በአላህም ላይ እብለትን ከቀጣጠፈ ወይም ወደርሱ ምንም ያልተወረደለት ሲኾን «ወደኔ ተወረደልኝ» ካለና፡-«አላህም ያወረደውን ብጤ በእርግጥ አወርዳለሁ» ካለ ሰው ይበልጥ በዳይ ማን ነው በደለኞችንም በሞት መከራዎች ውስጥ በኾኑ ጊዜ መላእክት እጆቻቸውን ዘርጊዎች ኾነው « (ለቅጥጥብ) ነፍሶቻችሁን አውጡ፤ በአላህ ላይ እውነት ያልኾነን ነገር ትናገሩ በነበራችሁትና ከአንቀጾቹም ትኮሩ በነበራችሁት ምክንያት ዛሬ የውርደትን ቅጣት ትመነዳላችሁ» (የሚሏቸው ሲኾኑ) ብታይ ኖሮ (አስደናቂን ነገር ባየህ ነበር)፡፡
Al-An'am 6:93
Compare 2 Amharic translations
وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا أَوْ قَالَ أُوحِيَ إِلَيَّ وَلَمْ يُوحَ إِلَيْهِ شَيْءٌ وَمَنْ قَالَ سَأُنْزِلُ مِثْلَ مَا أَنْزَلَ اللَّهُ ۗ وَلَوْ تَرَىٰ إِذِ الظَّالِمُونَ فِي غَمَرَاتِ الْمَوْتِ وَالْمَلَائِكَةُ بَاسِطُو أَيْدِيهِمْ أَخْرِجُوا أَنْفُسَكُمُ ۖ الْيَوْمَ تُجْزَوْنَ عَذَابَ الْهُونِ بِمَا كُنْتُمْ تَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ غَيْرَ الْحَقِّ وَكُنْتُمْ عَنْ آيَاتِهِ تَسْتَكْبِرُونَ
DragHold to move · × to hide
በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም ወደ እርሱ ምንም ያልተወረደለት ሲሆን «ወደ እኔ ተወረደልኝ።» ካለና «አላህ ያወረደውን አይነት ማውረድም በእርግጥ እችላለሁ።» ካለ ይበልጥ እራሱን በዳይ ማን ነው? በደለኞችን በሞት መከራዎች ውስጥ በሆኑ ጊዜ መላዕክት እጆቻቸውን ዘርጊዎች ሆነው (ለቅጥጥብ) «ነፍሶቻችሁን አውጡ። በአላህ ላይ እውነትን ያልሆነን ነገር ትናገሩም የነበራችሁና በአናቅጹም ላይ ትኮሩ በነበራችሁት ምክንያት ዛሬ የውርደት ቅጣት ትመነዳላችሁ» በሚሏቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ባየህ ነበር)።