Al-Ma'idah 5:2

Compare 2 Amharic translations

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُحِلُّوا شَعَائِرَ اللَّهِ وَلَا الشَّهْرَ الْحَرَامَ وَلَا الْهَدْيَ وَلَا الْقَلَائِدَ وَلَا آمِّينَ الْبَيْتَ الْحَرَامَ يَبْتَغُونَ فَضْلًا مِنْ رَبِّهِمْ وَرِضْوَانًا ۚ وَإِذَا حَلَلْتُمْ فَاصْطَادُوا ۚ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ أَنْ صَدُّوكُمْ عَنِ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ أَنْ تَعْتَدُوا ۘ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የአላህ (ክልክል ያደረጋቸውን) ምልክቶች የተፈቀዱ አታድርጉ፡፡ የተከበረውንም ወር በመጋደል አትድፈሩ፡፡ ወደ መካ የሚነዱትን መስዋዕትና የሚታበቱባቸውንም ገመዶች ከጌታቸው ችሮታንና ውዴታን ፈልገው ወደ ተከበረው ቤት አሳቢዎችንም ሰዎች (አትንኩ)፡፡ ከሐጅም ሥራ በወጣችሁ ጊዜ ዐድኑ፡፡ ከተከበረው መስጊድ ስለከለከሉዋችሁ ሰዎችን መጥላትም (በነሱ ላይ) ወሰን እንድታልፉ አይገፋፋችሁ፡፡ በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ምልክቶች ይሆኑ ዘንድ የከለከላቸውን ነገሮች የተፈቀዱ አታድርጉ። የተከበረውንም ወር በውስጡ ጦርነትን በማካሄድ አትድፈሩት። ወደ መካ የሚነዱትን የመስዋዕት እንስሳትና የሚታበቱባቸውን ገመዶች፤ ከጌታቸው ችሮታንና ውዴታን ፈልገው ወደ ተከበረው ቤት አሳቢዎችንም በክፉ አትንኳቸው። የሐጅን ስራ ፈጽማችሁ ባጠናቀቃችሁ ጊዜ የዱር አውሬዎችን እንደልባችሁ አድኑ። ከተከበረው መስጊድ ስለከለከሏችሁ ሰዎችን መጥላታችሁ በእነርሱ ላይ ወሰንን እንድታልፉና (ፍትህን እንድታዛቡ) አይገፋፉችሁ። በበጎ ተግባርና አላህን በመፍራት እርስ በእርስ ተባበሩ። ኃጢአትና ወሰንን በማለፍ ግን አትተባበሩ። አላህን በትክክል ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና።

Africa Academy