እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ የመርየምን ልጅ አልመሲሕን እናቱንም በምድር ያለንም ሁሉ ለማጥፋት ቢሻ ከአላህ ማዳንን የሚችል ማነው በላቸው፡፡ የሰማያትና የምድር የመካከላቸውም ንግሥና የአላህ ብቻ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
Al-Ma'idah 5:17
Compare 2 Amharic translations
لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۚ قُلْ فَمَنْ يَمْلِكُ مِنَ اللَّهِ شَيْئًا إِنْ أَرَادَ أَنْ يُهْلِكَ الْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُ وَمَنْ فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ۗ وَلِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا ۚ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
DragHold to move · × to hide
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ «አላህ ማለት የመርየም ልጅ አልመሲህ ነው።» ያሉ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ በአላህ ካዱ። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ የመርየምን ልጅ አልመሲህንና እናቱን እንደዚሁም በምድር ያለን ፍጡር ሁሉ ለማጥፋት ቢሻ ከአላህ ማዳን የሚችል ማን ነው? የሰማያትና የምድር የመካከላቸዉም ንግስና የአላህ ብቻ ነው። የሚፈልገውን ይፈጥራል። አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና።» በላቸው።