Al-Isra' 17:97

Compare 2 Amharic translations

وَمَنْ يَهْدِ اللَّهُ فَهُوَ الْمُهْتَدِ ۖ وَمَنْ يُضْلِلْ فَلَنْ تَجِدَ لَهُمْ أَوْلِيَاءَ مِنْ دُونِهِ ۖ وَنَحْشُرُهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ عَلَىٰ وُجُوهِهِمْ عُمْيًا وَبُكْمًا وَصُمًّا ۖ مَأْوَاهُمْ جَهَنَّمُ ۖ كُلَّمَا خَبَتْ زِدْنَاهُمْ سَعِيرًا

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

አላህም ያቀናው ሰው ቅኑ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ያጠመማቸውም ሰዎች ከእርሱ ሌላ ለእነርሱ ፈጽሞ ረዳት አታገኝላቸውም፡፡ በትንሣኤ ቀንም ዕውሮች፣ ዲዳዎችም ደንቆሮዎችም ኾነው በፊቶቻቸው ላይ (እየተጎተቱ) እንሰበስባቸዋለን፡፡ መኖሪያቸው ገሀነም ናት፡፡ (ነዲድዋ) በደከመች ቁጥር መንቀልቀልን እንጨምርባቸዋለን፡፤

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያቀናው በእርግጥም የተቀና ማለት እርሱው ነው። እርሱ ያጠመማቸውን ግን ከቅጣቱ የሚያድናቸው ማንም ወዳጅ አታገኝላቸዉም። የትንሳኤ ቀንም እውር፤ ዲዳና፤ ደንቆሮ አድርገን በፊቶቻቸው እየተጎተቱ እንሰበስባቸዋለን። መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት። ሀይሏ በደከመ ጊዜም ግለትን እንጨምርላቸዋለን።

Africa Academy