እርሱ ያ ከመጽሐፉ ሰዎች እነዚያን የካዱትን ከቤቶቻቸው ለመጀመሪያው ማውጣት ያወጣቸው ነው፡፡ መውጣታቸውን አላሰባችሁም፡፡ እነርሱም ምሽጎቻቸው ከአላህ (ኀይል) የሚከላከሉላቸው መኾናቸውን አሰቡ፡፡ አላህም ካላሰቡት ስፍራ መጣባቸው፡፡ በልቦቻቸውም ውስጥ መርበድበድን ጣለባቸው፡፡ ቤቶቻቸውን በእጆቻቸውና በምእምናኖቹ እጆች ያፈርሳሉ፡፡ አስተውሉም የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ!
Al-Hashr 59:2
Compare 2 Amharic translations
هُوَ الَّذِي أَخْرَجَ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ مِنْ دِيَارِهِمْ لِأَوَّلِ الْحَشْرِ ۚ مَا ظَنَنْتُمْ أَنْ يَخْرُجُوا ۖ وَظَنُّوا أَنَّهُمْ مَانِعَتُهُمْ حُصُونُهُمْ مِنَ اللَّهِ فَأَتَاهُمُ اللَّهُ مِنْ حَيْثُ لَمْ يَحْتَسِبُوا ۖ وَقَذَفَ فِي قُلُوبِهِمُ الرُّعْبَ ۚ يُخْرِبُونَ بُيُوتَهُمْ بِأَيْدِيهِمْ وَأَيْدِي الْمُؤْمِنِينَ فَاعْتَبِرُوا يَا أُولِي الْأَبْصَارِ
DragHold to move · × to hide
እርሱ ያ! ከመጽሐፍ ሰዎች መካከል እነዚያን በአላህ የካዱትን ወገኖች ከቤቶቻቸው የመጀመሪያውን ማስወጣት ያስወጣቸው ነው። (ሙስሊሞች ሆይ!) መውጣታቸውንም አላሰባችሁትም ነበር። እነርሱም ምሽጎቻቸው ከአላህ ኃይል የሚከላከሉላቸው መሆናቸውን አሰቡ። አላህ ግን ካላሰቡት በኩል መጣባቸው። እናም በልቦቻቸው ውስጥ መርበድበድን (ፍርሃትን) ጣለባቸው። ቤቶቻቸውን በገዛ እጆቻቸውና በትክክለኛ አማኞች እጅ ያፈርሳሉ (አፈረሱ)። እናንተ የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ! አስተውሉ።