Al-An'am 6:138

Compare 2 Amharic translations

وَقَالُوا هَٰذِهِ أَنْعَامٌ وَحَرْثٌ حِجْرٌ لَا يَطْعَمُهَا إِلَّا مَنْ نَشَاءُ بِزَعْمِهِمْ وَأَنْعَامٌ حُرِّمَتْ ظُهُورُهَا وَأَنْعَامٌ لَا يَذْكُرُونَ اسْمَ اللَّهِ عَلَيْهَا افْتِرَاءً عَلَيْهِ ۚ سَيَجْزِيهِمْ بِمَا كَانُوا يَفْتَرُونَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

በሐሳባቸውም ይህች እርም የኾነች ለማዳ እንስሳና አዝመራ ናት፡፡ የምንሻው ሰው እንጂ ሌላ አይበላትም፡፡ (ይህች) ጀርቦችዋ እርም የተደረገች ለማዳ እንስሳም ናት (አትጫንም)፡፡ ይህች በርሷ ላይ የአላህን ስም (ስትታረድ) የማይጠሩባትም እንስሳ ናት አሉ፡፡ በእርሱ ላይ ለመቅጠፍ (ነገሩን ወደ አላህ አስጠጉ)፡፡ ይቀጥፉት በነበሩት ነገር በእርግጥ ይቀጣቸዋል፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

በሀሳባቸውም «እነዚህ እርም የሆኑ ለማዳ እንሰሳና አዝመራ ናቸው። የምንሻለት ሰው እንጂ ሌላ ማንም አይበላቸዉም። እነዚህ ደግሞ ጀርባዎቻቸው እርም የተደረገ ለማዳ እንሰሳ ናቸው። አይጫኑም። እነዚህ ሲታረዱ በእነርሱ ላይ የአላህን ስም የማይጠሩባቸዉም እንሰሳት ናቸው።» አሉ። በእርሱ ላይ ለመቅጠፍ ነገሩን ወደ አላህ አስጠጉ። ይቀጥፉት በነበሩት ነገር በእርግጥ ይቀጣቸዋል።

Africa Academy