እነዚያ አራጣን የሚበሉ ያ ሰይጣን ከመንካቱ የተነሳ የሚጥለው ሰው (ከአውድቁ) እንደሚነሳ ብጤ እንጅ (ከመቃብራቸው) አይነሱም፡፡ ይህ እነርሱ መሸጥ የአራጣ ብጤ ብቻ ነው በማለታቸው ነው፡፡ ግን መሸጥን አላህ ፈቅዷል፡፡ አራጣንም እርም አድርጓል፡፡ ከጌታውም ግሳጼ የመጣለትና የተከለከለ ሰው ለርሱ (ከመከልከሉ በፊት) ያለፈው አለው፡፡ ነገሩም ወደ አላህ ነው፤ (አራጣን ወደ መብላት) የተመለሰም ሰው እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
Al-Baqarah 2:275
Compare 2 Amharic translations
الَّذِينَ يَأْكُلُونَ الرِّبَا لَا يَقُومُونَ إِلَّا كَمَا يَقُومُ الَّذِي يَتَخَبَّطُهُ الشَّيْطَانُ مِنَ الْمَسِّ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَالُوا إِنَّمَا الْبَيْعُ مِثْلُ الرِّبَا ۗ وَأَحَلَّ اللَّهُ الْبَيْعَ وَحَرَّمَ الرِّبَا ۚ فَمَنْ جَاءَهُ مَوْعِظَةٌ مِنْ رَبِّهِ فَانْتَهَىٰ فَلَهُ مَا سَلَفَ وَأَمْرُهُ إِلَى اللَّهِ ۖ وَمَنْ عَادَ فَأُولَٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ
DragHold to move · × to hide
እነዚያ አራጣን የሚበሉ ሁሉ ያ ሰይጣን ሰፍኖበት ራሱን የሚስት ሰው ከአውድቅቱ እንደሚነሳ አይነት ሁነው እንጂ ከመቃብራቸው አይነሱም። ይህም የሆነው እነርሱ መሸጥ ልክ እንደ አራጣ ነው በማለታቸው ነው። አላህ ግን መሸጥን ፈቅዷል። አራጣን እርም አድርጓል። ከጌታው ግሳጼ የመጣለት እና ከዚያ የተከለከለ ሰው ሁሉ ከዚህ አዋጅ በፊት ያካበተውን እንደያዘ መቆየት ይችላል። የወደፊት እጣፈንታው ወደ አላህ ነው። አራጣን ወደ መብላት የተመለሱ ሰዎች እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው። እነርሱ በውስጧ ዘወታሪዎች ናቸው።