በሰማያትና በምድርም ያለው ምስጢር ሁሉ የአላህ ነው፡፡ ነገሩ ሁሉም ወደርሱ ይመለሳል፡፡ ስለዚህ ተገዛው፡፡ በእርሱም ላይ ተጠጋ፡፡ ጌታህም ከሚሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም፡፡
Hud 11:123
Compare 2 Amharic translations
وَلِلَّهِ غَيْبُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَإِلَيْهِ يُرْجَعُ الْأَمْرُ كُلُّهُ فَاعْبُدْهُ وَتَوَكَّلْ عَلَيْهِ ۚ وَمَا رَبُّكَ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ
DragHold to move · × to hide
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በሰማያትና በምድር ያለው ሚስጥር ሁሉ የአላህ ብቻ ነው። ሁሉም ነገር ወደ እርሱ ብቻ ይመለሳል። ስለዚህ እሱን ብቻ ተገዛው። በእርሱም ላይ ብቻ ተመካ። ጌታህም ከምትሠሩት ሁሉ ዘንጊ አይደለም።