እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሠሩትን ለነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ያሏቸው መኾኑን አብስራቸው፡፡ ከርሷ ከፍሬ (ዓይነት) ሲሳይን በተመገቡ ቁጥር (ፍሬዎችዋ ስለሚመሳሰሉ) «ይህ ያ ከአሁን በፊት የተገመብነው ነው» ይላሉ፡፡ እርሱንም ተመሳሳይ ኾኖ ተሰጡት፡፡ ለነሱም በውስጧ ንጹህ የተደረጉ ሚስቶች አሏቸው፡፡ እነሱም በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
Al-Baqarah 2:25
Compare 2 Amharic translations
وَبَشِّرِ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أَنَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ ۖ كُلَّمَا رُزِقُوا مِنْهَا مِنْ ثَمَرَةٍ رِزْقًا ۙ قَالُوا هَٰذَا الَّذِي رُزِقْنَا مِنْ قَبْلُ ۖ وَأُتُوا بِهِ مُتَشَابِهًا ۖ وَلَهُمْ فِيهَا أَزْوَاجٌ مُطَهَّرَةٌ ۖ وَهُمْ فِيهَا خَالِدُونَ
DragHold to move · × to hide
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በትክክል በአላህ ያመኑትንና መልካም ተግባራትን የሰሩትን ሰዎች ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ያሏቸው መሆኑን አብስራቸው። በእርሷም ፍራፍሬ በተለገሱ ቁጥር (ፍሬዎቿ ስለሚመሳሰሉ) «ይህማ ያ ከአሁን በፊት የተመገብነው ነው።» ይላሉ። እርሱ ተመሳሳይ ሆኖ ይሰጣቸዋል ለእነርሱም በውስጧ ንጹህ ሚስቶች አሏቸው። እነርሱም በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው።