Al-Baqarah 2:189

Compare 2 Amharic translations

يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَهِلَّةِ ۖ قُلْ هِيَ مَوَاقِيتُ لِلنَّاسِ وَالْحَجِّ ۗ وَلَيْسَ الْبِرُّ بِأَنْ تَأْتُوا الْبُيُوتَ مِنْ ظُهُورِهَا وَلَٰكِنَّ الْبِرَّ مَنِ اتَّقَىٰ ۗ وَأْتُوا الْبُيُوتَ مِنْ أَبْوَابِهَا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

(ሙሐመድ ሆይ!) ከለጋ ጨረቃዎች (መለዋወጥ) ይጠየቁሃል፡፡ እነርሱ ለሰዎች (ጥቅም) ለሐጅም (ማወቂያ) ጊዜያቶች (ምልክቶች) ናቸው በላቸው፡፡ መልካም ሥራም ቤቶችን ከጀርባዎቻቸው በመምጣታችሁ አይደለም፡፡ ግን የመልካም ሥራ ባለቤት የተጠነቀቀ ሰው ነው፡፡ ቤቶችንም ከደጃፎቻቸው በኩል ግቡ፤ አላህንም ፍሩ ልትድኑ ይከጀላልና (በላቸው)፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ስለ ለጋ ጨረቃ መለዋወጥ ይጠይቁሃል። «ይህ ክስተት ሰዎች ጊዜን ለመለካት የሚጠቀሙበትና የሐጅንም ወቅት ለማወቅ የሚረዳ ምልክት ነው። መልካም ስራ ቤቶችን ከጀርባዎቻቸው መግባታችሁ አይደለም። ይልቁንም የመልካም ስራ ባለቤት አላህን የሚፈራው ነው። ቤቶችንም በፊት በሮቻቸው በኩል ግቡ። አላህንም ፍሩ። ከጀሀነም ቅጣት ልትድኑ ዘንድ።» በላቸው።

Africa Academy