Al-Baqarah 2:283

Compare 2 Amharic translations

وَإِنْ كُنْتُمْ عَلَىٰ سَفَرٍ وَلَمْ تَجِدُوا كَاتِبًا فَرِهَانٌ مَقْبُوضَةٌ ۖ فَإِنْ أَمِنَ بَعْضُكُمْ بَعْضًا فَلْيُؤَدِّ الَّذِي اؤْتُمِنَ أَمَانَتَهُ وَلْيَتَّقِ اللَّهَ رَبَّهُ ۗ وَلَا تَكْتُمُوا الشَّهَادَةَ ۚ وَمَنْ يَكْتُمْهَا فَإِنَّهُ آثِمٌ قَلْبُهُ ۗ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

በጉዞ ላይ ብትኾኑና ጸሐፊን ባታገኙ የተጨበጡ መተማመኛዎችን ያዙ፡፡ ከፊላችሁም ከፊሉን ቢያምን ያ የታመነው ሰው አደራውን ያድርስ፡፡ አላህንም ጌታውን ይፍራ፡፡ ምስክርነትንም አትደብቁ፡፡ የሚደብቃትም ሰው እርሱ ልቡ ኃጢኣተኛ ነው፡፡ አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

በጉዞ ላይ ብትሆኑና ጸሐፊ ባታገኙ በእጅ የተጨበጡ መተማመኛዎችን ያዙ። ከፊላችሁ ከፊሉን ቢያምን ያ የታመነው ሰው አደራውን በትክክል ያድርስ። አላህንም ጌታውን ይፍራ። ምስክርነትንም አትደብቁ። ምስክርነትን የሚደብቃት ልበ ኃጢአተኛ ነው። አላህ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነውና።

Africa Academy