እነዚያንም ሃይማኖታቸውን ጨዋታና ላግጣ አድርገው የያዙትን ቅርቢቱም ሕይወት ያታለለቻቸውን ተዋቸው፡፡ በእርሱም (በቁርኣን) ነፍስ በሠራችው ሥራ እንዳትጠፋ አስታውስ፡፡ ለእርሷ ከአላህ ሌላ ረዳትና አማላጅ የላትም፡፡ በመበዢያም ሁሉ ብትበዥ ከርሷ አይወሰድም፡፡ እነዚህ እነዚያ በሠሩት ሥራ የተጠፉት ናቸው፡፡ ለነሱ ይክዱ በነበሩት ምክንያት ከፈላ ውሃ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
Al-An'am 6:70
Compare 2 Amharic translations
وَذَرِ الَّذِينَ اتَّخَذُوا دِينَهُمْ لَعِبًا وَلَهْوًا وَغَرَّتْهُمُ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا ۚ وَذَكِّرْ بِهِ أَنْ تُبْسَلَ نَفْسٌ بِمَا كَسَبَتْ لَيْسَ لَهَا مِنْ دُونِ اللَّهِ وَلِيٌّ وَلَا شَفِيعٌ وَإِنْ تَعْدِلْ كُلَّ عَدْلٍ لَا يُؤْخَذْ مِنْهَا ۗ أُولَٰئِكَ الَّذِينَ أُبْسِلُوا بِمَا كَسَبُوا ۖ لَهُمْ شَرَابٌ مِنْ حَمِيمٍ وَعَذَابٌ أَلِيمٌ بِمَا كَانُوا يَكْفُرُونَ
DragHold to move · × to hide
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያንም ሃይማኖታቸውን ጨዋታና ቀልድ አድርገው የያዙትንና ቅርቢቱ ሕይወት ያታለለቻቸውን ተዋቸው። ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ እንዳትጠፋ በእርሱ (በቁርአን) አስታውስ። ለእርሷ ከአላህ ሌላ ወዳጅም ሆነ አማላጅ ማንም የላትም። ፊዳ የተባለን ሁሉ ብትከፍል እንኳን ተቀባይነት የላትም። እነዚያ በሰሩት ስራ ለጥፋት የተሰጡት ናቸው። በክህደታቸው ምክንያት ከፈላ ውሃ መጠጥና አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።