
مَا أَنْتُمْ عَلَيْهِ بِفَاتِنِينَ
በእርሱ በአላህ ላይ አንድንም አጥማሚዎች አይደላችሁም
إِلَّا مَنْ هُوَ صَالِ الْجَحِيمِ
ያንን እርሱ ገሀነም ገቢ የሆነውን ቢሆን እንጂ (አጥማሚዎች አይደላችሁም)።
وَمَا مِنَّا إِلَّا لَهُ مَقَامٌ مَعْلُومٌ
(መላእክቶችም አሉ) «ከእኛ አንድም የለም፤ ለእርሱ የታወቀ ደረጃ ያለው ቢሆን እንጅ።
وَإِنَّا لَنَحْنُ الصَّافُّونَ
«እኛም ጌታን ለመገዛት ተሰላፊዎቹ እኛ ነን።
وَإِنَّا لَنَحْنُ الْمُسَبِّحُونَ
«እኛም አላህን አጥሪዎቹ እኛው ነን።»
وَإِنْ كَانُوا لَيَقُولُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱ (ከሓዲያን) በእርግጥ ይሉ ነበር:
لَوْ أَنَّ عِنْدَنَا ذِكْرًا مِنَ الْأَوَّلِينَ
«ከቀድሞዎቹ መጽሐፍ ገሳጭ መጽሐፍ እኛ ዘንድ በነበረ ኖሮ
لَكُنَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ
«የአላህ ምርጦች ባሮች በሆን ነበር።»
فَكَفَرُوا بِهِ ۖ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ
ግን (ቁርኣኑ በመጣላቸው ጊዜ) በእርሱ ላይ ካዱ። ወደ ፊትም በእርግጥ ያውቃሉ።
وَلَقَدْ سَبَقَتْ كَلِمَتُنَا لِعِبَادِنَا الْمُرْسَلِينَ
የእርዳታ ቃላችንም መልዕክተኞች ለሆኑት ባሮቻችን በእውነት አልፋለች።
إِنَّهُمْ لَهُمُ الْمَنْصُورُونَ
እነርሱ ተረጂዎቹ እነርሱ ብቻ ናቸው።
وَإِنَّ جُنْدَنَا لَهُمُ الْغَالِبُونَ
ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው።
فَتَوَلَّ عَنْهُمْ حَتَّىٰ حِينٍ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ከመካ ከሓዲያን እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ዙር ተዋቸው።
وَأَبْصِرْهُمْ فَسَوْفَ يُبْصِرُونَ
ተመልከታቸዉም ወደፊትም የሚደርስባቸውን ያያሉ።
أَفَبِعَذَابِنَا يَسْتَعْجِلُونَ
በቅጣታችንም ያቻኩሉናልን?
فَإِذَا نَزَلَ بِسَاحَتِهِمْ فَسَاءَ صَبَاحُ الْمُنْذَرِينَ
በቀያቸዉም በወረደ ጊዜ የተስፈራሪዎቹ ንጋት ከፋ!
وَتَوَلَّ عَنْهُمْ حَتَّىٰ حِينٍ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነርሱን እስከ ጥቂት ጊዜ ድረስ ተዋቸው።
وَأَبْصِرْ فَسَوْفَ يُبْصِرُونَ
ተመልከትም በእርግጥም ያያሉ።
سُبْحَانَ رَبِّكَ رَبِّ الْعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ።
وَسَلَامٌ عَلَى الْمُرْسَلِينَ
በመልዕክተኞቹም ላይ ሰላም ይሁን።
وَالْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ
ምስጋና ሁሉም ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው።