Al-Baqarah 2:30

Compare 2 Amharic translations

وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً ۖ قَالُوا أَتَجْعَلُ فِيهَا مَنْ يُفْسِدُ فِيهَا وَيَسْفِكُ الدِّمَاءَ وَنَحْنُ نُسَبِّحُ بِحَمْدِكَ وَنُقَدِّسُ لَكَ ۖ قَالَ إِنِّي أَعْلَمُ مَا لَا تَعْلَمُونَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

(ሙሐመድ ሆይ) ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤» ባለ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ፤ እነርሱም) «በርሷ ውስጥ የሚያጠፋንና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ ላንተም የምንቀድስ ስንኾን?» አሉ፡፡ (አላህ) «እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ለመላዕክት «እኔ በምድር ላይ (ምትክ) ወኪል ላደርግ ነው።» ባለ ጊዜ (የሆነውን ለህዝቦችህ አስታውስ)። «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ፤ የምናሞግስህ ስንሆን በምድር ውስጥ የሚያጠፋንና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን?» አሉ። አላህም «እኔ እናንተ የማታውቁትን ነገር ሁሉ አውቃለሁ» አላቸው።

Africa Academy