وَالنَّجْمِ إِذَا هَوَىٰ
በኮከብ እምላለሁ በገባ ጊዜ፤
القرآن الكريمAfrica Academy
بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።
وَالنَّجْمِ إِذَا هَوَىٰ
በኮከብ እምላለሁ በገባ ጊዜ፤
مَا ضَلَّ صَاحِبُكُمْ وَمَا غَوَىٰ
(እናንተ የመካ ሰዎች ሆይ)፤ ባልደረባችሁ ሙሐመድ ከሐቅ አልተሳሳተም። አላፈነገጠም።
وَمَا يَنْطِقُ عَنِ الْهَوَىٰ
ከልብ ወለድ ስሜቱም አይናገርም።
إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ
እርሱ (ንግግሩ) ከአላህ የሚወርድ ራዕይ እንጂ ሌላ አይደለም።
عَلَّمَهُ شَدِيدُ الْقُوَىٰ
ሀይለ ብርቱ የሆነው አስተማረው።
ذُو مِرَّةٍ فَاسْتَوَىٰ
የብርታትና የውብ ቅርጽ ባለቤት የሆነው። ከዚያም ላይ ሆኖ ተመቻቸ።
وَهُوَ بِالْأُفُقِ الْأَعْلَىٰ
በላይኛው አድማስ ላይ ሆኖ፤
ثُمَّ دَنَا فَتَدَلَّىٰ
ከዚያም (ነቢዩን) ቀረበው፤ በጣም ተጠጋውም።
فَكَانَ قَابَ قَوْسَيْنِ أَوْ أَدْنَىٰ
ከዚያም የሁለት ደጋን ጫፎች ያህል ወይም ከዚያም ባነሰ ርቀት ላይ ሆነም።
فَأَوْحَىٰ إِلَىٰ عَبْدِهِ مَا أَوْحَىٰ
እናም (አላህ) ለአገልጋዩ (ለሙሐመድ) ማውረድ የሻውን አወረደ።
مَا كَذَبَ الْفُؤَادُ مَا رَأَىٰ
ያየውን ነገር ሁሉ ልቦናው አላስተባበለዉም።
أَفَتُمَارُونَهُ عَلَىٰ مَا يَرَىٰ
ታዲያ (ከሓዲያን ሆይ!) በሚያየው ጉዳይ ላይ ትከራከሩታላችሁን?
وَلَقَدْ رَآهُ نَزْلَةً أُخْرَىٰ
እርግጥ በሌላይቱም መውረድ (ነቢዩ ሙሐመድ መልዐኩ ጂብሪልን) አይቶታል።
عِنْدَ سِدْرَةِ الْمُنْتَهَىٰ
ይኸዉም ሲድረቱ አል-ሙንተሃ (የመጨረሻቱ ቁርቁራ) (በተባለችው ዛፍ) ዘንድ ነው።
عِنْدَهَا جَنَّةُ الْمَأْوَىٰ
እርሷ ዘንድ መኖርያ የሆነችው ገነት አለች።
إِذْ يَغْشَى السِّدْرَةَ مَا يَغْشَىٰ
(ቁርቁራይቱን) ሸፋኝ ነገር በሸፈናት ጊዜ (አየው)።
مَا زَاغَ الْبَصَرُ وَمَا طَغَىٰ
አይኑ አልተዘነበለም። ወሰንም አላለፈም።
لَقَدْ رَأَىٰ مِنْ آيَاتِ رَبِّهِ الْكُبْرَىٰ
ከጌታው ታላላቅ ተዐምራት በእርግጥ ተመለከተ።
أَفَرَأَيْتُمُ اللَّاتَ وَالْعُزَّىٰ
(ቁርይሾች ሆይ!) ላትንና ዑዛን አያችሁን?
وَمَنَاةَ الثَّالِثَةَ الْأُخْرَىٰ
ስለ ሶስተኛዋ ሌላዋ መናትም (የምታውቁትን እስቲ ንገሩኝ።)
أَلَكُمُ الذَّكَرُ وَلَهُ الْأُنْثَىٰ
ለእናንተ ወንድ ወንድ ለእሱ ግን ሴት ሴት ታደርጋላችሁን።
تِلْكَ إِذًا قِسْمَةٌ ضِيزَىٰ
ይህ ተግባር አድሏዊ ክፍፍል ነው።
إِنْ هِيَ إِلَّا أَسْمَاءٌ سَمَّيْتُمُوهَا أَنْتُمْ وَآبَاؤُكُمْ مَا أَنْزَلَ اللَّهُ بِهَا مِنْ سُلْطَانٍ ۚ إِنْ يَتَّبِعُونَ إِلَّا الظَّنَّ وَمَا تَهْوَى الْأَنْفُسُ ۖ وَلَقَدْ جَاءَهُمْ مِنْ رَبِّهِمُ الْهُدَىٰ
እነዚያ ጣዖታት እናንተና አባቶቻችሁ የሰየማችኋቸው ስሞች ብቻ እንጂ ሌላ አይደሉም።አላህ በእርሷ (መገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም። ጣዖት አምላኪዎች ሁሉ ከጌታቸው የተላከላቸው ቅኑ መመሪያ እያለ የሚከተሉት ግን ጥርጣሬንና ስሜትን ብቻ ነው።
أَمْ لِلْإِنْسَانِ مَا تَمَنَّىٰ
የሰው ልጅ የፈለገውን ሁሉ ያገኛልን?
