ወደ ሰሙድም ወንድማቸውን ሷሊህን (ላክን) ፡፡ አላቸው «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ (እውነተኛ ለመኾኔ) ከጌታችሁ የኾነች ምልክት በእርግጥ መጥታላችኋለች፡፡ ይህች ለእናንተ ተዓምር ስትኾን የአላህ ግመል ናትና ተዋት፡፡ በአላህ ምድር ውስጥ ትብላ፤ (ትጠጣም)፡፡ በክፉ አትንኳትም፡፡ አሳማሚ ቅጣት ይይዛችኋልና፡፡»
Al-A'raf 7:73
Compare 2 Amharic translations
وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا ۗ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ قَدْ جَاءَتْكُمْ بَيِّنَةٌ مِنْ رَبِّكُمْ ۖ هَٰذِهِ نَاقَةُ اللَّهِ لَكُمْ آيَةً ۖ فَذَرُوهَا تَأْكُلْ فِي أَرْضِ اللَّهِ ۖ وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوءٍ فَيَأْخُذَكُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
DragHold to move · × to hide
ወደ ሰሙድ ህዝቦችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን። «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ብቻ ተገዙ። ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ምንም አምላክ የላችሁም። እውነተኛ ለመሆኔ ከጌታችሁ የሆነች ምልክት በእርግጥ መጥታላችኋለች። ይህች ለእናንተ ተዓምር ስትሆን የአላህ ግመል ናትና ተዋት። በአላህ ምድር ውስጥ እንደፈለገች ትብላ። በክፉ አትንኳትም። አሳማሚ ቅጣት ይይዛችኋልና።» አለ።