Al-Baqarah 2:260

Compare 2 Amharic translations

وَإِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّ أَرِنِي كَيْفَ تُحْيِي الْمَوْتَىٰ ۖ قَالَ أَوَلَمْ تُؤْمِنْ ۖ قَالَ بَلَىٰ وَلَٰكِنْ لِيَطْمَئِنَّ قَلْبِي ۖ قَالَ فَخُذْ أَرْبَعَةً مِنَ الطَّيْرِ فَصُرْهُنَّ إِلَيْكَ ثُمَّ اجْعَلْ عَلَىٰ كُلِّ جَبَلٍ مِنْهُنَّ جُزْءًا ثُمَّ ادْعُهُنَّ يَأْتِينَكَ سَعْيًا ۚ وَاعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ኢብራሂምም «ጌታዬ ሆይ! ሙታንን እንዴት ሕያው እንደምታደርግ አሳየኝ» ባለ ጊዜ (አስታውስ፡፡) አላህ ፡- «አላመንክምን» አለው፡፡ «አይደለም (አምኛለሁ)፤ ግን ልቤ እንዲረጋ» ነው አለ፡፡ (አላህም)፡- «ከበራሪዎች (ከወፎች) አራትን ያዝ፡፡ ወደ አንተም ሰብስባቸው፡፡ (ቆራርጣቸውም)፤ ከዚያም በየኮረብታው ሁሉ ላይ ከነርሱ ቁራጭን አድርግ፡፡ ከዚያም ጥራቸው፤ ፈጥነው ይመጡሃልና፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ መኾኑን ዕወቅ» አለው፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ኢብራሂም «ጌታዬ ሆይ! ሙታንን እንዴት ሕያው እንደምታደርግ እስቲ አሳየኝ» ባለ ጊዜ የሆነውን ታሪክ አስታውስ። አላህ፡- «አላመንክምን?» አለው። ኢብራሂምም «በፍጹም (አይደለም) አምኛለሁ። ግን ልቤ ሙሉ በሙሉ እንዲረጋጋ ነው።» አለው። አላህም፡- «አራት ወፎችን ያዝና ወደ አንተ ሰብስባቸው። ከዚያ ቆራርጣቸው። ከዚያም በየኮረብታው ሁሉ ላይ ከእነርሱ ቁራጭ ቁራጭ አካላቸውን አስቀምጥ። ከዚያም ጥራቸው በፍጥነት ወደ አንተ ይመጣሉ። አላህ አሸናፊና ጥበበኛ መሆኑን እወቅ።» አለው።

Africa Academy