فَلِلَّهِ الْآخِرَةُ وَالْأُولَىٰ
መጪው ዓለምም ሆነ የመጀመሪያው ዓለም የአላህ ብቻ ነው።
وَكَمْ مِنْ مَلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِنْ بَعْدِ أَنْ يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَنْ يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ
በሰማያት ውስጥ ካሉ መላዕክት አላህ ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ያማልዱ ዘንድ ከፈቀደላቸው በኋላ እንጂ ምልጃቸው የማይፈይድ አያሌዎች ናቸው።
إِنَّ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ لَيُسَمُّونَ الْمَلَائِكَةَ تَسْمِيَةَ الْأُنْثَىٰ
እነዚያ በመጪው ዓለም የማያምኑት መላዕክትን በእንስት ስም ይሰይማሉ።
وَمَا لَهُمْ بِهِ مِنْ عِلْمٍ ۖ إِنْ يَتَّبِعُونَ إِلَّا الظَّنَّ ۖ وَإِنَّ الظَّنَّ لَا يُغْنِي مِنَ الْحَقِّ شَيْئًا
ለእነርሱም በእርሱ እውቀት የላቸውም። እነርሱ የሚከተሉት ጥርጣሬን ብቻ ነው። ጥርጣሬ ደግሞ ሀቅን አይተካም።
فَأَعْرِضْ عَنْ مَنْ تَوَلَّىٰ عَنْ ذِكْرِنَا وَلَمْ يُرِدْ إِلَّا الْحَيَاةَ الدُّنْيَا
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከቁርኣን አፈንግጦና የዚችን ዓለም ኑሮ እንጂ ሌላ ከማይመኝ ሰው እራስህን አሽሽ።
ذَٰلِكَ مَبْلَغُهُمْ مِنَ الْعِلْمِ ۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعْلَمُ بِمَنْ ضَلَّ عَنْ سَبِيلِهِ وَهُوَ أَعْلَمُ بِمَنِ اهْتَدَىٰ
ይህ የእውቀታቸው ጣሪያ (መጨረሻ) ነው። ጌታህ እርሱ መንገዱን የሳተውን ሰው ከሁሉም ይበልጥ አዋቂ ነው። የተቀናውንም እርሱ ይበልጥ አዋቂ ነው።
وَلِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ لِيَجْزِيَ الَّذِينَ أَسَاءُوا بِمَا عَمِلُوا وَيَجْزِيَ الَّذِينَ أَحْسَنُوا بِالْحُسْنَى
በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የአላህ ነው። እነዚያን ያጠፉትን በተግባራቸው ለመመንዳትና እነዚያን መልካም የሰሩትንም በመልካሟ (በገነት) ሊመነዳ ነው።
الَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَائِرَ الْإِثْمِ وَالْفَوَاحِشَ إِلَّا اللَّمَمَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ وَاسِعُ الْمَغْفِرَةِ ۚ هُوَ أَعْلَمُ بِكُمْ إِذْ أَنْشَأَكُمْ مِنَ الْأَرْضِ وَإِذْ أَنْتُمْ أَجِنَّةٌ فِي بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ ۖ فَلَا تُزَكُّوا أَنْفُسَكُمْ ۖ هُوَ أَعْلَمُ بِمَنِ اتَّقَىٰ
እነርሱም ከጥቃቅን ጥፋቶች በቀር ከባባድ ወንጀሎችንና አጸያፊ ተግባሮችን የራቁ ናቸው። ጌታህ ምህረተ ሰፊ ነው። እርሱ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜም ሆነ በእናቶቻችሁ ማሕጸን ውስጥ ጽንሶች በሆናችሁበት ጊዜ ያውቃችኋል። ስለዚህ እራሳችሁን አታሞግሱ። እርሱ በትክክል የሚፈራውን ሰው ከሁሉም ይበልጥ አዋቂ ነው።
أَفَرَأَيْتَ الَّذِي تَوَلَّىٰ
ያን ከእምነት የሸሸውን አየህን (እስቲ ንገረኝ)?
