Al-Baqarah 2:177

Compare 2 Amharic translations

لَيْسَ الْبِرَّ أَنْ تُوَلُّوا وُجُوهَكُمْ قِبَلَ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ وَلَٰكِنَّ الْبِرَّ مَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَالْمَلَائِكَةِ وَالْكِتَابِ وَالنَّبِيِّينَ وَآتَى الْمَالَ عَلَىٰ حُبِّهِ ذَوِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينَ وَابْنَ السَّبِيلِ وَالسَّائِلِينَ وَفِي الرِّقَابِ وَأَقَامَ الصَّلَاةَ وَآتَى الزَّكَاةَ وَالْمُوفُونَ بِعَهْدِهِمْ إِذَا عَاهَدُوا ۖ وَالصَّابِرِينَ فِي الْبَأْسَاءِ وَالضَّرَّاءِ وَحِينَ الْبَأْسِ ۗ أُولَٰئِكَ الَّذِينَ صَدَقُوا ۖ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْمُتَّقُونَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

መልካም ሥራ ፊቶቻችሁን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞር አይደለም፡፡ ግን መልካም ሥራ በአላህና በመጨረሻው ቀን፣ በመላእክትም፣ በመጻሕፍትም፣ በነቢያትም፣ ያመነ ሰው፤ ገንዘብንም ከመውደዱ ጋር ለዝምድና ባለቤቶች፣ ለየቲሞች፣ ለምስኪኖችም፣ ለመንገደኞችም፣ ለለማኞችም፣ ለጫንቃዎችም (ማስለቀቅ) የሰጠ ሰውና፤ ሶላትንም ደንቡን ጠብቆ የሰገደ፣ ዘካንም የሰጠ፤ ቃል ኪዳንም በገቡ ጊዜ በኪዳናቸው የሞሉ (ሰዎች ሥራ) ነው፡፡ በችግር በበሽታና በጦር ጊዜም ታጋሾችን (እናወድሳለን)፡፡ እነዚህ እነዚያ እውነትን የያዙ ናቸው፡፡ እነዚያም ተጠንቃቂዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

መልካምነት ፊቶቻችሁን ወደ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞራችሁ አይደለም። መልካምነት በአላህ፣ በመጨረሻው ቀን፣ በመላዕክት፣ በመጻህፍት በነብያት ያመነ፤ ገንዘብንም ምንም ያህል የነዋይ (ገንዘብ) ፍቅር ቢኖረዉም ለዝምድና ባለቤቶች፣ ለየቲሞች፣ ለሚስኪኖች፣ ለመንገደኞች፣ ለለማኞች፣ ባሪያዎችን ነፃ ለማውጣት የሰጠ፤ ሶላትን ደንቡን ጠብቆ የሰገደና ዘካንም ያወጣ ነው። እንዲሁም ቃልኪዳን በገቡ ጊዜም ቃልኪዳናቸውን የሚሞሉ በችግር፣ በበሽታና በፍልሚያ ጊዜ ታጋሾች ናቸው። እነዚህ እነዚያ እውነትን የያዙ መሆናቸውን በተግባር አረጋግጠዋል። አላህን የሚፈሩትም እነርሱው ናቸው።

Africa Academy