Al-Baqarah 2:255

Compare 2 Amharic translations

اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ۚ لَا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلَا نَوْمٌ ۚ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ مَنْ ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِنْدَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ ۚ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ ۖ وَلَا يُحِيطُونَ بِشَيْءٍ مِنْ عِلْمِهِ إِلَّا بِمَا شَاءَ ۚ وَسِعَ كُرْسِيُّهُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ ۖ وَلَا يَئُودُهُ حِفْظُهُمَا ۚ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)፡፡ መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡ እርሱ የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

አላህ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም። አላህ ምንግዜም ሕያው፤ በራሱ የተብቃቃ ነው። ማንጎላጀትም ሆነ እንቅልፍ አትይዘዉም። በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው። ያ እርሱ ዘንድ በፍቃዱ ቢሆን እንጂ የሚያማልድ ማን ነው? (ከፍጡራን) ሁሉ በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ጠንቅቆ ያውቃል። በሻው ነገር እንጂ ከእውቀቱ (ፍጡራን) በምንም ነገር አያካብቡም። መንበሩ የሰማያትንና የምድርን ስፋት ይበልጣል። ጥበቃቸዉም አያቅተዉም። እርሱ የሁሉ የበላይና ታላቅ ነው።

Africa Academy