እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደዚያ ገንዘቡን ለሰዎች ማሳየት ሲል እንደሚሰጠውና በአላህና በመጨረሻውም ቀን እንደማያምነው ሰው ምጽዋቶቻችሁን በመመጻደቅና በማስከፋት አታበላሹ፡፡ ምሳሌውም በላዩ ዐፈር እንዳለበት ለንጣ ድንጋይ ኃይለኛ ዝናብ እንዳገኘውና ምልጥ አድርጎ እንደተወው ብጤ ነው፡፡ ከሠሩት ነገር በምንም ላይ (ሊጠቀሙ) አይችሉም፡፡ አላህ ከሓዲያንን ሕዝቦች አይመራም፡፡
Al-Baqarah 2:264
Compare 2 Amharic translations
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُبْطِلُوا صَدَقَاتِكُمْ بِالْمَنِّ وَالْأَذَىٰ كَالَّذِي يُنْفِقُ مَالَهُ رِئَاءَ النَّاسِ وَلَا يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۖ فَمَثَلُهُ كَمَثَلِ صَفْوَانٍ عَلَيْهِ تُرَابٌ فَأَصَابَهُ وَابِلٌ فَتَرَكَهُ صَلْدًا ۖ لَا يَقْدِرُونَ عَلَىٰ شَيْءٍ مِمَّا كَسَبُوا ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْكَافِرِينَ
DragHold to move · × to hide
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እንደ እነዚያ ገንዘቡን ለሰዎች ለማሳየት ሲል እንደሚሰጠውና በአላህና በመጨረሻው ቀን እንደማያምነው ሰው ምጽዋቶቻችሁን በመመፃደቅና ተረጂውን በማስከፋት አታበላሹ። የዚህ አይነቱም ድርጊት ምሳሌው በላዩ ላይ አፈር እንዳረፈበት ለስላሳ ድንጋይ ሲሆን እሱም ሀይለኛ ዝናብ አግኝቶት እንደተራቆተ ብጤ ነው። እነኝህ አይነት ሰዎች ከሰሩት ነገር በምኑም ሊጠቀሙ አይችሉም። አላህ ከሓዲያን ሕዝቦችን በፍጹም ወደ ቀናው መንገድ አይመራምና።