Al-A'raf 7:160

Compare 2 Amharic translations

وَقَطَّعْنَاهُمُ اثْنَتَيْ عَشْرَةَ أَسْبَاطًا أُمَمًا ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ إِذِ اسْتَسْقَاهُ قَوْمُهُ أَنِ اضْرِبْ بِعَصَاكَ الْحَجَرَ ۖ فَانْبَجَسَتْ مِنْهُ اثْنَتَا عَشْرَةَ عَيْنًا ۖ قَدْ عَلِمَ كُلُّ أُنَاسٍ مَشْرَبَهُمْ ۚ وَظَلَّلْنَا عَلَيْهِمُ الْغَمَامَ وَأَنْزَلْنَا عَلَيْهِمُ الْمَنَّ وَالسَّلْوَىٰ ۖ كُلُوا مِنْ طَيِّبَاتِ مَا رَزَقْنَاكُمْ ۚ وَمَا ظَلَمُونَا وَلَٰكِنْ كَانُوا أَنْفُسَهُمْ يَظْلِمُونَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

ዐሥራ ሁለት ነገዶች ሕዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው፡፡ ወደ ሙሳም ወገኖቹ መጠጣትን በፈለጉበት ጊዜ «ድንጋዩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክን፡፡ (መታውም) ከእርሱ ዐሥራ ሁለት ምንጮችም ፈለቁ፡፡ ሰዎቹ ሁሉ መጠጫቸውን በእርግጥ ዐወቁ፡፡ በእነሱም ላይ ደመናን አጠለልን፡፡ በእነሱም ላይ መናንና ድርጭትን አወረድን፡፡ «ከሰጠናችሁም መልካም ሲሳይ ብሉ» (አልን፤ ጸጋችንን በመካዳቸው) አልበደሉንምም፡፡ ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ነበሩ፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

የሙሳን ህዝቦች አስራ ሁለት ነገዶች አድርገን ከፋፈልናቸው። ወደ ሙሳም ወገኖቹ ውሃን በፈለጉበት ጊዜ ድንጋዩን በበትርህ ምታው ስንል ላክን። (መታዉም) አስራ ሁለት ምንጮች ፈለቁ። ሰዎቹ ሁሉ መጠጫቸውን በእርግጥ አወቁ። በእነርሱም ላይ ዳመናን አጠለልን። በእነርሱም ላይ "መንን" እና ድርጭትን አወረድን። «ከሰጠናችሁም መልካም ሲሳይ ብሉ።» አልን። ጸጋዎቻችንን በመካዳቸው አልበደሉንም። ግን ነፍሶቻቸውን የሚበድሉ ህዝቦች ነበሩ።

Africa Academy