Al-Baqarah 2:102

Compare 2 Amharic translations

وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَىٰ مُلْكِ سُلَيْمَانَ ۖ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَٰكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ وَمَا أُنْزِلَ عَلَى الْمَلَكَيْنِ بِبَابِلَ هَارُوتَ وَمَارُوتَ ۚ وَمَا يُعَلِّمَانِ مِنْ أَحَدٍ حَتَّىٰ يَقُولَا إِنَّمَا نَحْنُ فِتْنَةٌ فَلَا تَكْفُرْ ۖ فَيَتَعَلَّمُونَ مِنْهُمَا مَا يُفَرِّقُونَ بِهِ بَيْنَ الْمَرْءِ وَزَوْجِهِ ۚ وَمَا هُمْ بِضَارِّينَ بِهِ مِنْ أَحَدٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ وَيَتَعَلَّمُونَ مَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنْفَعُهُمْ ۚ وَلَقَدْ عَلِمُوا لَمَنِ اشْتَرَاهُ مَا لَهُ فِي الْآخِرَةِ مِنْ خَلَاقٍ ۚ وَلَبِئْسَ مَا شَرَوْا بِهِ أَنْفُسَهُمْ ۚ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን (ድግምት) ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ (ድግምተኛ አልነበረም)፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩትና ማሩት ላይ የተወረደውን ነገር (ያስተምሩዋቸዋል)፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በርሱ የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ፡፡ እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም፡፡ የሚጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውንም ይማራሉ፡፡ የገዛውም ሰው ለርሱ በመጨረሻይቱ አገር ምንም እድል የሌለው መኾኑን በእርግጥ ዐወቁ፡፡ ነፍሶቻቸውንም በርሱ የሸጡበት ዋጋ ከፋ! የሚያውቁ በኾኑ ኖሮ (ባልሠሩት ነበር)፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

(የአላህን መጽሐፍ አንቀበልም ያሉ አይሁዶች) ሰይጣናት በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን ድግምት ተከተሉ። ሱለይማን ጌታውን አልካደም።( ድግምተኛ አልነበረም።) ሰይጣናት ግን ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲሆኑ በጌታቸው ካዱ። በባቢሎን (በባቢል) በሁለቱ መላዕክት በሀሩትና በማሩት ላይ የተወረደውን ተከተሉ። (ሀሩትና ማሩት) ግን «እኛ መፈተኛ ብቻ ነንና በጌታህ አትካድ» እስከሚሉ ድረስ አንድንም አያስተምሩም ነበር። ከእነርሱም በባልና በሚስቱ መካከል የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ። እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር አንድንም በርሱ አይጎዱም። (ድግምት የሚማሩ ሁሉ) የሚጎዳቸውንና ቅንጣት የማይጠቅማቸውን ትምህርት ይማራሉ። የገዛው በመጨረሻይቱ አገር ምንም ዕድል የሌለው መሆኑን በእርግጥ ተገንዝበዋል። ነፍሶቻቸውን የሸጡበት ዋጋ ምንኛ ከፋ። የሚያውቁ በሆኑ ኖሮ (ይህን ተግባር ባልተገበሩት ነበር።)

Africa Academy