እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ሕዝቦች ያችን በውስጧ በረከት ያደረግንባትን ምድር ምሥራቆችዋንም ምዕራቦቿንም አወረስናቸው፡፡ የጌታህም መልካሚቱ ቃል በእስራኤል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች፡፡ ፈርዖንና ሰዎቹም ይሠሩት የነበረውን (ሕንጻ) ዳስ ያደርጉትም የነበረውን አፈረስን፡፡
Al-A'raf 7:137
Compare 2 Amharic translations
وَأَوْرَثْنَا الْقَوْمَ الَّذِينَ كَانُوا يُسْتَضْعَفُونَ مَشَارِقَ الْأَرْضِ وَمَغَارِبَهَا الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا ۖ وَتَمَّتْ كَلِمَتُ رَبِّكَ الْحُسْنَىٰ عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ بِمَا صَبَرُوا ۖ وَدَمَّرْنَا مَا كَانَ يَصْنَعُ فِرْعَوْنُ وَقَوْمُهُ وَمَا كَانُوا يَعْرِشُونَ
DragHold to move · × to hide
እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ህዝቦች ያቺን በውስጧ በረከት ያደረግንባትን ምድር ምስራቋንም ምዕራቧንም አወረስናቸው። (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የጌታህ መልካሚቱ ቃል በኢስራኢል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች። ፈርዖንና ሰዎቹ ይሰሩት የነበረውን ህንጻና ዳስ ያደርጉት የነበረውንም አፈረስን።