Al-A'raf 7:143

Compare 2 Amharic translations

وَلَمَّا جَاءَ مُوسَىٰ لِمِيقَاتِنَا وَكَلَّمَهُ رَبُّهُ قَالَ رَبِّ أَرِنِي أَنْظُرْ إِلَيْكَ ۚ قَالَ لَنْ تَرَانِي وَلَٰكِنِ انْظُرْ إِلَى الْجَبَلِ فَإِنِ اسْتَقَرَّ مَكَانَهُ فَسَوْفَ تَرَانِي ۚ فَلَمَّا تَجَلَّىٰ رَبُّهُ لِلْجَبَلِ جَعَلَهُ دَكًّا وَخَرَّ مُوسَىٰ صَعِقًا ۚ فَلَمَّا أَفَاقَ قَالَ سُبْحَانَكَ تُبْتُ إِلَيْكَ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُؤْمِنِينَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ሙሳም ለቀጠሯችን በመጣና ጌታውም ባነጋገረው ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! (ነፍስህን) አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና» አለ፡፡ (አላህም)፡- «በፍጹም አታየኝም ግን ወደ ተራራው ተመልከት፡፡ በስፍራውም ቢረጋ በእርግጥ ታየኛለህ» አለው፡፡ ጌታው ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው፡፡ ሙሳም ጮሆ ወደቀ፡፡ በአንሰራራም ጊዜ «ጥራት ይገባህ፡፡ ወዳንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም (በወቅቱ) የምእምናን መጀመሪያ ነኝ» አለ፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

ሙሳ ለቀጠሮው በመጣና ጌታዉም ባነጋገረው ጊዜ፡ «ጌታዬ ሆይ! በእርግጥ ራስህን አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና።» አለ። (አላህም)፡- «እኔን በፍጹም አታየኝም። ግን ወደ ተራራው ተመልከትና በስፍራው ከረጋ አንተም ታየኛለህ።» አለው። ጌታዉም ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው። ሙሳም ራሱን ስቶ ወደቀ። በአንሰራራም ጊዜ «ጌታዬ ጥራት ይገባህ ወደ አንተ ተመለስኩ። እኔም በጊዜያቴ የአማኞች መጀመሪያ ነኝ።» አለ።

Africa Academy