Al-A'raf 7:43

Compare 2 Amharic translations

وَنَزَعْنَا مَا فِي صُدُورِهِمْ مِنْ غِلٍّ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهِمُ الْأَنْهَارُ ۖ وَقَالُوا الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي هَدَانَا لِهَٰذَا وَمَا كُنَّا لِنَهْتَدِيَ لَوْلَا أَنْ هَدَانَا اللَّهُ ۖ لَقَدْ جَاءَتْ رُسُلُ رَبِّنَا بِالْحَقِّ ۖ وَنُودُوا أَنْ تِلْكُمُ الْجَنَّةُ أُورِثْتُمُوهَا بِمَا كُنْتُمْ تَعْمَلُونَ

القرآن الكريم

DragHold to move · × to hide

በደረቶቻቸው ውስጥ ያለውንም ጥላቻ እናስወግዳለን፡፡ ወንዞች በሥሮቻቸው ይፈሳሉ፡፡ «ለዚያም ወደዚህ (ላደረሰን ሥራ) ለመራን አላህ ምስጋና ይገባው፡፡ አላህ ባልመራንም ኖሮ አንመራም ነበር፡፡ የጌታችን መልክተኞች በእውነት ላይ ሲኾኑ በእርግጥ መጥተውልናል» ይላሉ፡፡ ይህች ገነት ትሠሩት በነበራችሁት ተሰጣችኋት በማለት ይጠራሉ፡፡

Muhammed Sadiq and Muhammed al-Thani Habib

በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ጥላቻም እናስወግዳለን። ወንዞች በሥሮቻቸው ይፈሳሉ። «ወደዚህ (ገነት) ላደረሰን ሥራ ለመራን ለአላህ ምስጋና ይገባው። አላህ ባልመራን ኖሮ ወደዚህ አንመራም ነበር። የጌታችን መልዕክተኞች በእውነት ላይ ሲሆኑ መጥተውልናል።» ይላሉ። «ይህ ገነት ትሠሩት በነበራችሁት እንድትወርሱት የተደረጋችሁት ነው።» በማለት ይጠራሉ።

Africa Academy