Al-Baqarah 2:267

Compare 2 Amharic translations

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَنْفِقُوا مِنْ طَيِّبَاتِ مَا كَسَبْتُمْ وَمِمَّا أَخْرَجْنَا لَكُمْ مِنَ الْأَرْضِ ۖ وَلَا تَيَمَّمُوا الْخَبِيثَ مِنْهُ تُنْفِقُونَ وَلَسْتُمْ بِآخِذِيهِ إِلَّا أَنْ تُغْمِضُوا فِيهِ ۚ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ حَمِيدٌ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ካፈራችሁትና ከዚያም ለእናንተ ከምድር ካወጣንላችሁ ከመልካሙን ለግሱ፡፡ መጥፎውንም (ለመስጠት) አታስቡ፡፡ በእርሱ ዓይኖቻችሁን ጨፍናችሁ እንጂ የማትወስዱት ስትኾኑ ከእርሱ (ከመጥፎው) (ትሰጣላችሁን) አላህ ተብቃቂ ምስጉን መኾኑን ዕወቁ፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ካፈራችሁትና ከዚያ ለእናንተ ከምድር ካወጣንላችሁ ከመልካሙ ለግሱ። መጥፎውንም ለመስጠት አታስቡ። እርሱን ለራሳችሁ አይኖቻችሁን ጨፍናችሁ እንጂ የማትወስዱት ስትሆኑ ከእርሱ (ከመጥፎ) ትሰጣላችሁን? አላህ ተብቃቂና ምስጉን መሆኑን እወቁ።

Africa Academy