Al-Baqarah 2:185

Compare 2 Amharic translations

شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنْزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَنْ شَهِدَ مِنْكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖ وَمَنْ كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِنْ أَيَّامٍ أُخَرَ ۗ يُرِيدُ اللَّهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፡፡ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) (መጾም) አለበት፡፡ አላህ በእናንተ ገሩን (ነገር) ይሻል፡፡ በእናንተም ችግሩን አይሻም፡፡ ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩትና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገግንላችሁ)፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

(ያ እንድትጾሙት የተደነገገላችሁ ወር) በእርሱ ዉስጥ ለሰዎች መሪ ቅኑን መንገድና እውነትን ከዉሸት የሚለየው ገላጭ ቁርአን የተወረደበት የረመዷን ወር ነው። ከናንተ መካከል ወሩን ያገኘ ይጹመው። በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የሆነ ሰው (ካፈጠረ) ከሌሎች ቀናት ባልፆማቸው ቀናት ቁጥሮች ልክ መፆም አለበት። አላህ ሁልጊዜም ለእናንተ ገሩን ነገር ይሻል እንጂ በእናንተ ላይ ጫናን መፍጠርን አይሻምና ነው። (ለፆም የተወሰኑትን) ቀናት ልትሞሉና አላህን ቅንኑ መንገድ ስለመራችሁ ልታከብሩትና ልታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገገላችሁ)።

Africa Academy