እነዚያንም ከአላህ ሌላ የሚገዙዋቸውን (ጣዖታትን) አትስደቡ፡፡ ድንበርን በማለፍ ያለዕውቀት አላህን ይሰድባሉና፡፡ እንደዚሁ ለሕዝቦች ሁሉ ሥራቸውን ደግ አስመሰልንላቸው፡፡ ከዚያም መመለሻቸው ወደ ጌታቸው ነው፡፡ ይሠሩት የነበሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል፡፡
Al-An'am 6:108
Compare 2 Amharic translations
وَلَا تَسُبُّوا الَّذِينَ يَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ فَيَسُبُّوا اللَّهَ عَدْوًا بِغَيْرِ عِلْمٍ ۗ كَذَٰلِكَ زَيَّنَّا لِكُلِّ أُمَّةٍ عَمَلَهُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّهِمْ مَرْجِعُهُمْ فَيُنَبِّئُهُمْ بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ
DragHold to move · × to hide
(ሙስሊሞች ሆይ!) እነዚያንም ከአላህ ሌላ የሚገዟቸውን ጣዖታትን አትስደቡ። እነርሱም ድንበርን በማለፍ ያለ እውቀት አላህን ይሰድባሉና። ልክ እንደዚሁ ለህዝቦች ሁሉ ስራቸውን ደግ አስመሰልንላቸው። ከዚያም መመለሻቸው ወደ ጌታቸው ብቻ ነው። ይሰሩት የነበሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል።