Al-Baqarah 2:197

Compare 2 Amharic translations

الْحَجُّ أَشْهُرٌ مَعْلُومَاتٌ ۚ فَمَنْ فَرَضَ فِيهِنَّ الْحَجَّ فَلَا رَفَثَ وَلَا فُسُوقَ وَلَا جِدَالَ فِي الْحَجِّ ۗ وَمَا تَفْعَلُوا مِنْ خَيْرٍ يَعْلَمْهُ اللَّهُ ۗ وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ሐጅ (ጊዜያቱ) የታወቁ ወሮች ናቸው፡፡ በእነርሱም ውስጥ ሐጅን (እንዲሠራ) ነፍሱን ያስገደደ ሰው በሐጅ ውስጥ ሴትን መገናኘት ማመጽም ክርክርም የለም፡፡ ከበጎም ሥራ የምትሠሩትን ሁሉ አላህ ያውቀዋል፡፡ ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ (አላህን መፍራት) ነው፡፡ የአእምሮዎችም ባለቤቶች ሆይ! ፍሩኝ፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

ሐጅ የሚፈጸመው በተወሰኑ የታወቁ ወራት ነው። እናም በእነርሱ ውስጥ ሐጅን ለመስራት ግዴታ የገባ ሰው በሐጅ ክንውን ውስጥ እያለ ሴትን መገናኘት፤ በአላህ ላይ ማመጽና ክርክር አያደርግም። (ሙስሊሞች ሆይ!) ከበጎ ነገር የምትሰሩትን ሁሉ አላህ ያውቀዋል። ስንቅም ያዙ። ከስንቅ ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው። የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ! እኔን ብቻ ፍሩኝ።

Africa Academy