Al-Baqarah 2:253

Compare 2 Amharic translations

تِلْكَ الرُّسُلُ فَضَّلْنَا بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۘ مِنْهُمْ مَنْ كَلَّمَ اللَّهُ ۖ وَرَفَعَ بَعْضَهُمْ دَرَجَاتٍ ۚ وَآتَيْنَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ الْبَيِّنَاتِ وَأَيَّدْنَاهُ بِرُوحِ الْقُدُسِ ۗ وَلَوْ شَاءَ اللَّهُ مَا اقْتَتَلَ الَّذِينَ مِنْ بَعْدِهِمْ مِنْ بَعْدِ مَا جَاءَتْهُمُ الْبَيِّنَاتُ وَلَٰكِنِ اخْتَلَفُوا فَمِنْهُمْ مَنْ آمَنَ وَمِنْهُمْ مَنْ كَفَرَ ۚ وَلَوْ شَاءَ اللَّهُ مَا اقْتَتَلُوا وَلَٰكِنَّ اللَّهَ يَفْعَلُ مَا يُرِيدُ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

እነዚህን መልክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን፡፡ ከእነርሱ ውስጥ አላህ ያነጋገረው አልለ፡፡ ከፊሎቻቸውንም በደረጃዎች ከፍ አደረገ፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው፡፡ በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው፡፡ አላህ በሻ ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ (ከመልክተኞቹ) በኋላ የነበሩት ግልጽ ታምራቶች ከመጡላቸው በኋላ ባልተጋደሉ ነበር፡፡ ግን ተለያዩ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ያመነ ሰው አልለ፡፡ ከነርሱም ውስጥ የካደ ሰው አልለ፡፡ አላህ በሻ ኖሮ ባልተዋጉ (ባልተለያዩ) ነበር፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ይሠራል፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

እነዚያን መልዕክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን። ከእነርሱ መካከልም አላህ ያነጋገረው አለ። ከፊሎቻቸውንም በደረጃ ከሌሎች ከፍ አድርጓል። የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ተዐምራት ሰጠነው። በቅዱስ መንፈስም (በመላኩ ጂብሪል) አበረታነው። አላህ በፈለገ ኖሮ እነዚያ ከእነርሱ በኋላ የነበሩት መረጃው ከመጣላቸው በኋላ እርስ በእርሳቸው ባልተዋጉ ነበር። ግን ተለያዩ። በመሆኑም ከመሀከላቸው ትክክለኛ አማኝ ክፍል አለ። ከመሀከላቸዉም ከሃዲ አለ። አላህ በፈለገ ኖሮ እርስ በእርሳቸው ባልተዋጉ ነበር። አላህ ግን የሚሻውን ሁሉ ይሰራል።

Africa Academy