Al-Hashr 59:7

Compare 2 Amharic translations

مَا أَفَاءَ اللَّهُ عَلَىٰ رَسُولِهِ مِنْ أَهْلِ الْقُرَىٰ فَلِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ وَلِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَابْنِ السَّبِيلِ كَيْ لَا يَكُونَ دُولَةً بَيْنَ الْأَغْنِيَاءِ مِنْكُمْ ۚ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانْتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

አላህ ከከተሞቹ ሰዎች (ሀብት) በመልክተኛው ላይ የመለሰው (ሀብት) ከእናንተ ውስጥ በሀብታሞቹ መካከል ተዘዋዋሪ እንዳይኾን፡፡ ለአላህና ለመልክተኛው፣ ለዝምድና ባለቤትም፣ አባት ለሌላቸው ልጆችም፣ ለድኾችም፣ ለመንገደኛም (የሚስሰጥ) ነው፡፡ መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

አላህ ከከተሞች ሰዎች ሀብት መካከል በመልዕክተኛው ላይ የመለሰው ሀብት ከናንተ ውስጥ በሀብታሞች መካከል ብቻ ተዘዋዋሪ እንዳይሆን ለአላህና ለመልዕክተኛው፤ ለዝምድና ባለቤትም፤ አባት ለሌላቸው የቲም ልጆችም፤ ለድሆችና፤ ለመንገደኛ፤ የሚሰጥ ነው። መልዕክተኛው የሰጣችሁን ሁሉ ማንኛዉም ነገር ያዙት። የከለከላችሁን ነገር ሁሉም ተከልከሉ። አላህን ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና።

Africa Academy