የዐረብ ዘላኖች «አምነናል» አሉ፡፡ «አላመናችሁም፤ ግን ሰልመናል በሉ፡፡ «እምነቱም በልቦቻችሁ ውስጥ ገና (ጠልቆ) አልገባም፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ብትታዘዙ ከሥራዎቻችሁ ምንንም አያጎድልባችሁም፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው፡፡
Al-Hujurat 49:14
Compare 2 Amharic translations
قَالَتِ الْأَعْرَابُ آمَنَّا ۖ قُلْ لَمْ تُؤْمِنُوا وَلَٰكِنْ قُولُوا أَسْلَمْنَا وَلَمَّا يَدْخُلِ الْإِيمَانُ فِي قُلُوبِكُمْ ۖ وَإِنْ تُطِيعُوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ لَا يَلِتْكُمْ مِنْ أَعْمَالِكُمْ شَيْئًا ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَحِيمٌ
DragHold to move · × to hide
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዐረብ ዘላኖች አምነናል አሉ። «አላመናችሁም ግን ሰልመናል በሉ እምነቱም በልቦቻችሁ ውስጥ ገና ጠልቆ አልገባም። አላህንና መልዕክተኛውን ብትታዘዙ ከስራዎቻችሁ ምንም አይጎድልባችሁም። አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና» በላቸው።