Al-Baqarah 2:144

Compare 2 Amharic translations

قَدْ نَرَىٰ تَقَلُّبَ وَجْهِكَ فِي السَّمَاءِ ۖ فَلَنُوَلِّيَنَّكَ قِبْلَةً تَرْضَاهَا ۚ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ ۚ وَحَيْثُ مَا كُنْتُمْ فَوَلُّوا وُجُوهَكُمْ شَطْرَهُ ۗ وَإِنَّ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ لَيَعْلَمُونَ أَنَّهُ الْحَقُّ مِنْ رَبِّهِمْ ۗ وَمَا اللَّهُ بِغَافِلٍ عَمَّا يَعْمَلُونَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

የፊትህን ወደ ሰማይ መገላበጥ በእርግጥ እናያለን፡፡ ወደምትወዳትም ቂብላ እናዞርሃለን፡፡ ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ (ወደ ካዕባ) አግጣጫ አዙር፡፡ የትም ስፍራ ብትኾኑም (ስትሰግዱ) ፊቶቻችሁን ወደርሱ አግጣጫ አዙሩ፡፡ እነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት መሆኑን ያውቃሉ፡፡ አላህም ከምትሠሩት ሥራ ዘንጊ አይደለም፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

የፊትህን ወደ ሰማይ ማንጋጠጥክን በእርግጥ ተመልክተናል። እናም ወደ ምትወዳት (ካዕባ) ቂብላ እናዞርሃለን። ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ ወደ ካዕባ አቅጣጫ አዙር። (ሙስሊሞች ሆይ!) የትም ስፍራ ብትሆኑ ስትሰግዱ ፊቶቻችሁን ወደ ካዕባ አቅጣጫ አዙሩ። እነዚያ መጽሐፉን የተሰጡት እርሱ ከጌታቸው ሲሆን እውነት መሆኑን ያውቃሉ። አላህ ከሚሰሩት ስራ ዘንጊ አይደለም።

Africa Academy