ጧሉትም በሠራዊቱ (ታጅቦ) በወጣ ጊዜ፡- «አላህ በወንዝ (ውሃ) ፈታኛችሁ ነው ከርሱም የጠጣ ሰው ከእኔ አይደለም፡፡ ያልቀመሰው ሰው እርሱ ከኔ ነው በእጁ መዝገንን የዘገነ ሰው ብቻ ሲቀር » አለ፡፡ ከእነርሱም ጥቂቶች ሲቀሩ ከርሱ ጠጡ፡፡ እርሱና እነዚያም ከእርሱ ጋር ያመኑት (ወንዙን) ባለፉት ጊዜ፡- «ጃሎትንና ሠራዊቱን በመዋጋት ለኛ ዛሬ ችሎታ የለንም» አሉት፡፡ እነዚያ እነርሱ አላህን ተገናኝዎች መኾናቸው የሚያረጋግጡት፡- «ከጥቂት ጭፍራ በአላህ ፈቃድ ብዙን ጭፍራ ያሸነፈች ብዙ ናት፤ አላህ ከታጋሾች ጋር ነው» አሉ፡፡
Al-Baqarah 2:249
Compare 2 Amharic translations
فَلَمَّا فَصَلَ طَالُوتُ بِالْجُنُودِ قَالَ إِنَّ اللَّهَ مُبْتَلِيكُمْ بِنَهَرٍ فَمَنْ شَرِبَ مِنْهُ فَلَيْسَ مِنِّي وَمَنْ لَمْ يَطْعَمْهُ فَإِنَّهُ مِنِّي إِلَّا مَنِ اغْتَرَفَ غُرْفَةً بِيَدِهِ ۚ فَشَرِبُوا مِنْهُ إِلَّا قَلِيلًا مِنْهُمْ ۚ فَلَمَّا جَاوَزَهُ هُوَ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ قَالُوا لَا طَاقَةَ لَنَا الْيَوْمَ بِجَالُوتَ وَجُنُودِهِ ۚ قَالَ الَّذِينَ يَظُنُّونَ أَنَّهُمْ مُلَاقُو اللَّهِ كَمْ مِنْ فِئَةٍ قَلِيلَةٍ غَلَبَتْ فِئَةً كَثِيرَةً بِإِذْنِ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ مَعَ الصَّابِرِينَ
DragHold to move · × to hide
ጧሉትም በሰራዊቱ ታጅቦ በወጣ ጊዜ ‹‹አላህ በወንዝ ውሃ ይፈትናችኋል። እናም ከእርሱ የጠጣ ሰው ሁሉ ከእኔ አይደለም። እሱን ያልቀመሰው ሰው ግን በእጁ አንድ እፍኝ ያህል የዘገነ ሰው ብቻ ሲቀር እርሱ ከእኔ ነው›› አለ። ከእነርሱም መካከል ጥቂቶች ሲቀሩ ከእርሱ ጠጡ። እርሱና እነዚያ ከእርሱ ጋር ያመኑት ወንዙን ባለፉት ጊዜ፡- «ጃሉትን (ጎልያድን) እና ሰራዊቱን ለመዋጋት በቂ ችሎታና ጥንካሬ የለንም።» አሉት። እነዚያ ከአላህ ጋር እንደሚገናኙ የሚያረጋግጡትም «ጥቂት ቡድን በአላህ ፈቃድ ብዙውን ቡድን ያሸነፈበት አጋጣሚ ብዙ ነው። አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና።» አሉ።