Al-A'raf 7:157

Compare 2 Amharic translations

الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الرَّسُولَ النَّبِيَّ الْأُمِّيَّ الَّذِي يَجِدُونَهُ مَكْتُوبًا عِنْدَهُمْ فِي التَّوْرَاةِ وَالْإِنْجِيلِ يَأْمُرُهُمْ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَاهُمْ عَنِ الْمُنْكَرِ وَيُحِلُّ لَهُمُ الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ وَيَضَعُ عَنْهُمْ إِصْرَهُمْ وَالْأَغْلَالَ الَّتِي كَانَتْ عَلَيْهِمْ ۚ فَالَّذِينَ آمَنُوا بِهِ وَعَزَّرُوهُ وَنَصَرُوهُ وَاتَّبَعُوا النُّورَ الَّذِي أُنْزِلَ مَعَهُ ۙ أُولَٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ለእነዚያ ያንን እነሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነቢይ የኾነውን መልክተኛ የሚከተሉ ለኾኑት (በእርግጥ እጽፍለታለሁ)፡፡ በበጎ ሥራ ያዛቸዋል፡፡ ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል፡፡ መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፡፡ መጥፎ ነገሮችንም በእነርሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል፡፡ ከእነሱም ላይ ሸክማቸውንና እነዚያንም በእነርሱ ላይ የነበሩትን እንዛዝላዎች (ከባድ ሕግጋቶች) ያነሳላቸዋል፡፡ እነዚያም በእርሱ ያመኑ ያከበሩትም የረዱትም ያንንም ከእርሱ ጋር የተወረደውን ብርሃን የተከተሉ እነዚያ እነሱ የሚያድኑ ናቸው፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

ለእነዚያ ያንን እነርሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብን ነብይ የሚከተሉ ለሆኑ (ሁሉ በእርግጥ እጽፋታለሁ)። በበጎ ሥራ ያዛቸዋል። ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል። መልካም ነገሮችንም ለእነርሱ ይፈቅድላቸዋል። መጥፎ ነገሮችንም በነሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል። ከእነርሱም ላይ ሸክማቸውንና እነዚያንም በእነርሱ ላይ የነበሩትን እንደ እንዛዝላ ይከብዱ የነበሩ ከባድ ህግጋትን ያነሳላቸዋል። እነዚያ በእርሱ ያመኑ፤ ያከበሩት፤ የረዱትና ያንን ከርሱ ጋር የተወረደውን ብርሃን የተከተሉ ሁሉ እነዚያ እነርሱ ከቅጣት የሚድኑ ናቸው።

Africa Academy