١ إِذَا جَاءَكَ الْمُنَافِقُونَ قَالُوا نَشْهَدُ إِنَّكَ لَرَسُولُ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ إِنَّكَ لَرَسُولُهُ وَاللَّهُ يَشْهَدُ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ لَكَاذِبُونَ
1 አስመሳዮች በመጡህ (ወደ አንተ በመጡ) ጊዜ «አንተ የአላህ መልዕክተኛ መሆንህን በእርግጥ (ምለን) እንመሰክራለን» ይላሉ። አላህም አንተ በእርግጥ መልዕክተኛው መሆንህን ያውቃል። አላህም አስመሳዮችን ውሸታሞች መሆናቸውን ይመሰክራል።
٢ اتَّخَذُوا أَيْمَانَهُمْ جُنَّةً فَصَدُّوا عَنْ سَبِيلِ اللَّهِ ۚ إِنَّهُمْ سَاءَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
2 መሓላዎቻቸውን ጋሻ አድርገው ያዙ። ከአላህም መንገድ ከለከሉ። እነርሱ ይሰሩት የነበሩት ነገር ሁሉ ከፋ።
٣ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ آمَنُوا ثُمَّ كَفَرُوا فَطُبِعَ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ فَهُمْ لَا يَفْقَهُونَ
3 ይህ እነርሱ (በምላስ) አምነው ከዚያም (በልብ) የካዱ በመሆናቸው በልቦቻቸዉም ላይ ታተመባቸው። ስለዚህ እነርሱ አያውቁም።
٤ وَإِذَا رَأَيْتَهُمْ تُعْجِبُكَ أَجْسَامُهُمْ ۖ وَإِنْ يَقُولُوا تَسْمَعْ لِقَوْلِهِمْ ۖ كَأَنَّهُمْ خُشُبٌ مُسَنَّدَةٌ ۖ يَحْسَبُونَ كُلَّ صَيْحَةٍ عَلَيْهِمْ ۚ هُمُ الْعَدُوُّ فَاحْذَرْهُمْ ۚ قَاتَلَهُمُ اللَّهُ ۖ أَنَّىٰ يُؤْفَكُونَ
4 ባየሃቸው ጊዜ አካሎቻቸው ያስደንቁሃል። ቢናገሩም ንግግራቸውን ታዳምጣለህ። እነርሱ ልክ ወደ ግድግዳ የተጠጉ ግንዶችን ይመስላሉ። ጩኸትን ሁሉ በእነርሱ ላይ ነው ብለው ያስባሉ። እነርሱ ጠላቶች ናቸውና ተጠንቀቃቸው። አላህ ይጋደላቸው። (ከእምነት) እንዴት ይመለሳሉ (ያፈገፍጋሉ)።
٥ وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا يَسْتَغْفِرْ لَكُمْ رَسُولُ اللَّهِ لَوَّوْا رُءُوسَهُمْ وَرَأَيْتَهُمْ يَصُدُّونَ وَهُمْ مُسْتَكْبِرُونَ
5 ለእነርሱም፡- «ኑ የአላህ መልዕክተኛ ለእናንተ ምህረትን ይለምንላችኋል» በተባሉ ጊዜ በማፌዝ ራሶቻቸውን ያዞራሉ። እነርሱም ትዕቢተኞች ሆነው ሲሸሹ ታያቸዋለህ።
٦ سَوَاءٌ عَلَيْهِمْ أَسْتَغْفَرْتَ لَهُمْ أَمْ لَمْ تَسْتَغْفِرْ لَهُمْ لَنْ يَغْفِرَ اللَّهُ لَهُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْفَاسِقِينَ
6 ምህረትን ብትለምንላቸውም ባትለምንላቸዉም በእነርሱ ላይ ሁሉም እኩል ነው። አላህ ለእነርሱ በፍጹም አይምርም። አላህ አመጸኛ ህዝቦችን አይመራምና።
٧ هُمُ الَّذِينَ يَقُولُونَ لَا تُنْفِقُوا عَلَىٰ مَنْ عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ حَتَّىٰ يَنْفَضُّوا ۗ وَلِلَّهِ خَزَائِنُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلَٰكِنَّ الْمُنَافِقِينَ لَا يَفْقَهُونَ
7 እነርሱ፡- «እነዚያ ከአላህ መልዕክተኛ ዘንድ ያሉት ሰዎች እስከ ሚበታተኑ ድረስ ምጽዋት አትስጡ» የሚሉ ናቸው። የሰማያትና የምድር ድልቦች የአላህ ብቻ ናቸው። ግን አስመሳዮች አይገነዘቡም።
٨ يَقُولُونَ لَئِنْ رَجَعْنَا إِلَى الْمَدِينَةِ لَيُخْرِجَنَّ الْأَعَزُّ مِنْهَا الْأَذَلَّ ۚ وَلِلَّهِ الْعِزَّةُ وَلِرَسُولِهِ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَلَٰكِنَّ الْمُنَافِقِينَ لَا يَعْلَمُونَ
8 «ወደ መዲና ብንመለስ አሸናፊው ወራዳውን በእርግጥ ከእርሷ ያስወጣል» ይላሉ። አሸናፊነትም ለአላህ ለመልዕክተኛው እና ለምዕምናን ብቻ ነው። ግን አስመሳዮች አያውቁም።
٩ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُلْهِكُمْ أَمْوَالُكُمْ وَلَا أَوْلَادُكُمْ عَنْ ذِكْرِ اللَّهِ ۚ وَمَنْ يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ
9 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ አላህን ከማስታወስ አያታልሏችሁ (አያዘናጓችሁ)። ይህንንም የሚሰሩ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎች ናቸው።
١٠ وَأَنْفِقُوا مِنْ مَا رَزَقْنَاكُمْ مِنْ قَبْلِ أَنْ يَأْتِيَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ فَيَقُولَ رَبِّ لَوْلَا أَخَّرْتَنِي إِلَىٰ أَجَلٍ قَرِيبٍ فَأَصَّدَّقَ وَأَكُنْ مِنَ الصَّالِحِينَ
10 አንዳችሁም ሞት ሳይመጣበትና «ጌታየ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጎችም ሰዎች እንድሆን ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ» ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ።
١١ وَلَنْ يُؤَخِّرَ اللَّهُ نَفْسًا إِذَا جَاءَ أَجَلُهَا ۚ وَاللَّهُ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ
11 ማንኛይቱም ነፍስ የሞት ጊዜዋ በመጣባት ጊዜ አላህ በፍጹም አያቆያትም። አላህም በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።