Al-Baqarah 2:165

Compare 2 Amharic translations

وَمِنَ النَّاسِ مَنْ يَتَّخِذُ مِنْ دُونِ اللَّهِ أَنْدَادًا يُحِبُّونَهُمْ كَحُبِّ اللَّهِ ۖ وَالَّذِينَ آمَنُوا أَشَدُّ حُبًّا لِلَّهِ ۗ وَلَوْ يَرَى الَّذِينَ ظَلَمُوا إِذْ يَرَوْنَ الْعَذَابَ أَنَّ الْقُوَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًا وَأَنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعَذَابِ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን (ጣዖታትን) አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አልሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡ እነዚያም የበደሉት ሰዎች ቅጣትን (በትንሣኤ ቀን) ባዩ ጊዜ ኀይል ሁሉ ለአላህ ብቻ መኾኑንና አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን (በአዱኛ ዓለም) ቢያውቁ ኖሮ (ባላንጣዎችን በመያዛቸው በተጸጸቱ ነበር)፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

ከሰዎች መካከል ከአላህ ሌላ ባላንጣዎችን/ ጣዖታትን/ አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ሆነው የሚይዙ አሉ። እነዚያ ያመኑት ግን አላህን ከምንም በላይ ይወዳሉ። እነዚያም የበደሉት ሰዎች ቅጣትን በትንሳኤ ቀን ባዩ ጊዜ ሀይል ሁሉ ለአላህ ብቻ መሆኑንና አላህም ቅጣቱ ብርቱ እንደሆነ (በዚህች ዐለም ሳሉ) ቢያውቁ ኖሮ (ባላንጣዎችን ባልያዙ ነበር)።

Africa Academy