Resurrection · al-Qiyamah · سورة القيامة · 40 ayahs

القرآن الكريمAfrica Academy

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)።

لَا أُقْسِمُ بِيَوْمِ الْقِيَامَةِ

(ሁኔታው ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም)። በትንሳኤ ቀን እምላለሁ።

وَلَا أُقْسِمُ بِالنَّفْسِ اللَّوَّامَةِ

(ሁኔታው ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም)። ራሷን ወቃሽ በሆነች ነፍስም እምላለሁ።

أَيَحْسَبُ الْإِنْسَانُ أَلَّنْ نَجْمَعَ عِظَامَهُ

(በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ።) ሰው አጥንቶቹን አለመሰብሰባችንን ያስባልን?

بَلَىٰ قَادِرِينَ عَلَىٰ أَنْ نُسَوِّيَ بَنَانَهُ

እንዴታ ጣቶቹንም ፊት እንደነበሩት በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንሆን (እንሰበስባቸዋለን)።

بَلْ يُرِيدُ الْإِنْسَانُ لِيَفْجُرَ أَمَامَهُ

ይልቁን ሰው በፊቱ ባለ ነገር በትንሳኤ ቀን ሊያስተባብል ይፈልጋል።

يَسْأَلُ أَيَّانَ يَوْمُ الْقِيَامَةِ

«የትንሳኤው ቀን መቼ ነው?» ሲል ይጠይቃል።

فَإِذَا بَرِقَ الْبَصَرُ

ዓይንም በዋለለ ጊዜ።

وَخَسَفَ الْقَمَرُ

ጨረቃም በጨለመ ጊዜ።

وَجُمِعَ الشَّمْسُ وَالْقَمَرُ

ጸሐይና ጨረቃም በተሰበሰቡ ጊዜ፤

يَقُولُ الْإِنْسَانُ يَوْمَئِذٍ أَيْنَ الْمَفَرُّ

ሰው በዚያን ቀን «መሸሻው የት ነው?» ይላል።

كَلَّا لَا وَزَرَ

«ይከልከል፤ ምንም መጠጊያ የለም።

إِلَىٰ رَبِّكَ يَوْمَئِذٍ الْمُسْتَقَرُّ

በዚያ ቀን መርጊያው ወደ ጌታህ ብቻ ነው።» ይባላል።

يُنَبَّأُ الْإِنْسَانُ يَوْمَئِذٍ بِمَا قَدَّمَ وَأَخَّرَ

ሰው በዚያን ቀን ያስቀደመውም ያስቆየውም ሁሉ ይነገረዋል።

بَلِ الْإِنْسَانُ عَلَىٰ نَفْسِهِ بَصِيرَةٌ

በእርግጥ ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው።

وَلَوْ أَلْقَىٰ مَعَاذِيرَهُ

ምክንያቶቹን ሁሉ ቢያመጣ እንኳን (አይሰማም)።

لَا تُحَرِّكْ بِهِ لِسَانَكَ لِتَعْجَلَ بِهِ

በቁርኣን ንባብ ልትቸኩል ብለህ ምላስህን አታላውስ።

إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ

በልብህ ውስጥ መሰብሰቡና ማስነበቡ በኛ ላይ ነውና።

فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَهُ

ባነበብነው ጊዜ (ካለቀ በኋላ) ንባቡን ተከተል።

ثُمَّ إِنَّ عَلَيْنَا بَيَانَهُ

ከዚያም (ላንተ) ማብራራቱ በእኛ ላይ ነው።

كَلَّا بَلْ تُحِبُّونَ الْعَاجِلَةَ

(ነገሩ ከሓዲያን እንደሚሉት አይደለም)፤ ይልቁንም (ሰዎች ሆይ!) ፈጣኒቱን ዓለም ትወዳላችሁ።

وَتَذَرُونَ الْآخِرَةَ

የመጨረሻይቱን ዓለም (ግን) ትተዋላችሁ።

وُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ نَاضِرَةٌ

(የተወሰኑ) ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች ናቸው።

إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٌ

ወደ ጌታቸው ተመልካቾችም ናቸው።

وَوُجُوهٌ يَوْمَئِذٍ بَاسِرَةٌ

(ሌሎች) ፊቶች ደግሞ በዚያ ቀን አጨፍጋጊዎች ናቸው።

تَظُنُّ أَنْ يُفْعَلَ بِهَا فَاقِرَةٌ

በእነርሱም ላይ አደጋ እንደሚሰራባቸው ያረጋገጣሉ።

كَلَّا إِذَا بَلَغَتِ التَّرَاقِيَ

(ነገሩ እንደሚያስቡት አይደለም።) (ነፍስ) ወደ ጉሮሮ በደረሰች ጊዜ፤

وَقِيلَ مَنْ ۜ رَاقٍ

«አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፤

وَظَنَّ أَنَّهُ الْفِرَاقُ

(የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መለየት መሆኑን ባረጋገጠ ጊዜ፤

وَالْتَفَّتِ السَّاقُ بِالسَّاقِ

ባትም ከባት በተጣበቀች ጊዜ፤

إِلَىٰ رَبِّكَ يَوْمَئِذٍ الْمَسَاقُ

በዚያ ቀን መነዳት ወደ ጌታህ (ፍርድ) ብቻ ነው።

فَلَا صَدَّقَ وَلَا صَلَّىٰ

እናም (ከሀዲው) አላመነምም፤ አልሰገደምም።

وَلَٰكِنْ كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ

ግን በአላህ አስተባበለ፤ ከእምነት ዞረም።

ثُمَّ ذَهَبَ إِلَىٰ أَهْلِهِ يَتَمَطَّىٰ

ከዚያም እየተንጎማለለ ወደ ቤተሰቡ ሄደ።

أَوْلَىٰ لَكَ فَأَوْلَىٰ

(የምትጠላውን ነገር) ላንተው ይሁን፤ ላንተ ተገቢህም ነው።

ثُمَّ أَوْلَىٰ لَكَ فَأَوْلَىٰ

ከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ላንተ የተገባህም ነው።

أَيَحْسَبُ الْإِنْسَانُ أَنْ يُتْرَكَ سُدًى

ሰው እንደፈለገ እንዲኖር ልቅ ሆኖ የሚተው ይመስለዋልን?

أَلَمْ يَكُ نُطْفَةً مِنْ مَنِيٍّ يُمْنَىٰ

ከሚፈሰስ የፍትወት ፈሳሽ የሆነ ጠብታ አልነበረምን?

ثُمَّ كَانَ عَلَقَةً فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ

ከዚያ የረጋ ደም ሆነ። ከዚያ አላህ ሰው አድርጎ ፈጠረው፤ አስተካከለዉም።

فَجَعَلَ مِنْهُ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنْثَىٰ

ከእርሱም ሁለት ዓይነቶች ወንድና ሴትን አደረገ።

أَلَيْسَ ذَٰلِكَ بِقَادِرٍ عَلَىٰ أَنْ يُحْيِيَ الْمَوْتَىٰ

(ታዲያ) ይህ ሀያል (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን?