«ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ ሩቅንም አላውቅም፡፡ ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም፡፡ ወደእኔ የሚወርድልኝን እንጅ ሌላን አልከተልም» በላቸው፡፡ «ዕውርና የሚያይ ይስተካከላሉን አታስተነትኑምን» በላቸው፡፡
Al-An'am 6:50
Compare 2 Amharic translations
قُلْ لَا أَقُولُ لَكُمْ عِنْدِي خَزَائِنُ اللَّهِ وَلَا أَعْلَمُ الْغَيْبَ وَلَا أَقُولُ لَكُمْ إِنِّي مَلَكٌ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰ إِلَيَّ ۚ قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الْأَعْمَىٰ وَالْبَصِيرُ ۚ أَفَلَا تَتَفَكَّرُونَ
DragHold to move · × to hide
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልላችሁም። ሩቅ ሚስጥርንም አላውቅም። መልዓክ ነኝም አልልም። ወደ እኔ የሚወርድልኝን መልዕክት ብቻ እንጂ ሌላን አልከተልም።» በላቸው። «እውርና የሚያይ ይስተካከላሉን? አታስተነትኑምን!» በላቸው።