وَأَعْطَىٰ قَلِيلًا وَأَكْدَىٰ
ጥቂትን ብቻ ሰጥቶ ያቋረጠውን፤
أَعِنْدَهُ عِلْمُ الْغَيْبِ فَهُوَ يَرَىٰ
ለመሆኑ የሚያውቀው የሩቅ ሚስጢር አለውና እርሱንም ያያልን?
أَمْ لَمْ يُنَبَّأْ بِمَا فِي صُحُفِ مُوسَىٰ
ወይስ በሙሳ ፅሁፍ ውስጥ ያለው አልተነገረውም?
وَإِبْرَاهِيمَ الَّذِي وَفَّىٰ
በኢብራሂም (ትእዛዛቱን) በፈፀመው ያለውስ አልተነገረዉምን?
أَلَّا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ
ይኸዉም ወንጀለኛ ነፍስ የሌላውን ነፍስ ወንጀል በፍጹም አትሸከምም።
وَأَنْ لَيْسَ لِلْإِنْسَانِ إِلَّا مَا سَعَىٰ
የሰው ልጅም የለፋበትን ብቻ እንጂ ሌላ የለዉም።
وَأَنَّ سَعْيَهُ سَوْفَ يُرَىٰ
የሰራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል።
ثُمَّ يُجْزَاهُ الْجَزَاءَ الْأَوْفَىٰ
ከዚያም (ጌታው) ሙሉ ምንዳውን ይመነዳዋል።
وَأَنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ الْمُنْتَهَىٰ
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሁሉም መጨረሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው።
وَأَنَّهُ هُوَ أَضْحَكَ وَأَبْكَىٰ
እርሱ ያ ያሳቀና ያስለቀሰ ነው።
وَأَنَّهُ هُوَ أَمَاتَ وَأَحْيَا
እርሱ ያ ያሞተና ሕያው ያደረገም ነው።
وَأَنَّهُ خَلَقَ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنْثَىٰ
እርሱ ያ ጥንድን፤ ወንድንና ሴትን የፈጠረ ነው።
مِنْ نُطْفَةٍ إِذَا تُمْنَىٰ
ይኸዉም ከፍትወት ጠብታ በማሕጸን ውስጥ በምትፈሰስ ጊዜ ነው።
وَأَنَّ عَلَيْهِ النَّشْأَةَ الْأُخْرَىٰ
ሌላውን ፍጥረት (ትንሳኤን) ማስገኘትም በእርሱ ላይ ነው።
وَأَنَّهُ هُوَ أَغْنَىٰ وَأَقْنَىٰ
እርሱ ያ ሀብትን የሰጠና ያብቃቃ ነው።
وَأَنَّهُ هُوَ رَبُّ الشِّعْرَىٰ
እርሱ የሺዕራ ጌታ ነው።
وَأَنَّهُ أَهْلَكَ عَادًا الْأُولَىٰ
እርሱ የቀድሞዋን ዓድ (ሕዝቦች) አጠፋ።
وَثَمُودَ فَمَا أَبْقَىٰ
ሰሙድንም አጠፋ። አንድንም አላስቀረም።
وَقَوْمَ نُوحٍ مِنْ قَبْلُ ۖ إِنَّهُمْ كَانُوا هُمْ أَظْلَمَ وَأَطْغَىٰ
በፊትም የኑህን ህዝቦች አጥፍቷል። እነርሱ እጅግ በዳዮችና በጣም አመጸኞች ነበሩና ነው።
وَالْمُؤْتَفِكَةَ أَهْوَىٰ
የተገለበጡትንም ደፋ።
فَغَشَّاهَا مَا غَشَّىٰ
ባሸፈናት ሸፈናት።
فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكَ تَتَمَارَىٰ
(የሰው ልጅ ሆይ)፤ ከጌታህ ጸጋዎች በየትኛው ነው የምትጠራጠረው።
هَٰذَا نَذِيرٌ مِنَ النُّذُرِ الْأُولَىٰ
(ሰዎች ሆይ!) ይህ (ሙሐመድ) ከቀድሞዎቹ አስጠንቃቂዎች አንዱ ነው።
أَزِفَتِ الْآزِفَةُ
ቀራቢቱም ቀረበች።
لَيْسَ لَهَا مِنْ دُونِ اللَّهِ كَاشِفَةٌ
ከአላህ በስተቀር ገላጭ የላትም።
أَفَمِنْ هَٰذَا الْحَدِيثِ تَعْجَبُونَ
በዚህ ዘገባ ትደነቃላችሁን?
وَتَضْحَكُونَ وَلَا تَبْكُونَ
ትስቃላችሁን? አታለቅሱምን?
وَأَنْتُمْ سَامِدُونَ
እናንተ ዘወትር ዘንጊዎች ናችሁን?
فَاسْجُدُوا لِلَّهِ وَاعْبُدُوا ۩
ለአላህ ስገዱ በብቸኝነትም አምልኩትም።