አላህ ለአንድ ሰው በሆዱ ውስጥ ሁለትን ልቦች አላደረገም፡፡ ሚስቶቻችሁንም እነዚያን ከእነርሱ እንደናቶቻችሁ ጀርባዎች ይሁኑብን የምትሏቸውን እናቶቻችሁ አላደረገም፡፡ ልጅ በማድረግ የምታስጠጓቸውንም ልጆቻችሁ አላደረገም፡፡ ይህ በአፎቻችሁ የምትሉት ነው፡፡ አላህም እውነቱን ይናገራል፡፡ እርሱም ትክክለኛውን መንገድ ይመራል፡፡
Al-Ahzab 33:4
Compare 2 Amharic translations
مَا جَعَلَ اللَّهُ لِرَجُلٍ مِنْ قَلْبَيْنِ فِي جَوْفِهِ ۚ وَمَا جَعَلَ أَزْوَاجَكُمُ اللَّائِي تُظَاهِرُونَ مِنْهُنَّ أُمَّهَاتِكُمْ ۚ وَمَا جَعَلَ أَدْعِيَاءَكُمْ أَبْنَاءَكُمْ ۚ ذَٰلِكُمْ قَوْلُكُمْ بِأَفْوَاهِكُمْ ۖ وَاللَّهُ يَقُولُ الْحَقَّ وَهُوَ يَهْدِي السَّبِيلَ
DragHold to move · × to hide
(ሙስሊሞች ሆይ!) አላህ ለአንድ ሰው በሆዱ ውስጥ ሁለትን ልቦች አላደረገም። እነዚያን «እንደናቶቻችን ጀርባዎች ይሁኑብን» የምትሏቸውን ሚስቶቻችሁንም እናቶቻችሁ አላደረገም። ልጅ በማድረግ የምታስጠጓቸውንም ልጆቻችሁ አላደረገም። ይህ በአፎቻችሁ የምትሉት ቃላችሁ ብቻ ነው። አላህ እውነትን ይናገራል። ትክክለኛውን መንገድም ይመራል።