የጡርንም ጋራ ከበላያችሁ ያነሳን ስንኾን (በኦሪት ሕግ እንድትሠሩ) ኪዳናችሁን በያዝን ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ «የሰጠናችሁን በኀይል ያዙ፤ ስሙም፤» (አልን)፡፡«ሰማን አመጽንም» አሉ፡፡ የወይፈኑንም ውዴታ በክሕደታቸው ምክንያት በልቦቻቸው ውስጥ ተጠጡ፡፡ «አማኞች እንደኾናችሁ እምነታችሁ በርሱ የሚያዛችሁ ነገር ከፋ!» በላቸው፡፡
Al-Baqarah 2:93
Compare 2 Amharic translations
وَإِذْ أَخَذْنَا مِيثَاقَكُمْ وَرَفَعْنَا فَوْقَكُمُ الطُّورَ خُذُوا مَا آتَيْنَاكُمْ بِقُوَّةٍ وَاسْمَعُوا ۖ قَالُوا سَمِعْنَا وَعَصَيْنَا وَأُشْرِبُوا فِي قُلُوبِهِمُ الْعِجْلَ بِكُفْرِهِمْ ۚ قُلْ بِئْسَمَا يَأْمُرُكُمْ بِهِ إِيمَانُكُمْ إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ
DragHold to move · × to hide
የጡርን ጋራ ከበላያችሁ በማንሳት (በተውራት ሕግ እንድትሰሩ) ቃል ኪዳናችሁን በያዝን ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ)። «የሰጠናችሁን በጽናት ያዙ። ያልነውንም ስሙ።» አልን። «ሰማን ግን አመጽን» አሉ። የወይፈኑም ውዴታ በክህደታቸው ምክንያት በልቦቻቸው ውስጥ ገብቷል። «ትክክለኛ አማኞች እንደሆናችሁ እምነታችሁ የሚያዛችሁ ነገር የከፋ ነው።» በላቸው።