Saba' 34:3

Compare 2 Amharic translations

وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لَا تَأْتِينَا السَّاعَةُ ۖ قُلْ بَلَىٰ وَرَبِّي لَتَأْتِيَنَّكُمْ عَالِمِ الْغَيْبِ ۖ لَا يَعْزُبُ عَنْهُ مِثْقَالُ ذَرَّةٍ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ وَلَا أَصْغَرُ مِنْ ذَٰلِكَ وَلَا أَكْبَرُ إِلَّا فِي كِتَابٍ مُبِينٍ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

እነዚያ የካዱትም «ሰዓቲቱ አትመጣብንም» አሉ፡፡ በላቸው «አይደለም፤ ሩቁን ሁሉ ዐዋቂ በኾነው ጌታዬ እምላለሁ፡፡ በእርግጥ ትመጣባችኋለች፡፡ የብናኝ ክብደት ያክል እንኳ በሰማያትና በምድር ውስጥ ከእርሱ አይርቅም፡፡ ከዚህ ያነሰም ኾነ የበለጠ የለም በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢኾን እንጅ፡፡»

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ የካዱትም ሰዎች «ሰዓቲቱ አትመጣብንም» አሉ፡ «ጉዳዩ እንዳሰባችሁት አይደለም። ሩቁን ሁሉ አዋቂ በሆነው ጌታዬ እምላለሁ። በእርግጥ ትመጣባችኋለች። የብናኝ ክብደት ያክል እንኳ በሰማያትና በምድር ውስጥ ከእሱ አይሰወርም አይርቅም። ከዚህ ያነሰም ሆነ የበለጠ የለም በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢሆን እንጂ።» በላቸው

Africa Academy