Yusuf 12:31

Compare 2 Amharic translations

فَلَمَّا سَمِعَتْ بِمَكْرِهِنَّ أَرْسَلَتْ إِلَيْهِنَّ وَأَعْتَدَتْ لَهُنَّ مُتَّكَأً وَآتَتْ كُلَّ وَاحِدَةٍ مِنْهُنَّ سِكِّينًا وَقَالَتِ اخْرُجْ عَلَيْهِنَّ ۖ فَلَمَّا رَأَيْنَهُ أَكْبَرْنَهُ وَقَطَّعْنَ أَيْدِيَهُنَّ وَقُلْنَ حَاشَ لِلَّهِ مَا هَٰذَا بَشَرًا إِنْ هَٰذَا إِلَّا مَلَكٌ كَرِيمٌ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ሀሜታቸውንም በሰማች ጊዜ ወደነሱ ላከችባቸው፡፡ ምግብንም ለእነርሱ አዘጋጀችላቸው፡፡ ከእነሱ ለያንዳንዳቸውም ቢላዋን ሰጠች፡፡ በእነሱም ላይ «ውጣ» አለችው፡፡ ባዩትም ጊዜ አደነቁት፡፡ እጆቻቸውንም ቆረጡ፡፡ አላህም ጥራት ይገባው፡፡ ይህ ሰው አይደለም፡፡ ይህ ያማረ መልአክ እንጅ ሌላ አይደለም አሉ፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

እርሷም ሐሜታቸውን በሰማች ጊዜ ወደነሱ ላከችላቸው። ግብዣንም ለእነርሱ አዘጋጀችላቸው። ለያንዳንዳቸዉም ቢላዋን ሰጠችና «በእነርሱም ላይ ውጣ።» አለችው። እነርሱም በተመለከቱት ጊዜ በጣም አደነቁት። እጆቻቸዉንም ቆረጡ። «ለአላህ ጥራት ይገባው። ይህ ሰው አይደለም። ይህ የተከበረ መልአክ እንጂ ሌላ አይደለም።» አሉ።

Africa Academy